ሰበር ዜና፡- በአርበኛ ጎቤ መልኬ የሚመራው የአማራ ህዝባዊ ሃይል ዛሬም በድጋሜ ድል ተቀዳጀ!

አርብ ታህሳስ 14 ቀን 2009
በትናንትናው ውጊያ የተቀጠቀጠው የወያኔ መንጋ ዛሬም ያለ የሌለ ሃይላቸውን አጠናክረው ጀግናው ጎቤ በሚመራው ህዝባዊ ወገን ላይ ጥቃት ቢሰነዝሩም አይቀጡ ቅጣት ተቀጥተው ተመልሰዋል። ድል በድል የሆነው ጎቤ ከነሰራዊቱ በጥሩ ሁኔታ ላይ መሆናቸው ታውቋል።
በዛሬው እለት ከሁመራ የተነሱ በ6 መኪና የሞሉ የወያኔ ወታደር ወደመተማ አቅጣጫ እያመሩ ነው። ስናር ላይ መድረሳቸው ታውቋልና በመተማ ቋራና አካባቢው ጥንቃቄ እንዲደረግ መልእክት ይተላለፍ።
ጎንደር ላይ በየአቅጣጫው የተወጠረው ወያኔ ያለ እረፍት የወታደር እንቅስቃሴ እያደረገ ነው። የመኸር ስራውን በጥድፊያ የተያያዘውን ገበሬ እጅግ የፈራው ወያኔ የተደገሰለትን ለማደናቀፍ ሲል አስቀድሞ በየቦታው ጦርነት እያስነሳ ይገኛል። ወያኔ የፈራውን እንደማያመልጠው ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉት በሙሉ ልብ ይናገራሉ።

News update from Gonder
The victorious peasant rebellion in Gonder, northern province of Ethiopia, lead by the towering figure in the name of Gobe scored a significant gain against the TPLF brutal regime for the second day in a raw. This area have been under heavy military activity for the last six months. The popular uprising is the result of the 25 years of repression by the Tigray minority regime. This popular movement flags the claim of Wolqait as a land taken away from Gonder by TPLF and the people denied of their Amhara identity.
#Muluneh_Yohannes @ Amhara Ppl

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.