የውይይቱ መንሥኤ፤ ለውድ ፕሮፌሰር ፍቅሬ – ከፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ

የውይይቱ መንሥኤ፤

ለውድ ፕሮፌሰር ፍቅሬ፤ ከጌታቸው ኃይሌ

የውይይቱ መንሥኤ፤ ለውድ ፕሮፌሰር ፍቅሬ  - ከፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ 1
ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ

“የኦሮሞ እና የአማራ እውነተኛው የዘር ምንጭ” ብለህ የጻፍከው፥ እውነተኛው የዘር ምንጭ አይደለም ጥሩ ተረት ነው ብየ ምክንያቴን ብሰጥ ቁጣህ ከመጠን አልፎ ስድብ ውስጥ ገባህ። “ተረቴን እንደታሪክ አልቀበል ያልክ ሁሉ ጌታቸው የደረሰበትን አይተህ ተቀጣ” ማለትህ ይመስላል። ውይይታችን በመጽሐፍህ ውስጥ ስላካተትካቸው ሐሳቦች እንጂ፥ አንተንና አንዳንድ አራጋቢዎችን እንደመሰላችሁ፥ ስላንተ ወይም ስለኔ አይደለም። እኔ ማስረጃ ይዤ ተረቶች ናቸው ያልኳቸውን አስተዋፅኦችህን አንድ በአንድ ከነማስረጃዬ ዘርዝሬያለሁ፤ ጉዳያችን ያለው እዚህ ላይ ነው። ለናሙና ያህል ከዘረዘርኳቸው ዓሥራ ሦስት ስሕተቶች ውስጥ የአማራው ሕዝብ አባት የተፀነሰው እባሕር ውስጥ ነው ያልከው ስሕተት ይገኝበታል። ስሕተቶች ያልኳቸውን ስሕተቶች አለመሆናቸውን አንድ ባንድ እንድታስረዳ አንባቢህ ይጠብቃል። እውነተኛ ታሪክ ለመሆናቸው ማስረጃው ስድብና ውሸት አይደለም። መልስ መስጠት ካልቻልክ አፍረህና አርፈህ ዝም በል። ማፈርና መልስ አለመስጠት መብትህ ናቸው።
 
ስሕተቶችህን ማንሣቴን “በቂም በቀል መፅሃፉን ለማጠልሸት” ያደረግሁት አድርገህ ጽፈሃል። ምን ጥቅም ፈልጌ ያንተን ሥራ አጠለሻለሁ? አስተማሪ ስለሆንኩ ተማሪዬና የተማሪዬ ተማሪ (የኔ ተማሪ ዮናስ አድማሱና የዮናስ ተማሪ አንተ) በሙያችሁ አሸብርቃችሁ ሳይ እኮራባችኋለሁ እንጂ፥ ሥራችሁን አላጠለሽም። ውረድ ተዋረዱ የሚመሰክረው “ደቂቀ ጌታቸው” መሆናችሁን ነው። ቂሙና በቀሉ መንሥኤ የሌለው ክስ ነው። ከእኔ ሌላ በታሪክ ዕውቀታቸው የተከበሩ ሌሎች ሰዎችም በመጽሐፍህና በምንጭህ ቅሬታቸውን ገልጸዋል። የርዕዮት ጠያቂ ሙሉጌታ ጸጋዬም ሥራህን የነቀፈው አሸዋ ላይ የተመሠረተ ቤት ሆኖ ስላገኘው ነው። ንቀው ካልተውህ፥ ወይም በኔ ላይ ያወረድከው የስድብ ናዳ እንዳይደርስባቸው ካልፈሩ፥ ሌሎችም ሊነሡ ይችላሉ፤ ታዲያ እነሱ ሁሉ ቂም በቀል ያላቸው ሊሆኑ ነው ወይስ እኔ ብቻ ነኝ ቂመኛውና በቀለኛው?  —ሙሉውን  በፒ.ዲ.ኤፍ ለማንበብ ይህንን ይጫ

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.