ከዳላስ የኢትዮጵያ ጉዳዮች ውይይት መድረክ የቀረበ ጥሬ

New Year Resolution

ይድረስ ለመላው ዲያስፖራ ባላችሁበት፤ በአሜሪካ፤ በአውሮፓ፤ በአውስትራሊያ፤ በኤሽያ፤          ባፍሪካና፤ በመካከለኛው ምስራቅ የምትገኙ በሙሉ። እንኩዋን ለኢትዮጵያ ገና በአልና ለፈረንጆቹ አዲስ ዓመት አደረሳችሁ በማለት እኛ በዳላስ የምንገኝ የዳላስ የኢትዮጵያ ጉዳዮች ውይይት መድረክ ( Forum ) ልባዊ ሰላምታችንን እናቀርባልን።

ይህ የዳላስ መወያያ መድረክ ( Forum ) አጠር ያለ መለክት ይዘንላችሁ ስንቀርብ በጥሞና እንድታዳምጡን በትህትና ከወዲሁ እንጠይቃለን። ወገኖች ሁላችሁም እንደምታውቁት ዛሬ አገራችን በመንታ መንገድ ላይ እንደምትገኝ ለናንተ መንገሩ አስፈላጊ አይመስለንም፤ የወያኔ ዘረኛው የወንበዴ ቡድን አገዛዝ የሕዝባችንን ሰቆቃ እያጠነከረ በግፍ ያለምንም ርህራሄ በተለያየ ወጣቱን ትውልድ እያሳደደ በማሰር፤ በመግደልና ለስደት በመዳረግ ላይ ይገኛል፤ ሕዝባዊ እንቢተኝነቱም የዚያኑ ያህል ተጠናክሮ ይህን የዘረኛ ቡድን መተንፈሻ እንዳሳጣው የማይካድ ሓቅ ነው። በተለያዩ አካባቢዎች ጀግና የኢትዮጵያ ልጆች በጎበዝ አለቃቸው እየተመሩ በአማራው ክልል የወያኔን ቡችሎች መውጫ መግቢያ እያሳጡዋቸው ነው። በውጭውም አለም ያለው ዲያስፖራም በተለያየ መልኩ፤ ሰላማዌ ሰልፍ በመውጣት ዲፕሎማሳዌ ውጥረቶችን በመፍጠርና ፒትሽን በማስፈርም ለተባበሩት መንግስትና ለሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎችና ለተመሳሰሉ ድርጅቶች አቤቱታውን በማሰማት የወያኔን መንግስት እይተፋለም ነው።

ወያኔ ዛሬ አንድ ሐሙስ የቀረው የውንበዴ ጥርቅም በመሆኑ  የዚህን ዘረኛ መንግስት እድሜና ትንፋሽ ለማሳጠር ሁሉም በአንድነት ቆሞ በሁሉም ዓይነት ሁለገብ ትግል በማድረግ እድሜውን ማሳጠር ግድ ይላል።

ይህንኑ መሰርት በማድረግ የዳላስ ኢትዮጵያውያን የውይይት መድረክ ተወያይቶ የደረስበት ውሳኔ የዲያስፖራው ሕብረተሰብ ይጠቀምበታል ብለን ስለአሰብን ይህንን ቀላልና ለአንድ ጊዜ ብቻ ( ካስፈለገም ይቀጥላል ) በመጠቀም ወያኔ የሚስገበግበትን የውጭ ምንዛሬ ለአንድ ወር በማስቀረት ዋለቱ እንዲሳሳ ለማድረግ ያቅድነውን ዘመቻ እንድትካፈሉ እንጠይቃለን። ወገኖች ትግሉን በሁሉ አቅጣጫ ማጋጋል ስለሆነና የትግል ትንሽ ስለሌለ በንቀት የማይታለፍም ስለማይሆን ባለን አቅም ሁሉ ጠጠር በመወርወር ወያኔን ማቁሰል መቻል አለብን ይሄን መተግበሩ ደግሞ ማንኛውም ኢትዮጵያንና ወገኑን የሚወድ ኢትዮጵያዌ ግዴታ ነው።

እስከዛሬ ተሞከሮ አያውቅም ባንልም ትኩረት ያልትሰጠበትና በተግባር ላይ ያልዋለ የትግል ስልት እንደቀላል የተወስደ ቢኖር አንዱ የወያኔን የውጭ ምንዛሬ ማዳከም ነው፤ ወያኔ በየዓመቱ ከዲያስፖራው ብቻ ከአንድ ቢሊዬን ዶላር በላይ ( Billion ) እንደሚያገኝ የታወቀ ነው። ለዚህ መፍቴ ይሆናል ብለን የገመትነው ደግሞ በዚህ በአመት በዓል ወቅት እያንዳንዱ ዲያስፖራ ለዘመዶቹ የሚሆን ገንዘብ እንድምንልክ የታወቀ ሲሆን ይህም ገንዘብ በዶላር ተመንዝሮ ወያኔ ኪስ ይገብባል። በተጨማሪም የወገኖቻችን መግደያና የዘር ማጥፊይ መሳሪያ ታንክና ጥይት መግዣ ላይ ያውሉታል ይህ እየታወቀ ሰራችንን ባለመስራታችን ወያኔዎቹ ከጥይት መግዣ የተረፋቸውን ተከፋፍለው የኢትዮጵያ ሕዝብ በረሃብ ሲያልቅ እነሱ ግን በየአውሮፓው መንደላቀቂያ አድርገውታል።

ታዲይ እንደዚህም ሰንል በዚያች ደሃ አገር የሚኖሩትን ወግኖቻችንን ችግርና ረሃብ ረስተን ሳይሆን ድር ቢያብር አንበሳ ያሰር እንደሚባለው ሁሉ ለሁልጊዚ ሳይሆን ለአንድ ጊዜ ለአንድ ወር ብቻ ብናቆም ወያኔን በትንሹም ቢሆን ማቁሰሉ አይቀሬ ነው። ሌላው መታወስ ያለበት ጨርሶም አትላኩ ማለታችንም ሳይሆን በዌስተር ዩኒየን፤ መኒ ግራም፤ ባንክ ድራፍት ( western union, money gram, bank draft ) በመሳሰሉት አትላኩ ማለታችን ነው፤ ምክንያቱም ይህ ገንዘብ በቀጥታ ወያኔ ባንክ ወስጥ ገቢ ስለሚሆን ነው። በሌላ መንገድ ግን በማንኛውም ማድረስ ትችላላችሁ።

ስለዚህ የዳላስ ኢትዮጵያውያን መወያያ መድረክ ፎረም ይህንን ሃሳባችንን የአመቱ መጫረሻ የሚቀጥለው አመት መቀበያ ሪዞሉሽን ( Resolution ) እንድታደርጉልን በትህትና እንጠይቃልን   

በድጋሜ ይህ ጉዳይ በአገር ቤት ወስጥ በየአቅጣጫው ከወያኔ ጋር ለሚዋደቁ ጀግና የጎበዝ አልቆችና በጦር ግንባር የሚፋለሙ አርበኞቻችንን በምንም አይነት መልኩ አይምለከትም ለነሱ ከዚህ በፊት በሚደረገው መንገድ ሁሉ እንዲቀጥል አደራ እንላለን

ድል ለ ኢትዮጵያ ሕዝብ ሞት ለ ወያኔ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.