ከወያኔ ደህንነት ቢሮ ተገኘ የተባለው መረጃ …..:- ህዝባችንን ለመቀጥቀጥ የሚደረግ የቅድመ ተጠይቅ መደላድል ? – ሸንቁጥ አየለ

ከወያኔ የደህንነት ቢሮ የተገኘ መረጃ ተብሎ እየተሰራጨ ያለዉ መረጃ ሆን ተብሎ
በወያኔ ተቀናብሮ ወደ ተቃዋሚዉ ጎራ የተላከ መረጃ ይመስላል::መረጃ ተብሎ የተሰራጨዉ ነገር እንደሚያትተዉ ወያኔ በዉጭ ያለዉን ትግል ማዳከም የቻለዉ በዉጭ ያሉትን ተቃዋሚዎች በራሱ ተላላኪዎች አማካይነት መከፋፈል በመቻሉ ነዉ:: በሁለተኛ ደረጃም ይሄዉ መረጃ የተባለዉ ነገር እንደሚያብራራዉ በሀገሪቱ መንግስት ሊቆጣጠረዉ የማይችል ከፍተኛ የህዝብ ተቃዉሞ ይነሳል::

እናም የማህበራዊ ሚዲያዉ እና ልዩ ልዩ የተቃዋሚ ሚዲያዎች እንደ ትልቅ ነገር መረጃዉን እያሰራጩት ነዉ::

ሆኖም እንዲህ አይነት መረጃዎች ከብዙ አንጽር መተንተን አለባቸዉ:: መረጃዉ እንደሚመስለኝ ሆን ተብሎ ወያኔ ለማወናበጃነት የለቀቀዉ መረጃ ነዉ:: ልክ አፈትልኮ የወጣ መረጃ እንዲመስል ተደርጎ ወደ ተቃዋሚዎች መንደር የተላከ መረጃ ይመስለኛል::

አንደኛ የዉጭዉን ማህበረሰብ ለመከፋፈል እና አብሮ እንዳይቆም ለማድረግ:: ወይም የዉጭዉን ተቃዋሚ እኔ ነኝ የከፋፈልኩት ለማለት እና ይበልጥ በዉጭዉ ተቃዋሚ መሃከል መተማመን እንዳይኖር ለማድረግ ነዉ:: ሁለተኛም የጀመረዉን የኮማንድ ፖስት አካሄድ አጠናክሮ ለመቀጠል እና ህዝቡን ለመቀጥቀጥ::ከፍተኛ ተቃዉሞ ይነሳል::ስለዚህ ሀገሪቱን በወታደራዊ እዝ ስር አድርጌ ህዝቡን እየቀተቀጥኩ ያለሁት መንግስት ሊቆጣጠረዉ የማይችል ተቃዉሞ ሊነሳ መሆኑን ስለደረስኩበት ነዉ እያለ የራሱን ተጠይቅ ለመደርደር ነዉ::

ህዝባችንን ለመቀጥቀጥ የሚደረግ የቅድመ ተጠይቅ መደላድል ወያኔ እየሰራ መሆኑን በደንብ ማጤን ይገባል::

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.