ሕወሓት በማህበራዊ ሚዲያ ሰራዊቱ በኩል ያቀረበው የካሳ ይከፈለኝ ጥያቄ ለኢትዮጵያና ለሕዝቡ ያለውን የከፋ ጥላቻ ያመለክታል

 ምንሊክ ሳልሳዊ

ሕወሓት በማህበራዊ ሚዲያ ሰራዊቱ በኩል ያቀረበው የካሳ ይከፈለኝ ጥያቄ ለኢትዮጵያና ለሕዝቡ ያለውን የከፋ ጥላቻ ያመለክታል። #Ethiopia #Tigray #TPLF #MinilikSalsawi

Minilik Salsawi – mereja.com – ወያኔ ሁለት አጀንዳ ይዛ ብቅ ብላለች። የኣግአዝያውያን የትግራይ ከኤርትራ ጋር የመደባለቅ የማጭበርበርያ ኣጀንዳ እና ኢትዮጵያውያን ለትግራይ ካሳ ይክፈሉ የሚል የፖለቲካ የበላይነትን ለማረጋገጥ የተፈጠረ አጀንዳ እያላወሱት ይገኛሉ።

ይህ ሁሉ የሚደርገው የለውጥ ሃይሉን ለማጭበርበርና የሃገር ሃብት በሰፊው ጨማምሮ በኣዲስ መንገድ ለመዝረፍ ብሎም ሕዝቡ እልዋጥለት ያለውን የሕወሓት የበላይነት ለማስረገጥ ሆን ተብሎ የተንደፈ የፖለቲካ ሴራ ነው። በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት የተሰዉት እኮ ኢትዮጵያውያን ናቸው። ትግራይ እንደ ባዳ ካሳ የሚያስፈልጋት ለምን ይሆን? ካሳ ይከፈል የሚሉት ኣካላት ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን ምን ያህል ጥላቻ እንዳላቸውና የበታችነታቸውን በግልጽ ያሳያል። በኢትዮጵያ አራቱም ማእዘን የኢኮኖሚና የፖለቲካ የበላይነት በጠበንጃ ሃይል መቆጣጠራቸውና የኢትዮጵያ ሕዝብ የሕወሓትን የበላይነት ይወገድ በማለቱ ስጋት የገባቸው ሃይሎች የፈጠሩት ተንኮል መሆኑ እሙን ነው።

 

ሕወሓት የበላይነቱን ተጠቅሞ በመከላከያ በደህንነትና በሌሎች ከፍተኛ የኣገዛዝ ቁልፍ ቦታዎች በበቂ ሁኔታ የራሱን የዘር ስሪቶች በበላይነት አስቀምጦ እንደ ኢፈርት ባሉ ድርጅቶች በሕገወጥ መንገድ ሃገርን እያስበዘበዘ በከፍተኛ ምዝበራ ላይ ተፈናጦ እያለ የገዛ ወንድሙ ከሆነው ሕዝብ በተፈናቀለ ሕዝብ ሰበብ በመፍጠር የክልሎችን በጀት እየዘረፈ ጥቂቶችን ከነጉጀሌዎቻቸው አበልጽጎ ቀሪውን የትግራይ ሕዝብ በብድርና ድህነት አማቆ እየኖረ ለትግራይ ሕዝብ ካሳ መጠየቅ ሕወሓት ያለበትን ስጋትና የሞራል ዝቅጠት ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።

 

የኢትዮጵያ ንብረትና ሃብት እውን የትግራይ አይደለምን? የትግራይ ሕዝብ ከገዛ ወንድሙ ካሳ እንዲበላ የሚደረገው የትግራይ ሕዝብ ኢትዮጵያዊ አይደለምን? ይህች ተንኮልና ሴራ ቀሪው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ቁርሾና ጥላቻ ለመፍጠር ታቅዶ ይሆን? በባድመ ግጭት በተለያዩ ግንባሮች የተሰዉና የተጎዱ ኢትዮጵያውያን የትግራይ ሕዝብ ወንድማቸው ስለሆነ አይደለምን? የትግራይ ደሃ ሕዝብ ኣብላጫውን የያዘው በብድር ተቆራምዶ በስሙ ካሳ የሚበላው ለማን ተብሎ ይሆን ? በትግራይ ውስጥ የተሰው ኢትዮጵያውያን ስለምንድን ይሆን ?ወንድም ከወንድሙ ካሳ ሊበላ መታቀዱ ምን ታስቦ ይሆን? ለሰላምና ለዲሞክራሲ ለሃገር ሉዋላዊነትና ለዳር ድንበር ተብሎ የተሰዉት ጀግና የሚባሉት የሕወሓት ሰዎች ብቻ ናቸውን ? ሌላው ምንም መስዋትነት አልከፈለምን ? በአሁን ወቅት በሕወሓት ጥይት እየተገdeሉ ላሉ ካሳ ተከፍሏል? እየታሰሩ ለሚፈቱት ምን አይነት ድጎማ ተደርጓል? በሃሰት ክስ ለሚሰቃዩትን ምን ተደረገ? ይህ ሁሉ ሲሆን ዜጎች ሲጎዱ ካሳ ያላለው የሕወሓት ማህበራዊ ሚዲያ ሰራዊት በኢትዮጵያውያን መስዋትነት እየኖረ ኢትዮጵያውያንን ካሳ መጠየቅ ለምን ኣስፈለገ? እና ሌሎች በርካታ ጥያቄዎች ማንሳት ይቻላል።

 

ይህ ሁሉ እየተሴረ ያለው ግን የፖለቲካ የበላይነትን ለማረጋገጥ፣ የበታችነት ኣባዜ መጣናወት፣ የጥላቻ አጀንዳዎችን ለማስረጽ፣ የራስን መውደድ ስሜት የፈጠረው የሃሰት ጀግንነት እውቅና ኣግኝቶ አጨብጫቢ ለማብዛት፣ ከዚህ ጋር የተያያዙ የጥላቻ ስሜቶችን ለማቀጣጠልና የበለጣ የጋለ ችግር ለመፍጠር ለመዝረፍና የተለመደውን የክልሎች በጀት በካሳ ስም ለመቀራመት የተወጠነ የክፋት ሴረኝነት መሆኑ ኣያጠያይቅም። ኢትዮጵያ ሕወሓት እንዳሰበው የምትከፋፈል ሃገር አይደለችም። ኢትዮጵያ መንፈሳአኡ የምስጢር ፍልስፍና ናት። ማንም እየተነሳ የሚያስፈራራበት ምንም እኩይ አላማ ለጊዜው ሲያወሩት ቢመስልም ኣይሳካም። ኢትዮጵያ ካሁን ቀደም የውጪ ሃይሎችም ይሁኑ የውስጥ ቦርቧሪዎች በራሳቸው ጉድጓድ ቀብራለች። አሁንም ትግሉ ይቀጥላል ኢትዮጵያ ትለማልማለች። #ምንሊክሳልሳዊ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.