ዘረኛውን ወያኔ ፣ወደ ከርሰ መቃብሩ ለመውሰድ፣ ስንት ስም የለሽና ያልተዘመረላቸውን ገብርዬዎችን፣ መስዋእት ማድረግ ሊኖርብን ነው?

የሻለቃ መሳፍንት ጥጋቡ ወይም በቅጽል ስሙ የገብርዬ የመስዋእትነት ታሪክ፣ በጣም አንጀት የሚበላና እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ መርሳት የሌለበት ገድል ነው::  የአገር ፍቅር ልክፍት ማለት ምን ማለት እንደሆነ ፍንትው አርጎ የሚያሳይ፣ የሃቀኛና የጀግና ታሪክ ነው:
 
ከልጅነት እስከ እውቀት ድረስ ፣ሁለት መንግሥት ተዋግቶ፣ ኢትዮጵያን በውን ነጻ ለማውጣት፣ ውድ ህይወቱን የከፈለ፣ የማይረሳ  ኢትዮጵያዊ ነው::ዘረኛውና ወንበዴው የወያኔ ቡድን ፣የኢትዮጵያውያንን ደም እንደውሃ እያፈሰሰ በሚገኝበት በአሁኑ ሰዓት፣ ገብርዬን የመሰለ ጀግና ማጣት በጣም ያማል:: የገብርዬ ታሪክ በዚህ ቢያከትም ኖሮ፣ ምንኛ ባዘንን ነበር:: ግን ለአንዳፍታም ቢሆን የማንጠራጠረው ሃቅ  ቢኖር፣ ከአሁን በኋላ መቶ ሺ ገብርዬዎች እንደሚተኩ ነው:: 

የትጥቅ ትግሉ እየዳበረና በልምድ እየጎለበተ ሲሄድ፣ እልፍ አእላፍ ገብርዬዎች፣ እንደ አሸን እንደሚፈሉ አትጠራጠሩ:: ድላችንም፣ የዚያኑ ያህል ፣እርግጠኛ ይሆናል:: አሁን ጊዜው፣ የመስዋእትነት ሰዓት ነው:: ድሉን ለማየት፣ በዚህ የመስዋእትነት በር ማለፍ፣ የግድ ነው:: መንግሥተ ሰማያትን ወዶ፣ ሞትን ደግሞ ፈርቶ እንዴት ይሆናል?

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.