አቶ አየልኝ ሙሉዓለም ለአመታት የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ የነበሩት ከባድ ተልዕኮ ይዘዉ ወደ ሰሜን ጎንደር ዞን የዋና አስተዳዳሪነት ቦታ ተላኩ

ቆንጅት ስጦታው
 
ከ100 ዓመት በፊት ፋሺስቶች ለቅኝ ግዛት እና ባሪያ ንግድ ሲጠቀሙበት የነበረዉ የከፋፍለህ ግዛዉን መርህ ዛሬም የትግሬዉ ህዉሃት ስትራቴጂ አድርጎ እያጫረሰን ይገኛል፡፡
አቶ አየልኝ ሙሉዓለም ትዉልዱ ከጀግናዉ አገር ከዳባት ቢሆንም ተልዕኮዉ እና ሃሳቡ ግን ፀረ-ዳባት እና ፀረ-ህዝብ ከሆነዉ የትግሬ ቡድን ጋር በመሰለፍ ዳባትን እና መሰል የጎንደር እና የአማራ ህዝቦቹን መጨረስ ነዉ፡፡

ሰሞኑን ትግሬ ወያኔ እና ወታደሮቹ የዳባት እና ወገራ ጀግኖቹን መዋጋት ሲያቅታቸዉ እና በየስርቻዉ ተደፍተዉ ሲወድቁላቸዉ ወያኔ አንድ ሴራ ጠነሰ፤ የዳባት እና ወገራ ጀግኖቹን ተዋግቶ ማሸነፍ ሲያቅተዉ ቤታቸዉን ከተራራዉ ላይ በመሆን በአብሪ ጥይት በመምታት መቱን ተያይዘዉ ያሉትን የሳር ቤቶች በሙሉ አጋያቸዉ፡፡ ከዉስጥ የሚገኙትን ሴት እና ህፃነት አዛዉንት እና ሩጠዉ ማምለጥ የማይችሉ አቅመደካሞች ሳይቀሩ በእሳት ለበለባቸዉ፡፡

የዚህ ግፈኛ መንግስት ክፉ ስራ በዚህ አይመለስም ይልቁንስ ስራዉ አማራን ከዚህ ምድር ማጥፋት ነዉና አመቱን ሙሉ ሲለፋበት የከረመዉን እና ለቀጣይ የአመት ቀለብ ይሆነኛል፣ልጆቼን አሳድግበታለሁ፣ዝክር እዘክርበታለሁ፣እንግዳም እሸኝበታለሁ ያለዉን አዝመራዉን በየአዉድማዉ ከርቀት በአብሪ ጥይትና በመትረየስ እያነደደ የዚህን ምስኪን አርሶ አደር የእህል ክምር ወደ አመድነት ቀየረዉ፡፡

እግዚአብሄር ያሳያችሁ ድሮ እኛ የምናዉቀዉ ወታደር አገርን፣ ዳር ድንበርን፣ሉዓላዊነትን ሲጠብቅ ነበር፣ እኛ የምናዉቀዉ በታሪክም የሰማነዉ እንደ ትግሬ ወያኔ በቴሌቪዥን እና ራዲዮ ልማታዊ ነኝ አርሶ አደሩን ዋስትና እሆነዋለሁ እያለ አ/አደሩን የሚያሳድድ እና አዝመራዉን እና ቤቱን ዶግ አመድ የሚያደረግ ሳይሆን ሁላችንም ከታሪክ

የተማርነዉ፣ካለፉት መንግስታትም ያየነዉ የጣሊያንን፣የግብፅን፣የሱዳንን፣የሱማሌን ወራሪ ዶግ አመድ ሲያደርጉ ነበር፣አ/አደሩንም በጥይት ሳይሆን በፍቅር ሲመሩት ነበር እርስ በርስ በመከፋፈል ሳይሆን በመፈቃቀር እና እኩል በመጥቀም ነበር፡፡ ግን ምን ያደርጋል ጊዜ የሰጠዉ ቅል ሆነነና ከትግሬ አብራክ የወጣ ሳይጣን አገሪቱን በጥብጦ መኖሩ ሳያንሰዉ አሁንም በጅምላ ይጨርሳል፣ . . . የአማራ ልዩ ኃይል፣መከላከያ፣ፖሊስና ደህንነት፣አንተ አማራን ዘሩን የምታስጨርስ፣ደሙን የምታፈስ ካድሬ እና ካቢኔ ከቀበሌ እስከ ፌደራል ተዉ ወገንህን አታስጨርስ፣ተዉ የመረረዉ ህዝብ ነገ አንተን ከነቤተሰብህ ይዉጥሃል፣ተዉ እንደ ንብ ገንፍሎ ሊወጣ ነዉ፣ተዉ መተላለቅ ሊመጣ ነዉ፣ተዉ ፊትህን መልስ፣ተዉ ጠብመንጃህን አሁን አዙር፣ተዉ ወያኔ በየተራ ይጎበኝሃል፣ተዉ ይሄ ባንዳ መንግስት 25 አመት ለታገሉት ለነ ኮ/ል ደመቀ፣ ለነ 100 አለቃ ደጀኔ፣ ለነ ኮማንደር ዋኘዉ፣ ለነ ሜጀር ጄኔራል ሃየሎም አርያ ያልሆነ እንኳንስ ለአንተ፡፡ እንግዲህ ቀኗ ደርሳለች፣ አስተዋይ የሆነ ወደ ህዝቡ ወደወገኑ ይጠጋ፣ማዕበሉን የሚችል አይኖርም፡፡ በጣም የሚያሳዝነዉ የአማራን ልዩ ሃይል፣ወታደር እና አመራር በአማራ ህዝብ ለማስጨረስ፣እርስ በርሱ ለማስተላለቅ ትግሬ ወያኔ ከጫፉ ላይ ደርሷል፡፡ ዛሬ የምትገድለዉ፣የምታስረዉ እና የምታሳድደዉ ህዝብ ነገም አንተን ይበላሃል፡፡ ያኔ ትግሬ ከሀገሪቱ የዘረፈዉን እና ያካበተዉን ሃብት ይህን ፊልም እያየ ይበላል፡፡ ወዮልን የአንተን እና የእኔን መጠጊያ፡፡
እንግዲህ በስሜት እና በቁጭት ይህንን ሁሉ ፃፍኩ እንጅ በመነሻየ የጀመርኩትን ጉድ ልቋጨዉ፡፡የከፋፍለህ ጨርስ የትግሬ ወያኔ ስትራቴጂ አማራን አሁንም ለማስጨረስ እየተጋ ነዉ፡፡ አቶ አይልኝን ከክልል ጤና ቢሮ ባንዳዉን እዘዝን ከደ/ታቦር አስተዳዳሪነት በማምጣት 20 የገጠር ወረዳ እና 6 የከተማ መስተዳድር ወረዳ ያለዉን ትልቅ የአንድነት እና የፍቅር የጎንደሬነት ስሜት ያለዉን ህዝብ እምቢ ለትግሬ ወያኔ አንገዛም ያለዉን ህዝብ አከፋፍሎ እርስ በርሱ ለማባላት ከትግሬ ወያኔ የተጠነሰሰዉን ሴራ ለማስፈፀም ከላይ የጠቀስኳቸዉ 2ቱ ባንዳዎች ተልዕኮ ተሰጥቷቸዋል፡፡

