የወንድሞቻችን ደም ይጣራል!!ይጮሃል !! (ከባህርዳር ወጣቶች የተላለፈ መልዕክት )

ስለእውነት ትናንት አብረውን በባዶ እጃችን ሰልፍ ወጥተን በህወሓት አጋዚ ነፍሰ በላ ቅልብ ወታደር በጥይት አረር ከጎናችን የተሰውት፤ የዕድል ነገር በእጀችን ላይ የወደቁት የነፃነት ፍኖወች ሰማዕት
ጓዶቻችን ደም ሳይደርቅ ኮንሰርት ባህርዳር ላይ ? ጭፈራ ወልቃይት ዳንሻ ላይ ? አይደረግም !!
አይሆንም !!
የባህርዳር ህዝብ ሆይ ፦
ምነው ተዘነጋህ ነሃሴ 1 – 2008 ዓ.ም ? ውድ ወንድሞችህንና ጓዶችህን ፣ልጆችህን በህወሓት አጋዚ ጥይት ያጣህበት ቀን ! የግፉ ጂማሮ የእስራቱ ፣ድብደባው ፣መሰቃየቱ፣ መጠንሰሻ ቀን !
ህወሓት/ብአዴን ፀረ ህዝብ አቋሙን በይፍ ካወጀ ወዲህ ስንት ነገር ደረሰብህ? ድብደባው ፣ግድያ መልገላታቱ ፣አሰቃቂ ስቃይ … ይሄው ዛሬም በሀዘናችን ላይ እንጨት ልሰነቅር ኮንሰርት አዘጋጀ ያውም ባህርዳር ላይ ። አስታውስ የወንድሞቻችን ደም የፈሰሰበት ሁሉ ያያል ፤ይጮሃል ፤ይመሰክራል።
አዎ! ይመስክር ኮበል ኢንዱስትሪ የቀበሌ 11 ፣ይመስክር የቀበሌ 14 ፣የቀበሌ 7 ፣የቀበሌ
15 …የድባንቄ መድህሃኒዓለም ጎዳናወች የወንድሞቻችን ደም የነጠበበት ፣ይመስክር ክንድህ –
ወንድምህን የተሸከመው ፤ይመስክር እጆችህ -በወንድሞቻችንን ደም የታጠበው ፣ይመስክሩ ሀኪም
ቤቶች – የወንድሞቻችን አስከሬኖች የተገነዙበት ….
በወንድሞቻችን ደም የሚጫወተውና የሚያሾፈው የህወሓት/ብአዴን ወንጀለኛ ቡድን በቃህ ልንለው
ይገባል ። ይህ ሰላም አስመሳይነቱ ልናጋልጠው በህዝብ ላይ ማናለብኝነቱንና ትቢተኛ ልቡን
ልናስተነፍሰው ይገባል። ህወሓት በሰማዕታት በወንድሞቻችን ደም እያላገጠ ይገኛል ።ስለዚህ
የባህርዳር ህዝብ ወደ ኮንሰርቱ ባለመግባት፣ሌሎችን በመምከር ላልሰሙት በማሰማት
የህወሓትን ምኞት ከንቱ ቅዥት እናደርገው ዘንድ ከጎናችን በተሰውት ወንድሞቻችንና ጓዶቻችን
፣ስለነፃነት በእየማጎሪያ ቤቱ በታሰሩ ወገኖቻችን ስም ጥሪ ተላልፎልሃል ።
ድል የህዝብ ነው !!
ወንድሞቻችን ሰማዕት የሆኑለትን፣የታሰሩለትን ፣የተሰቃዩለትን የነፃነት ትግል ከግቡ እናደርሳለን !!
አንድነት ሃይል ነው !!
(ገብርየ)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.