የመለስ ዜናዊ ወዳጅ ቦብ ጊልዶፍ አዋሽ ወይን ጠጅ ፋብሪካን «ገዛ»! – አቻምየለህ ታምሩ

Blue Nile Investment, was formed through a partnership between 8 Miles, a UK based equity firm and Mulugeta Tesfakiros.

በወሎና ትግራይ ተከስቶ ለነበረው ርሃብ እርዳታ የሚውል ከአለም አቀፉ ማህበረሰብ ወደ 100 ሚሊየን ዶላር ተለግሶ ነበር። ይህንን አለማቀፍ ጥረት ካስተባበሩት መካከል ቦብ ጊልዶፍ ቀዳሚው ነበር። እነ ቦብ ጊልዶፍ ያሰባሰቡትን ገንዘብና የእርዳታ እህል ፋሽስት ወያኔ የእርዳታ እህሉን መንገድ ላይ አራግፋ ለሱዳን በመሸጥ የጦር መሳሪያ እንደገዛችበት የወያኔ ፊታውራሪዎች አጋልጠዋል።

የአለማቀፍ ጥረቱ አስተባባሪ የነበረውና የመለስ ዜናዊ ጭፍን አድናቂው ቦብ ጊልዶፍ ወያኔ ጫካ እያለ በድርቅ ለተጎዱ እንዲውል የተሰበሰበውን ገንዘብ ለመሳሪያ መግዣ አልዋለም በማለት ከነ አረጋዊ በርሀና ገብረ መድህን አርአያ በላይ አዋቂ ሆኖ መለስ ዜናዊንና ወያኔን ለአመታት ሲከላከል ባጅቷል።

ለዚህ ውለታው ይመልላ «ሰር» ቦብ ጊልዶፍ ከወያኔው ሙሉጌታ ተስፋኪሮስ ጋር በመሆን በኢትዮጵያ ለረጅም አመታት ያስቆጠረና በ1948 ዓ.ም. የተመሰረተውንና ተወዳጁን አዋሽ ወይን ጠጅ ፋብሪካ ገዝቶ ኢንቨስተር ለመሆን ወደ ኢትዮጵያ የገባው። ቦብ ጊልዶፍ ወያኔ የእርዳታ ገንዘብ ሽጦ ለነመለስ ዜናዊ በዋለው ውለታ ከአይሪሽ የፖፕ ሙዚቃ አቀንቃኝነት ወደ አለማቀፍ ኢንቨስተርነት ተመንድጎ ወደ ኢትዮጵያ ሲያመራ ለእርዳታ የተሰበሰበውን እለ መለስ ዜናዊ ለመሳሪያ መግዣ አውለውታል ብሎ ያጋለጠው ጆናታል ዲምቢልቢ ግን ኢትዮጵያን እንዳይረግጥ በወያኔ ታገደ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.