ከ ጃንዋሪ 13 እስከ 14፤ በዋሽንግተን ዲሲ በጉጉት ሲጠበቅ የቆየው የኢትዮጵያ ኃይሎች ምክክር ጉባኤ ይካሄዳል

በሀገራችን ውስጥ የሚታየውን የግፍ አገዛዝ አስወግዶ በኢትዮጵያ አንድነት ስር የስርአት ለውጥ ለማምጣት የሚችል ሰፋ ያለ የተቃዋሚዎች ትብብር መፍጠር ጊዜ የማይሰጥ አንገብጋቢ አገር አድን ጉዳይ ነው። ይህንንም ተገንዝበን፤ ላለፉት ተከ ታታይ ወራቶች ለተግባራዊነቱ በጋራ ሰፋ ያሉ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ላይ ነን። እነዚህን ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች አስመልክቶ፤ ተከታታይ መግለጫዎችን በማውጣትና ለተለያዩ የዜና አውታሮቻና ማብራሪያዎችን በመስጠት ላይ እንገኛለን ። ያደረግንውን አገራዊ ጥሪ ወቅታዊነት በመገንዘብ፤ የተለያዩ ዽርጅቶች ለመሳተፍ ፍቃደኛ መሆናቸውን በደብዳቤ ምላሽ በ መላክ ማረጋገጣቸውን መግለጽ እንወዳለን።

ያወጣናቸውን የጋራ መግለጫዎች ለማንበብ እንዲሁም የሰጠናቸውን ማብራሪያዎች ለማድመጥ የሚከተሉትን ሊንኮች ይጫኑ፦ የሴፕቴምበር 7 መግለጫ የኦክቶበር 13 መግለጫ SBS ራድዮ ቃለ-ምልልስ የአማራ ራድዮ ቃለ-ምልልስ የአዲስ ድምጽ ቃለ-ምልልስ የህሊና ራድዮ ቃለ-ምልልስ

የምክክር ጉባኤው ዋና ጭብጥ በሀገራችን ውስጥ የሚታየውን የግፍ አገዛዝ በተባበረና በተማከለ ትግል አስገድዶ/አስወግዶ በኢትዮጵያ አንድነት ስር የስርአት ለውጥ ለማምጣት የሚችል ሰፋ ያለ የተቃዋሚዎች ትብብርን በመፍጠር፤ ለኢትዮጲያ ህዝብና ለአለም አቀፍ ህብረተሰብ አማራጭ የሚሆን ኃይል የማውጣት ጥረት ነው። በዚህ ዙሪያና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ እያ ንዳንዱ ድርጅት ያለውን አማራጭ (Presentation) የሚያቀርብ ሲሆን፤ ከዚህ በተጨማሪ የተለያዩ ምሁራን ጥናታዊ ጽሁፍ እንዲያቀርቡ ይደረጋል። ይህ ሂደት የተለያዩ የሚዲያ አውታሮችንና ዘዴዎችን በመጠቀም በቀጥታ ስርጭት ለህዝብ ይተላለፋል።

በቀረቡት ሃሰቦች ላይ በድርጅቶች መካከል ውጤት ላይ ለመድረስ ዝግ ውይይትና ምክክር ይካሄድና፤ የምክክር ጉባኤውን ውጤት ለህዝብ ይፋ ለማድረግ ቅዳሜ ጃንዋሪ 14 ከ 3 pm ጀምሮ ጋዜጣዊ መግለጫ (Press conference) ከጋዜጠኞ ች ጋር ይደረጋል፤ በዚህም ውይይት በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያኖች ተገኝተው መሳተፍ እንዲችሉ ለሕዝብ ክፍት ይሆናል።

የስብሰባ ቦታ፤ Meeting House Of Friends Quaker Hall 2111 Florida Avenue NW Washington DC ቅዳሜ፤ 14 ጃንዋሪ 2017 ከ 3 pm እስከ 7 pm

ለበለጠ መረጃ፤ ስልክ ቁጥር፤ +1 (571) 237-9571 ወይም +1 (202) 534-5861

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!

የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋር ትግል ሸንጎ (SHENGO)
የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት (ENTC)
የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄ (EYNM)

ENTC: contact@etntc.org EYNM: ethiorevolution@gmail.com SHENGO: shengo.derbiaber@gmail.com

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.