የኢፈርት አላማዎች ሰዎስት ናቸው! – ናትናኤል አስመላሽ

1.ለትግራይን ህዝብ ስራ በመፍጠር ሽፋን ህውሓትን እንዳይቃወም ማድረግ.
2.የህውሓት ባለስልጣናት እና ቤተሰቦቻቸውን በሃብት ማበልጸግ.
3.ኢትዮጲያ/ትግራይ ውስጥ ተወዳዳሪ ድርጅት እንዳይኖር ማድረግ ብሎም ኢትዮጲያ መዝረፍ.

ኢፈርት ትግራይ ውስጥ ባቋቋማቸው ድርጅቶች ስራ ቢፈጥርም በነበረው ረጅም እቅድ ትግራይ ውስጥ ሊከሰት ለሚችል ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ጥያቄ እንዳይነሳ ረድቶታል፣ግቡ ሙሉ በሙሉ ተሳክቶለታል። ኢፈርት ውስጥ ተቀጥረው ከሚሰሩ ከሰላሳ ሺ በላይ ሰራተኞች ህውሓትን መቃወም ሆነ መተቸት አይችሉም፣ ይህንን ያደረገ ሰራተኛ በኢፈርት ህግ መሰረት ከስራ ይባረራል። ስለሆነም የኢፈርት ዋና ግቡ የትግራይን ህዝብ በተዘዋዋሪ መንገድ የህውሓት ወይም የኢፈርት ፍጹም ተገዢ (ባርያ) ማድረግ ነው።እኛ እናውቅልሃለን የሚሉ የህውሓት ባለስልጣናት የኢፈርት ገንዘብ በስማቸው አሜሪካ እና አውሮፓ አስቀምጠዋል። ይህ ሳያንስ የተቀመጠው ገንዘብ ለልጆቻቸው እና ሚስቶቻቸው ማስተላለፋቸው ነው። በአምባሳደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ ስም የተቀመጠ አስር ሚልዮን ዶላር ከሚስቱ ጋር ባጋጠመው ፍቺ የኢፈርት ወይንም በነሱ አባባል የትግራይ ህዝብ ገንዘብ ለሚስቱ ገቢ እንዲሆን ተደርገዋል። በኢፈርት ገንዘብ ጥሩ ኑሮ የሚኖሩ የህውሓት ባለስልጣናት እና ቤተሰቦቻቸው እንጂ የትግራይን ህዝብ ኣለመሆኑ በቂ ማስረጃ ነው፣ ይህንንም ለታሪ በገብሩ አስራት እና በኤርምያስ ለገሰ መጽሃፎች ተቀመጠዋል። ጊዜው ሲደርስ የትግራይ ህዝብ እነዚህ ነብሰ በሊታዎች መፋረዱ አይቀርም።ኢፈርት ኢትዮጲያ ውስጥ ብቸኛ ተወዳዳሪ ድርጅት ነው። ኢፈርት እንደ ሌሎች የግል ኩባን ያዎች ግብር የማይከፍል በመሆኑ በኢፈርት አጠራር ልማታዊ ነጋዴዎች ከጨዋታ ውጭ አድርገዋል። ከውጭ በሚያስገባቸው እቃዎች በሙሉ ቀረጥ ከፍሎ አያቅም። በሃገሪቱ ለሚደረጉ ግዙፍ ልማቶች ያለጨረታ ይረከባል፣ ባለፈቱ ሃያ አመታታ አንድም ቀን ኦዲት ተደርጎ የማያውቀው ኢፈርት የሙስና ሜዳም ጭምር ነው። ስራው በውል መሰረት ያጠናቀቀ አንድም የኢፈርት ካምፓኒ የለም። እነ ሱር ኮንስትራክሽ ትግራይ ውስጥ ያለጨረታ ያለተወዳዳሪ የወሰዱዋቸው ግምባታዎች ከታቀደላቸው ቀን አራት እና አምስት አመት ጠብቀው ያልቃሉ ለዛው ያለ ጥራት። የኢፈርት ዘረፋ እና ሙስና ብሎም የህውሓት ባለስልጣናት እና ቤተሰቦቻቸው የሃብት መጠን ለማየት የኤርሚያስ ለገሰ መጽሃፍን ማንበብ ጠቃሚ ነው።

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.