የጥምቀት ከተራ በጎንደር ጭር ብሏል! ዘገባ ሁለት


የወጡትም ታዳጊ ወጣቶች ለወያኔ መልእክት ለማስተላለፍ ነው። ከወያኔ የአደጋ ወጥመድ እንዳትገቡ ጠንቀቅ ነው። ጥምቀትን በአደባባይ የምናከብረው ከነፃነት በሁዋላ ነው ብሎ በአንድ ልብ የተማማለ ጀግና ህዝብ። ለደህንነታቸው ሲባል ፊታቸው እንዳይታይ የተደረገው እነዚህ ታዳጊ ወጣቶች የጀግናም ጀግና ናቸው!
ጎንደር ላይ ሁሉም ተማምሎ አንወጣም ያለ ሲሆን በተጨማሪም ወያኔ የራሱን ባንዴራ በትልቁ ፒያሳ ላይ የሰቀለ ቢሆንም ጀግኖቹ የጎንደር ወጣቶች እኛ ይህን የዳቢሎስ ባንዴራ ቁመን ሲውለበለብ አናየይም በማለት ሌት አውርደውታል። በዚህም የተበሳጨው ወያኔ ወደ 400 የሚጠጉ ወጣቶችን አስሯል። እስር ቤቱ ሁሉ የተጨናነቀ ሲሆን በተጨማረም ህዝቡ እንደማይወጣ የተረዳው ወያኔ በዙሪያው ያሉ የቀበሌ ነዋሪዎችን በ 1 ለ 5 እና በልማት ቡድን በምከር በነፍስወከፍ ጎንደር መጥተው እንዲያከብሩ አበል ከፍሏል፡፡ በነገው ዕለት ወደ ጥምቀተ ባህሩ ለመረጨት የሚመጡ ጥቂቶች እንኳን ቢኖሩ ታቦታቱን አጅቦ የሚሄድ አይኖርም፡፡ ዛሬ ለከተራ በዓልም የወጡትም በወያኔ የተገደዱ የቤተ ክህነት ቀሳውስትና በእነሱ ተጠቃሚ የሆኑ ግለሰቦችና የትግሬ ደህንነቶች ናቸው፡፡በየመስሪያ ቤቱ እንዲወጡ ቢያስጠነቅቅም መንግሰት ሰራተኛው ውር ሳይል ወሏል፡፡ባለኝ መረጃም በዳባትና በደባርቅ ተመሳሳይ ድባብ ታይቷል፡፡

#ሙሉነህ ዮሃንስ#

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.