ምላሻችሁ ይህ ነውን? – ከበላይ አበራ

የኢህአዴግ መንግስት በዓለም ደረጃ ከሩብ ምዕተ-ዓመት በላይ በስልጣን ላይ ከቆዩ ጥቂት መንግስታት አንዱ ነው፡፡ አሁንም በስልጣን ላይ ያለው አይጠግቤው ኢህአዴግ በስልጣን ዘመኑ ብዙ ውጣ ውረዶችን አሳልፏል፡፡ እያሳለፈም ይገኛል፡፡ በፍትሃዊ ምርጫ አንድ ጊዜም ያላሸነፈው ኢህአዴግ በሀገሪቱ ከተደረጉ 4 ብሄራዊ ምርጫዎች ሽንፈት ቢከናነብም አሻፈረኝ በማለት የምርጫ ኮሮጆዎችን በመመዝበር የምርጫውን ውጤት ቀይሮ አሸናፊ ነኝ በማለት የቅሌት አባወራ መሆኑን አሳይቷል፡፡ በእርግጥ በስልጣን ረጅም ዘመን ለመቆየት እንዲህ ዓይነት ሰንኳላ ተግባር የሚጠበቅ ነው፡፡

ከ2007 ዓ.ም ጀመሮ በተነሳው ሀገር-ዓቀፍ ተቃውሞ ከ2’000 በላይ ንፁሀን መሞታቸውና ብዙ ንብረቶች መውደማቸው ይታወቃል፡፡ ምስኪኗ ሀገራቸን መልሳ የማትተካው የህዝብ ክፍልና ፋብሪካዎች መክነውባታል፡፡ መንግስት ለተነሳው ተቃውሞ ግራ በመጋባቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በሚባል የህመም ማስታገሻ የተቃውሞው ቀሳውስት የሚላቸውን አድኖ በመያዝ፣ በማሰር፣ በመደብደብና በመግደል ተቃውሞውን ለማዳፈን ጥሯል፡፡ ይሁን እንጂ ውስጥ ውስጡን የህዝብ ብሳት ህዋ በመድረሱ አዳዲስ ተቃውሞዎች ፈንጥቀው መውጣታቸው አይቀሬ ይመስላል፡፡

የህዝብ ተቃውሞ በቅጡ አጢኖ ምላሽ ሲጠበቅበት የከፍተኛ ባለስልጣናት እርባናቢስ ሹም ሽረት በማድረግ ሁለተኛ ተቃውሞ የሚያስነሳ ተግባር ፈፅሟል፡፡ ህዝቡ የጠየቀው ከ25 ዓመታት በላይ በስልጣን ላይ በቆየበት ወቅት በፍትሃዊ አስተዳደር ችግር ስለተማረረ ከስልጣን ውረዱ ሲሆን ኢህአዴግ ደግሞ በለመደው እቃቃ ጫወታ ውስን ባለስልጣናትን ከስልጣን በማውረድ ህዝቡን በአግባቡ አላስተናገዱም ማለት ነበር፡፡ የግለሰቦች መለዋወጥ ምንም እንደማይፈይድ ህዝቡ ቢያውቅም ኢህአዴግ እከከኝ ልከክህ በሚል የፈዝ ጫወታ ለመሸፋፈን ሞክሯል፡፡

ሁለተኛው ደግሞ በየክልሉ፣ ዞኑና ወረዳዎች የአካባቢያችሁ ልጆች ናቸው የተሾሙት ከበደሏችሁ የራሳችሁ የአካባቢ አመራሮች ናቸው መንግስት አይደለም በማለት ከንቱ ማስተባበያ ማቅረቡ ይታወቃል፡፡ በእርግጥ በየአካባቢው የሚሾሙት የአካባቢው ልጆች ናቸው፡፡ ይሄንም ማንም አይክድም፡፡ ነገር ግን በዚህ ወረበላ መንግስት የትኛው አመራር ነው በነፃነት የፈቀደውን የሚያደርግ????? እስቲ ንገሩኝ??? አመራሮች የሚያወጡት ብስናና የሚፈሱት ፈስ ሳይቀር በሕዋሓት ፍቃድ ሆኖ ሳለ መልሰው እኛ አይደለንም የበደሏችሁ የራሳቸሁ አመራሮች ናቸው የሚሉት???

አንድ የእስፔኖች አባባል አለ፡፡ በብርጭቆ ውስጥ የሚገኝ ነጭ ፈሳሽ ወተት ነው፡፡ የኢህአዴግ መንግስት እስከ መጨረሻው የስልጣን እርከን በሕዋሓት ፍቃድ መሆኑ እየታወቀ ለማላዘን ሌላ ምክንያት መፈለግ ምን አመጣው??? አንድ አካባቢ ተቃውሞ ተበራክቷል ሲባል ትንሽ ልማት ይሰራና ተቃውሞ ለማብረድ የሚሞክረው እራሱ አይደል? የአመራር መልማይስ እራሱ አይደልም? አስተዳደራዊ ጥያቆዎቸን ለፖለቲካው ሲል ሲፈልግ የሚመልሰው ሳይፈልግ የሚተወው እራሱ አይደል??? ከስልጣን አመራሮችን የሚያወርደውና በመሰሎች የሚተካቸው እራሱ አይደልን? የፖለቲካው ድብቅ ተልዕኮ አስፈፃሚ የሚያደርጋቸው እራሱ አይደልን? ልማት የሚሰራባቸው ቦታዎች ተመርጠው እንዲሰሩ የሚያደርግ እራሱ አይደልን? ሌላው ቀርቶ በየመንግስት ቢሮዎች ደብዳቤዎች የሚፈረሙት በሕዋሓት ፍቃድ አይደለምን? ፖለቲካው እንዳይነካ ሌት ተቀን የሚዳክረው እራሱ አይደለምን? ለፖለቲካው ልዩ ጥበቃ እያደረገ ሀገራዊ ጉዳዮች እንዲህ እስኪ በላሹ ቆይቶ መልሶ በአመራሮች የሚያመካኘው እራሱ አይደለምን? አመራሮች ከሕዋሓት አንዲት ፍቃድ ሳያገኙ የትኛውን ጉዳይ ነው በግላቸው የሚፈፅሙት? ለትንሽ ለትልቁ ቢያንስ በስልክ ፍቃድ ሳይጠይቅ የትኛው አመራር ነው የሚሰራ? ተው እንዲህ የሞኞች ጫፍ አታድርጉን፡፡ ተው ተው እናንተ ሰዎች!!!

ነገር ሁሉ እንዲህ ሆኖ ሳለ በአካባቢያችሁ አመራሮች ተማረሩ በእኛ በሕዋሓቶች አትማረሩ እያለ በስልጣን እያላዘነ የሚፈልገውን ከ25 ዓመታት በኋላ ትግራይን ቀጣይዋ የአፍሪካ ሀገር ለማድረግ ከሚያደርጋቸው ትግሎች መካከል አንዱ ማስተባበያው መሆኑ ሊገርመን አይገባም፡፡ ህልሙ እውን ሳይሆን ከነቃን እዛው እንቅልፍ ላይ እያለ ህልሙን ሳይጨርስ በተባበረ ክንድ መግታት እንችላለን፡፡ እግ/ር ይርዳን፡፡ ለእነሱ ደግሞ ረዳት ያሳጣቸው፡፡ አሜን፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.