በወልቃይት ‹‹ዐማራ ነኝ››በማለታቸው ይቅርታ እንዲጠይቁ የተነገራቸው የሃይማኖት አባት ታሰሩ፤ – ሙሉቀን ተስፋው

•በባሕር ዳር ለስብሰባ የተጠሩ ወጣቶች የብሔራዊ ውትድርና ግዳጅ እንዲሔዱ ተነገራቸው

ሙሉቀን ተስፋው
ሙሉቀን ተስፋው

ጥር 9 ቀን 2009 ዓ.ም በወልቃይት አዲረመጽ ከተማ በትግራይ ቴሌቪዥን እየተቀረጹ ‹‹ዐማራ ነኝ›› ማለታቸው ስህተት እንደሆነ በማመን ይቅርታ እንዲጠይቁ የተነገራቸው ዐማሮች ባለመስማማታቸው መታሰራቸውን ከቦታው የደረሰ መረጃ አመልክቷል፡፡ ከታሰሩት ሰዎች መካከል የእስልምና እምነት ተከታይ አባቶች እንዳሉበት ተገልጧል፡፡ ሼክ ኢብራሒም ሰይድ የተባሉት አባት ትግራይ ክልል እና የፌደሬሽን ምክር ቤት በመሔድ የወልቃይት ጠገዴ የዐማራ ማንነት ጥያቄን ከሚያቀርቡ ሰዎች መካከል እንደነበሩ የጠቆመው መረጃችን ዛሬ ከቀጥር በኋላ መታሰራቸውን አድርሶናል፡፡ ከሼክ ኢብራሒም ጋር ሌሎች ሰዎችም አብረው ታስረዋል ተብሏል፡፡
በሌላ ዜና ደግሞ ከሰሞኑ በዘጠኙም ክፍለ ከተማዎች በየቤቱ እየዞሩ የመዘገቧውን ዕድሜያቸው ከ18 እስከ 32 ዓመት የሆናቸውን ሴቶች በክፍለ ከተማ ጽ/ቤቶች በመጥራት መሠረታዊ የውትድርና ትምህርት ገለጻ ካደረጉ በኋላ ብሔራዊ ውትድርና ግዳጅ እንደምንሔድ ተነግሮናል ብለዋል፡፡ እንደመረጃ ሰጪዎቻችን ከሆነ በሥልጠናው ላይ የነበሩ ሥራ አጥ ወጣት ሴቶች ስብሰባውን እያቋረጡ መሔዳቸውን ነው የሰማነው፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.