ባለፉት 25 ዓመታት የትግራይ ተወላጆች የያዙትን የፖለቲካ አቋምና ምክንያቶቹ

 ወልዳአብ ደንቡ ፡ 16/12/2016
 
የጥንታውያኖቻችን ዘመን፣ቅማቅሞቻችን ዘመን ፣ የቅምያቶቻችን ዘመን ፣ያያቶቻችን ዘመን ፣ያባቶቻችን ዘመን እያልን ያ ትውልድ ያፈራ ማኅበረስብ ዘመን ተደረሰ ። በሁሉም ዘመን የነበሩት ቀደምቶቻችን የሚታወሱባቸው ገድሎች እና ቅርሶች (ለጋሲ) አልዋቸው ። ስለቅድመ ወያኔ/ህወሃት -ጅግኖቻችን አበይት ወይም ወርቃማው ትውስታችን የሚሆነው- ኢትዮጵያ በመሳፍንት አገዛዝ በነበረበት ዘመንም ሆነ በማአከላዊ መንግሥት መተዳደር ከተጀመረ በኋላ የፖለቲካ ሥልጣንና የምጣኔ ሃብቷ(economy resources) በጨበጡትና ባልጨበጡ ተፎካካሪዮች መካከል -የከረረም ሆነ መለስተኛ ቅራኔዎች ቢኖርዋቸውም – በጋራ የኢትዮጵያ ‘ሉዓላዊነትና ዳርድንበር’ ሲያስከብሩ መኖራቸውን ነው ።

ያያቶቻችን ዘመን የሚተወሰው በአደዋ ጦርነት ሲሆን ያባቶቻችን ዘመን የሚተወሰው በማይጨው ጦርነት ወይም ከሁለተኛው የጣሊያን ወራሪ ሠራዊትጋር በተደረገ ጦርነት ነው። የእኔም አባት ከሁለተኛው የጣሊያን ሠራዊት ጋር ከተፋለሙት ጀገኖች አባቶቻችን አንዱ ነበር።  የእኔ ትውልድ የሚተወሰው ‘ያ ትውልድ’ በሚል ነው  ። ስለያ ትውልድ ቀናኢ ታሪክ በተለያዩ ጸሃፊዮች የተዳሰሰና አድማሰ ሰፊ ስለሆነ ማንጸባረቅ ከምፈልገው  ጉዳይ ጋር ለማገናኝት ያህል ቆንጸል አድርጌ አቀርበዋለሁ ። ማለት  አሁን የሚገዙንን ቁንጮ ባንዳዎችን ፣ በሜኤሶንና በኢሕአፓ መካከል በተፈጠረው  የፖለቲካ መስመር ልዩነት ምክንያት የተፈጠ   ሩትን አሳዛኝ ይሁንታዎችን ሳላካትት ።

ያ ትውልድ – ሕዝባችን ማኅበራዊ ፍትኅ አጣ -ማለት (ዳኝነት ተጓደለበት ፣በድኅነት ተጎሳቆለ ፣በበሽታ ተጠቃ ፣በመኖርያ ቤት እጦት ምክንያት በረንዳ አዳሪዩ በዛ ፣ ትምህርት ለሰፊው ሕዝብ አልተዳረሰም ፣ ገበሬው አርሶ የሚኖርበት መሬት አላገኝም) ፣አገራችን ዘመኑ ከሚፈቅደው የዕድገት ጥበቦች ወደኋላ ቀርቷል ፣ የብሄር ብሄረሰቦች- (የቋንቋ ፣የባህል ፣የፖለቲካ፣ የልማድ ፣ የእምነት ወዘተ እሴቶች በእኩልነት አልተሰተናገዱም) -የእነዚህ ሁሉ ምክንያት የመልካም /የዲሞክራሲያዊ አስተዳደር እጦት ነው በማለት — በጎሳ ፣በቋንቋ ፣በባህ   ል፣በሃይማኖት በጾታ፣በርዕዮት ዓለም ፣በመደብ ፣በፖለቲካ ፣በጎጥ፣ በሞያ ወዘተ..ሳይከ ፋፈል – ለሁለገብ ለውጥ ታገለ ። የሃይለሥላሤ ፈላጭ ቆራጭ ንጉሣዊ እና የደርግ ፋሽስታዊ ሥርዓቶችን ለማስከበር/ለማስቀጠል ከሰለጠኑትን –ፖሊስዎች፣ ጸረ-ሕዝ ቦችና ነፍስ ገዳዮች ጋር ግብግብ ገጥሞ የሕይወት መሰዋዕት ከፍሎዋል(ያ ትውልድ) ። ያ ትውልድ  ከግለኝነት የነጻ (selfless) ትውልድ  ነበር ። ያ ትውልድ በአገሩ፣ በሕዝቡ ፣ በታሪኩ ፣ በማንነቱ ወዘተ..ኩራትና ፍቅር የታነጸ ትውልድ ነበረ። ያ ትውልድ ከአንድ እናት ማኅጸን የተወለዱ ወንድምና እህት ይመስል ነበር ።

