የመጨረሻው መጀመሪያ የሆነውን የዐማራ ሕዝብ ተጋድሎ ዛሬውኑ በሞረሽ ወገኔ በኩል እንርዳ! – ሞወዐድ

ሞወዐድ ማስታወቂያና ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

የዐማራ ማንነት ጥያቄን መሰረት አድርጎ የተቀጣጠለው የዐማራ ሕዝብ ተጋድሎ ግብ የመኖር ህልውናችንን የነጠቀንን የትግሪዎች ነፃ አውጭ ግንባር ሰንሰለት በጣጥሶ ለማሽቀንጠር ነው። አሁን በተባጭ በተግባር በምድር ላይ ያለውን ፍልሚያ ከያሚያደርጉት ሕዝባዊ ኃይሎችና ጀግኖቻችን ጎን በመሰለፍ በውጭ ያለነው ተጋድሎው የሚፈልገውንና የሚጠይቀውን ሁሉ ማቅረብና መርዳት ይጠበቅብናል። ይህንንም ለማድረግ ሥልቶችና አመቺ ሁኔታዎች በሞረሽ ወገኔ ዐማራ ድርጅት አማካኝነት ተዘርግተዋል። በውጭ የምንኖር ወገኖች በድርጅትም ውስጥ ያለንም ሆነ በድርጅት ውስጥ ያልታቀፍን ወገኖች በጋራ ቆርጠን በመነሳት ከጀግኖቻችን ና አርበኞቻችን ጎን እኩል በመቆም የተቀጣጠለውና ዳግም የማይታጠፈውን ተጋድሎ ወደ ሠፊ ሕዝባዊ ንቅናቄ ለማስደግ እንችል ዘንድ እርዳታችሁ በአፋጣኝ ይፈለጋል።
 
በጋራና በተቀናጀ መልክ ለሕዝብ ነጻነት የሚያበቃውን የዐማራ ሕዝብ ተጋድሎ ቀጣይነት ኖሮት በታላቅ የድል ተስፋ ወደፊት እንዲገፋ እጃችሁን እንድትዘረጉ መስዋትነት በመክፈል ላይ ባሉት ጀግኖች ስም እንጠይቃለን። የዐማራው ትንሣኤ የኢትዮጵያ ትንሣኤ ነውና ጎልያድን የዘረረ ባሕሩን ከፍሎ ያሻገረ አምላክ ጦርነት በዐዋጅ ከታወጀበት የዐማራ ሕዝብ ጋር  ይሁን።
የገንዝቡን እርዳታ በተያያዘው መግለጫ መሰረት በሚመቻችሁ መንገድ በሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት በኩል ማደረግ የምትችሉ መሆናችሁን በአክብሮት እናስታውቃለን።
ዐማራነት ወንጀል አይደለም!
ትግሉ ተጠናክሮ ይቀጥላል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.