በ 7 ወታደሮች ተከቦ ተመሰገንን በዝዋይ እስር ቤት አግኝተነዋል

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

ተመስገንን አግኝተነዋል
ከ 10 ቀናት በኃላ ከ30 ደቂቃ በፊት ለ 3 ደቂቃ በዝዋይ እስር ቤት በልዩ ጥበቃ ለብቻው በ 7 ወታደሮች ተከቦ ተመሰገንን አግኝተነዋል። ተመስገንን ሰናገኝው ምን ማውራት ባንችልም ሲራመድ እንደሚያሰቸግረው አይተናል። እሱም ከሌሎቹ ህመሙ ውጪ ጨጓራው እጅጉን መታመሙን ነግሮናል።

እስካሁን የት እንደነበረ ምን እንዳረጉት በንጠይቅም ወታደሮቹ መመለስም መጠየቅም ከልክለውናል። ተመሰገንን ከበው ካመጡት ወታደሮች መካከል ሀላፊያቸውን እስካሁን ለምን እዚህ እንዳለ አልነገራቹህንም ስንለው ተመስገን እዚህ ያገኘነው ዛሬ ነው ብሎናል። የሆነው ሆኖ ተመሰገንን አግኝተነዋል። ተመስገንን አጣነው ካልንበት ግዜ አንስቶ ከጎናችን መሆናቹህን ላሳያቹሁን ሁሉ እጅግ በጣም እናመሰግናለን።

Tariku Desalegn

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.