አሁን በፀረ- ኢትዮጵያና በፀረ-የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነት መርሃግብር ተሰልፈው የሚገዙንን ቁንጮ የወያኔ/የኅወሃት ባንዳዎች የዚያ ትውልድ ትግል አጋር ነበሩ ለማለት የሚያስችል ጭብጥ ማስረጃ ባይኖረኝም ፤  አነስተኛ ፣መካከለኛና ከባድ ክብደት የነበራቸው  የትግራይ ተወላጆች ከያ ትውልድ ጋር ሁነው ታግለዋል ። ከባድ ክብደት ከነበራቸውና በቀንደኝነት ከያ ትውልድ ጋር ከታገሉት ውስጥ -ጥላሁን ግዛው ፣ብርሃነመስቀል ረዳ ፣ማርቆስ ሃጎስ ፣ ተስፋዬ ደበሳይ ፣ ግዴይ ዘራጽዮን ወዘተ..  ይገኙበታል ።

ባለፉት 25 ዓመታት የትግራይ ተወላጆች የያዙትን የፖለቲካ አቋም – ከላይ ከገለጽኳቸው ቀደምቶቻችንም ሆነ ከያ ትውልድ ታሪክና ገድል ፍጹም በተቃራኒዩ ስለመሆኑ –  ለእኛ ለኢትዮጵያውያን አንድ ሁለት ብሎ ማስረጃ ማቅረብ ባያስፈልግም ፤ እውነቱን ለሚክዱ –  የትግራይ ተውላጆች እጅግ በርካታ ከሆኑ ማስረጃዎች ጥቂቶችን እጠቁምላቸዋለሁ ፤ ከዚህ  በመቀጠል የምጦቁማቸው ማስረጃዎች በባዕዳን አገራት የሚኖሩ የትግራይ ተውላጆችን ይሁ  ንታ/ድርጊቶች እንጂ- በወያኔ የአፓርታይድ ሥርዓት ምክንያት ባገር ቤት ለ 25 ዓመታት ትግ  ራይ ባልሆኑ ኢትዮጵያውያን ላይ የተፈጸሙትን ሁለገብ ግፎችና ጥቃቶችን አያካትትም ። ይኸውም ፦

-ወያኔ/ህወሃት የኢትዮጵያ ሕዝብ ገዢ መሆን በጀመረ ማግሥት የትግራይ ተወላጆች በባ ዕዳን አገራት በኢትዮጵያዊነት ከተደራጁትን ማኅበሮች/ኮምኒቴዎች ተለይተው -ትግሬዎችን ብቻ ያቀፈ ኮምኒቲ/ዮች መመሥርት ጀመሩ/መሥርቷል

-በኢትዮጵያዊነት ተመሥርተው ኢትዮጵያውያንን በዕኩልነት ይገለገሉባቸው የነበሩትን  ቤተክርስቲናትና መስጊዶች  ለማዳከም  ፤ (1) ትግሬዎችን ብቻ ያቀፈ (2) ለወያኔ ያደሩ ሆዳም ኢትዮጵያ ውያንን ያቀፈ/ፉ ቤተክርስቲያናትና መስጊዶች ማደራጀት ጀመሩ/አድራጁ