ከዚህ በፊት ቅማንትን ከአማራ በመገንጠል ከአማራዉ ጋር በፍቅር ሳይሆን በጥርጣሬ እንዲተያዩ እና አንድ ላይ እንዳይቆሙ፣አማራዉ ወያኔን ለመዋጋት ሲነሳ ቅማንትን ትግሬዉ ከጎኑ በማሰለፍ የአማራን ኃይል ለማድከም የታሰበዉ ስትራቴጂ እንዳዋጣዉ እና ዛሬወም ቅማንቱ ከአማራ ጋር ሆድና ጀርባ እንዲሆን ብዙ ደክሞ፣ብዙ ለፍቶ እንደተዋጣላት ሁሉ (ከዚህ ላይ ለቅማንት ነባር ወገኖቻችን ብዙ ማለት የሚቻል ቢሆንም ለጊዜዉ በአጭሩ ማለት የምፈልገዉ ከትግሬ አማራ መቼም ቢሆን እንደሚሻልህ እና ነገ ትግሬ ወያኔ እንደሸንኮር አገዳ መጦ እንደሚታፍህ ይችን ቃልም እንዳትረሳት ለአማራ እንደነ ደመቀ መኮነን እና ካሳ ተክለ ብራሃን፣በረከት ስሞን . . . የመሰሉትን የእግር እሳት እንዳስቀመጠለት ለአንትም ስራዉን ሲጨርስ 3 ሆዳም ቅማንት ያስቀምጥና እርስ በርስህ እንደሚያባላህ አትርሳ ፡፡ እንግዲህ ወያኔ ለሰሜኑ ጀግናዉ አማራ ሰሞኑን ይዞት የመጣዉ ተልዕኮ ጎንደርን ከ3 ዞን በመከፋፈል አንደኛዉን መተማ፣2ኛዉን ደባርቅ፣3ኛዉን ጎንደር ከተማ በማድረግ እርስ በርስ እንዲጣሉ እንዲከፋፈሉ እና እንዲጨራረሱ አጀንዳቸዉን ከትግሬ ወያኔ ጋር ሳይሆን እርስ በርስ ደባርቅ ከዳባት፣መተማ ከቋራ፣አርማጭሆ ከቅማንት . . . እንዲፋጅ እና ሃሳቡን በማስቀልበስ ቅማንትን ከትግሬ ጎን በማሰለፍ የአማራን አከርካሪ ለመስበር ዝግጅቱ አልቋል፡፡

ይህንን ጨዋታ እንዲጫወቱ እና ተመልሰዉ ሌላ ኃላፊነት ለመስጠት የታሰቡት 2 ዋና ዋና ሆዳሞች ሲሆኑ የተሸለ ተቆቋሪነት ያላቸዉን አማራዎች በጥልቅ ተሃድሶ በሚል መንፈስ አሸቀንጥሮ ጥሏቸዋል፡፡
እንግዲህ ይህ ጉድ የት እንደሚያደርሰን ለሁላችንም ግልፅ ነዉ፡፡
ከዚህ እልቂት ለመዳን ሁላችንም ኃላፊነት አለብን፡፡

ነገ ዛሬ ሳንል ልባቸዉ የደነደነ በአማራ ህዝብ ስም የሚነግዱ ደም አፍሳሾችን በጋራ፣ በአንድነት እንታገል፣ከነ ጎቤ፣ከነ መሳፍንት፣ከነ 100 አለቃ ደጀኔ፣ከነ ኮሎኔል ደመቀ ዘዉዴ፣ከነ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ ተመስገን ደሳለኝ፣ . . .በ20 ሺ ከሚቆጠሩ በእስር ላይ እና እና በሺ ከሚቆጠሩ በርሃ ከገቡ ቆራጥ የአማራ ጀግኖች ጋር እንሰለፍ . . .ጊዜዉ አሁን ነዉ፡፡
እግዚዓብሄር የዚህን ጭራቅ መንግስት እና ምስለኔዎቹን ሞት በቅርቡ ያሳየን፡፡
ድል ለጭቁኖች እና ለተገፋዉ ህዝብ፡፡

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.