ታላቅ እና ደማቅ ልዪ የሙዚቃ እና የገንዘብ ማሰባሰብ ምሽት በሎሳንጂለስ

የጎንደር ህብረት ለኢትዮጵያ አንድነት (ጎህ) በአይነቱ ልዪ የሆነ ዝግጂት በሎስአንጂለስ አዘጋጂቷል በመጭው ቅዳሜ January 28, 2017 ምሽት ።

የጎንደርን አርበኞች ለወራት የዘለቀ የተጋድሎ ውሎ በአይነ ህሊናዎ እያሰቡ። ከሀገር ብንርቅም ጎንደሬዎች ከእናንተ ጋር ነን ፣ ለማለት ቃል የሚገቡበትን ምሽት ጎህ አዘጋጂቶልዎታል። እርስዎ ቤተሰብዎትን እና ጓደኞችዎን ይዘው መገኜት ብቻ ነው።
ዝነኛው አርቲስት ፋሲል ደመወዝ ወኔ ቀስቃሽ ዜማዎችን አዘጋጂቷል። ቀድሜ ወደ LA በመሄድ እዚያው እከተማዋ ሰንብቼ ነው ይህን ህዝብ የማስደስተው ብሎኛል።
ኦ! ኦ !ፋሲሎ መሳሪያውን ወል ውሎ ጃሎ ሊል ነው!
የእለቱ የክብር እንግዳ አንደበተ ርትዑ፣እጂግ ትሁት እና በጎህ አባላት ተወዳጂ የሆኑት ዶክተር አበበ ገላጋይ ናቼው።
የጎህ የሚዲያ ኮሚቲ ሰብሳቢ አቶ አቡኔ ብሩ ከጓደኞቻቼው ጋር ዝግጁታቼውን ቀድመው ማጠናቀቃቼውን ዛሬ በስልክ ነግረውኛል።
ለ LA ( ሎስአንጂለስ) ጎህ ቻፕተር መልካሙን ሁሉ ተመኜሁ
ልያ ፋንታ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.