– በቅድመ ወያኔ በኢትዮጵያዊነት -በጋራ ተሳትፎ እናከብራቸው የነበሩትን የዘመን መለወጫ፣  የገና ፣የፋሲካ ፣የኢድ አልጢር ፣የሮመዳን ወዘተ.. አውደ በዓሎቻችንና ወግ ማዕረጎቻችንን እኛና እነሱ በሚል በትግሬነትና በትግራይ ተወላልጅነት ስብስብ ብቻ ማክበር ጀመሩ

-እኔ በምኖርበት ከአውስትራሊያ ግዛቶች/ ስቴቶች አንዱ ዋና ከተማ 2500- 3000 ቁጥር ያላቸው የትግራይ ተወላጆች አሉ/ይኖራሉ ፤ ወያኔ ለ25ዓመታት በሕዝባችን ላይ እየፈጸመ ያለውን ግፍ ለማውገዝና የወያኔ ሉዑካን አውስትራሊያ በሚጎበኙበት ወቅት ባደረግናቸው የተቃውሞ ሰልፎች አንድ የትግራይ ተወላጅ ብቻ በተወስኑ ሰልፎች መተሳተፉን የተቃውሞ ሰልፍ አዘጋጆች አስተውሎዋል ።በሰው ቁስል እንጨት መስደት እንደሚባለው የትግራይ ተወላጆች እኛን በመቃወም – የወያኔ ግፎች ለማጽደቅና አበጅ  ለማለት ሰልፍ ይወጣሉ ። በተለያዩ አጋጣሚዮች ወያኔ አገራችንና ሕዝባችን ክፉኛ የጎዳና የበደለ መሆኑን ሲነገራቸው – ለመደባደብ ይቃጣሉ ፣ለምን ተደፈርን ብለው ይንጫጫሉ ፣ በወያኔ ላይ የሚነገረው ሁሉ ውሸት ነው (ትግሬ ስለገዛ) ነው በማለት ያዙኝ ልቀቁኝ ይላሉ ።

-ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን  ወክለው ወደ ተለያዩ አገሮች የሚላኩትን አምባሳደሮችና ሌሎች ልዕኳን  ከትግሬዎች ጋር ብቻ ነው የአገራችን ጉዳይ ተሰብስበው የሚየወያዩት- በቅርብ ጊዜ በቦስተን እንድተደረገው ዓይነት ፤ ይህ ሁሉ ሲሆን -በግል ፣በጥድም ይሁን በቡድን ልክ አይደለንም ፣አገባብ ያልሆነ  ድርጊት ነው የምንሰራው ብሎ – የተናገረ ፣ ድምጽ ያሰማ ፣ የጻፈ ወዘተ ትግሬ የለም

-እኛ ስናዝን እነሱ ይደሰታሉ ፣እኛ ስናለቅስ እነሱ ይስቃሉ

-በወያኔ የግፍና የሶቆቃ ሥራዓት አንገፍግፏቸው ራሳችውን (ስለሚሰቅሉትና ስለሚያቃጥሉት) ኢትዮጵያውያን ጉዳይ ሲነሳ -ጠግቦ/ጠግባ ነው በማለት ይሳለቃ ሉ፤ያሾፋሉ ።

የወጋ ቢረሳ የተወጋ አይረሳምና ድርጊቱን ያሳዘናቸው ኢትዮጵያውያን- ለምን እንደዚህ ያደርጋሉ? እንዴት ጎራ ለይተው  ይሰለፋሉ? ምክንያቱ ምን ይሆን? እያሉ-በነጠላም ፣ በጥንድም ፣በቡድንም  አዘወትረው  ከጠየቁና ከተወያዩ በኋላ – ትግሬዎች  ጎራ ለይተው የተሰለፉት በሚከተሉት ምክንያቶች እንደሆነ ሁሉም ይስማማሉ (እኔ በምኖርበት አካባቢ) ማለቴ ነው ።

  1. የአገራችንን የፖለቲካ ሥልጣን በእነሱ- ጠባብ ዘውግኞች እጅ በመውደቁ ፤

-የ90 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ሕዝብ – መብት ፣አእምሮ ፣አንድበት፣እጅና እግር መቆጣጠር በመቻላቸው

– ቤተሰባቸውም ሆነ እነሱ ወደ አገር ቤት ሲመለሱ- አዛዥ እንጂ ታዛዥ እንደማይሆኑ ስለሚያውቁ

– በኢትዮጵያ በሁለገብ የሥልጣን ተዋረድ-ዘመዶቻቸው በአንጻራዊ አዛዥነት ማዕረግ እንጂ በታዛዥነት እንደማይሰሩ ስለሚያውቁ

– የኢትዮጵያ የተፈጥሮና ዜጎቿ በላባቸው ያፈሩትን ሃብት(The wealth of a Nation <Ethiop>) በእነሱ ጎሳ እጅ በመውደቁ ፤ከአፍሪካ ሚሊየነሮች ቁንጮውን ቦታ የያዙት እነሱ በመሆናቸው

– ጭብጥ ቆሎ ተይዞ ወደ ምጣድ አሻሮ መጠጋት እንደሚባለው -ባደጉት ባዕዳን አገሮች በመሥራት ያገኙትን ገንዘብ ብቻ ሳይሆን- ለሥራ ፈትነትና ለጡረታ ከሚከፈላቸው የገቢምንጭ ያጠራቀሙትን  ይዘው ወደ አገር ቤት በመሄድ – ከወለድ ነጻ በሆነ ብድር ኅንጻዎች/ቪላዎች አሰርተው ወይም ገዝተው ማከራየት ስለቻሉና ስለሚችሉ

-ያለወለድ ከባንክ መበደር የሚያስችል የተለየ መብት ስለተሰጣቸው

-ያለቀረጥ አስመጪና ላኪ የመሆን መብት ስላላቸው

-በፖለቲካ ምክንያት በመንግሥት የሚፈለጉ በመሆናቸውን -የማስመሰያ (ፌክ) የማስጠንቀቂ  ያ ደብዳቤ አዘጋጅቶ በመስጠት ወደ ሥደደት ስለሚላኩ

-ያደጉ አገሮች በሞያም ሆነ ለንግድ ከድሃ አገሮች ወደ አገራቸው ለመውሰድ ያዘጋጁትን መሥፈርቶች (crieteria) የሚያሟሉ ሰነዶች አዘጋጅተው ስለሚሰጧቸው

-ለከፍተኛ ትምህርት ወደ አደጉ አገሮች ከሚላኩት 95% የትግራይ ተወላጆች በመሆናቸው   ወዘተርፈ

2.ቅኝ ገዢዮች በቅኝ ተገዢዮችን ለማስተዳደር የተጠቀሙበት -እኛና እነሱ ፣የበላይነትና የበታችነት፣የማምበርከክና የመምበርከክ  የፖለቲካ ሥራዓት/ ርዕዮት አስተምሮት ስለተሰጣቸው  (For being in doctorinated –  US v.s The other , Dominant  v.s  Subordninant- Political  system/Ideology ) .ከእነዚህም ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው

<> የአጼ የሖኒስና የራስ አሉላን ገድል ታሪክ ፣ የአክሱም ሐውልትና የአደዋን ድል ታሪካዊነትና ኩራት ፣ የትግራይ ሕዝብ ገድል፣ ባህል ፣ ቋንቋ ወዘተ..ለሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ምኑም አይደለም  ፤ ማለት የኢትጵያውያን  የገድል ፣የታሪክ ፣የባህል ፣የቋንቋ ፣የሰደቃዓላማ  ወዘተ.. እሴቶች ሁሉ – ከትግራይ ሕዝብ ጋር እንደማይዛመድ ወይም እንደማይገናኝ

<>  ያለፈው ምዕተ ዓመት ባማራ የበላይነት የኢትዮጵያ ቅኝ ተገዢ ነበርን ፤የሚቀጠለው መቶ ዓመት ሥርወ መንግሥቱ ለትግሬዎች ነው

<> “ከዚህ ከወርቃማ ትግሬ ዘር በመወለዴ እጅግ በጣም እኮራለሁ” መለስ ዜናዊ ። ያ ማለት ከትግራይ እናትና አባት የተወለደ ሁሉ ወርቃማ ነው ፤ኢትዮጵያውያን ‘ከብርና ከነሃስ’ የተፈ ጠሩ ስለሆኑ በትግሬዎች መገዛት ወይም በትግሬዎች ሥር መተዳደር ተፈጥሮአዊ ግዴታቸው ነው (by nature, Tigireans are the golden race , they are superior to all Ethiopian ethnics or all Ethiopian ethnics are inferior to Tigireans.Therefore,all the inferior Ethiopians should/must be governed by Tigireans)

<>  መሳርያ ብንሰጣቸውም ድፍረውም ሆነ ችለው ስለማይዋጉን አትሥጉ !

<> ህወሃት ከሌለ የኢትዮጵያ ፍጻሜ ማለት አርማጊዶን ስለሚሆን -ይህንን አደጋ/ሪስክ ወስዶ እኛን የሚዳፈር አይኖርም ፤ ከአሁን በኋላ ትግሬዎች እየተተካካን ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያ  ንን መግዛት ነው አይዟችሁ! ከሁለት ወር በፊት በአቶ አባይ ጸሃዬና ስዩም መስፍን ይህንኑ ሲደገሙት ተደምጧል ፤ እንድ ድሮ በተወጣጠረና በንድንፋታ ቃና ባይሆንም  የኢትዮጵያ ሕዝብ በህወሃት ካልተገዛ ከረዋንዳ የከፋ እልቂት ይገጥሞዋል፤ስለሆነም አትንኩን ዓይነት የማስፈራ ርያ ፕሮፓጋንዳ አስደምጧል ።

<> በጠመንጃ አፈሙዝ ማሸነፍና መሸነፍ የበጎ አድራጎት ኮንትራት አይደለም ፤ለማሸነፍም ሆነ ለመሸነፍ ዋጋ ያስከፍላል ፣ድሮ የቅኝ ተገዢያቸው  ነበርን፤አሁን አሸንፈን ቅኛችን አድርገናቸዋል ፤ እንደቅኝ ተገዢዮች ጸጥ ለጥ ብለው ይገዙልን ፤ የቅኞቻችን እሮሮ የሚስማ ጆሮም ሆነ የሚያዝን ኅሊና ሊኖረን አይገባም  ወዘተ… የሚሉ ናቸው ። ስለሆነም እነኚያ/እነ  ሱ በሚሉን ኢትጵያውያን ላይ -ንቀት ፣ጥላቻ ፣ ጭካኔ ፣ቂምና ትምክህት እንዲኖራቸው ተኮትኩቷል/ታንጿል ።

“Dogmatic ideologies remove doubt,but they have a major drawback.They are bound to be false.They can be imposed on society only by repressive methods that strifle free discussion and prevent a better understanding of reality.Such ideologies lead to a closed society….” (Andras Szanto :What George Orwell didn`t know). ቀኖናዊ ዕርዮቶች መጠራጠርን ያስወግዳሉ ፤ ግራና ቀኝ ሳይታይ -ጭፍን እርምጃ ለመውሰድ ይጠቅማሉ ፤በግድ/በጉልበት ሕዝብ ላይ ስለሚጫኑ- ሕዝብ ተወያይቶ እውነቱን እንዳያውቅ ይከለክላሉ ፤ ነገር ግን (lies have got short legs) የውሸት እግሮች  አጭር ናቸው እንደሚባለው -ዕድሜያቸው አጭር ነው ፤ የውሸት ተልዕኮዋቸው  ጠልፎ ይጥላቸዋል ። እንደ እነዚህ ዓይነት ዕርዮቶች – ‘ዝግ ማኅበረሰብ’ ማለት ከአዲስ እውቀት ፣ ከአዲስ አስተሳሰብ የተገደበና ኋላቀር አስተሳሰብ ያለው ማኅበረሰብ ይፈጥራሉ ።

“We usually remember George Orwell for the dangers he foretold about the effective use of propaganda,through which war becomes peace,torture becomes love ,ignorance becomes strength ,and despots and demagogues elevate  euphemism to a high art” (Drew Western)  in his ‘The New Frontier : The Instruments of Emotion topic’  in Andras Szanto). ጆርጅ ዎርዌል- ስለመጻኢ የረቀቀ  የፕሮፓጋንዳ አደገኛነት ‘የተነበየውን’ ሁሌ እናስታውሳለን ፤ ጦርነት እንደ ሰላም ፣ሰቆቃ እንደ ፍቅር ፣ድንቁርና እንደ ጥንካሬ ወዘተርፈ አድርጎ መስበክ የወደፊት ፕሮፓጋንዳ እንደሚሆኑ ፤  እንድ ለገሰ ዜናዊ ዓይነት – አምባገነኖችና አስመሣይ ሕዝባዊ መሪዮች (populist leaders) ወደ ሥልጣን ለመውጣትና ሥልጣናቸውን ለማራዘም (euphemism) ማለት በማር የተጠቀለለ ኮሶ ወይም መርዝ ባህሪ ባላቸው – ስሜት ቀስቃሽና ጣፋጭ ቃላ    ትና ሃረጎች ፣ ወደ ከፍተኛ ጥበብና ተወኔትነትን እንደሚያሳድጉ/አሳድገው እንደሚጠቀሙ ።  የትግራይ ተወላጆች ለንደዚህ ዓይነት ፕሮፓጋንዳ ተጋልጠዋል ፤በንደዚህ ዓይነት ፕሮፓጋንዳ  ተጠልፎዋል ።

3 የንቃተ-ኅሊና ዝቅተኝነት ፦ ፈጣን የመጓጓዣና የመገናኛ/ኢንፎርሜሽን ጥበብ ምክንያቶች – የዓለም ማኅበረስብ ድንበረየለሽ በሆነበት ፤ ብሄራዊ/አገራዊ ማኅበረሰብ ከዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ –  በእውቀት ፣ በንግድ ፣በምጣኔ ሃብት ፣ በጋብቻ ፣በማኅበራዊ ኑሮ ፣ በሃዘን ፣በደስታ ወዘተርፈ በተገናኘበት 21ኛው መቶ ክ/ዘመን ፤ ጨቅላ ግልገሎቿን (bunnies) አውሬዎች እንዳይበሉባት ጉድጓድ ውስጥ አስቀምጣ -ጉድጓዱን ጫፍ ላይ ሆና  ዘብ እንደምትጠብቅ  እናት ሚዳቆ ፤ በጎሳ ዙሪያ የመኮልኮል አስተሳሰብ (primordial thinking) ምክንያት ከንቃተ ኅሊና ማነስ የመነጨ ነው ። ትምኅርት ቤት በመሄድ ፣ በመማር ፣ በማንበ ብና በመጻፍ  ብቻ ‘ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ንቃተ ኅሊና’ አይሸመትም/ አይዳበርም ። የተለያየ ባህል ፣ ቋንቋ  ፣ልማድ ፣ ልምድ ፣እውቀት ፣እምነት ወዘተ..ካላቸው አገር በቀልና ባዕዳን- ግለስቦች ፣ ቡድን ፣ ኮምኒቲ/ማኅበረሰብ  ወዘተ.. ጋር አብሮ በመብላት ፣ በመጠጣት ፣በመ  ጫወት ፣በመወያየት ነው (through  interacting with people from divers  socio-cultural and socio-political background) ። በባዕዳን አገሮች የሚኖሩትም ሆነ አገር ቤት ያሉትን የትግራይ ተወላጆች – ከላይ እንደተገለጸችው እናት ሚዳቆ በጎሳቸው ዙርያ ብቻ ስለሚሽከረከሩ -ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ንቃታቸው ዝቅተኛ ነው ። ስለሆነም ቁንጮ ወያኔዎች እንደፈለጉ ያሽከረክሯቸዋል ፤ የሥልጣን ዘመናቸው ለማራዘምም ይጠቀሙባቸዋል ።

ከአገር ውጭ ያሉትም ሆነ የአገር ቤት የትግራይ ተውላጆች ላለፉት 25 ዓመታት ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ሕዝብ ተጻርረው ፤ የወያኔ የጸረ-ኢትዮጵያና የጸረ-ኢትዮጵያዊነት መርሃግብር ወግነውና ደግፈው የተሰለፉት – ከሞላ ጎደል ከዚህ በላይ በተጠቀሱት ምክንያቶች ነው ይላሉ – በአካባቢዬ በዚህ ጉዳይ/ነጥብ ዙርያ የሚወያዩ ኢትዮጵያውያን ። እኔ ጻፍልኝ ያሉኝን ጻፍኩ እንጂ እይታውና ግምገማው የእነሱ ነው ።

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.