በቤንሻንጉል የወርቅ ማእድን ማውጫን ለመቆጣጠር በተደረገ ጦርነት 4 የወያኔ ወታደሮች ተገደሉ። ብዛት ያላቸው ቆስለዋል

በዘርይሁን ሹመቴ

በቤኒሻንጉል ጉምዝ የህውሃት ወያኔ ወታደሮች በክልሉ ሸምቀው ከሚታገሉ የነጻነት አርበኞች ጥቃት እንደደረሰባቸው ተሰምቷል።

ይህ ከፍተኛ የወርቅ ክምችት ያለበት ክልል የመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ሃብትነት መሆን ቀርቶ በአገዛዙ እና ስርአቱን በመደገፍ በሚታወቁት በሼክ አላሙዲን ስር የሚገኝ ነው።

እንደ ምንጮች ገለጻ መሰረት በሸረቆሌ የሚገኘውን የወርቅ ማእድን በሚጠብቁ የወያኔ ወታደሮች ላይ በተከፈተ ጥቃት የአገዛዙ ወታደሮች ለጉዳትና ለሞት ተዳርገዋል።

በዚህ የነጻነት ታጋዮች በተከፈተ ጥቃት አራት (4) የህውሃት ወታደሮች መገደላቸውና ቁጥራቸው በዛ ያሉ ደግሞ ለከፍተኛ የአካል ጉዳት እንደተዳረጉ ሪፓርቶች ይገልጻሉ።

እጅግ ከፍተኛ የወርቅ ክምችት ከዚሁ ክልል የሚወጣ ቢሆንም የአካባቢው ተወላጆችና ነዋሪዎች ከጥቅሙ የመጋራት እድል በአገዛዙ ተነፍገዋል።

በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የነጻነት ሃይሎች ይህንን የወርቅ ማእድን ማውጫ አገዛዙ ካሰማራቸው ወታደሮች ለመንጠቅ ባደረጉት ውጊያ ሃለፎም እና ወራዊ አብርሃም የሚባሉ የትግራይ ተወላጆች ወታደሮች መገደላቸው ተረጋግጧል።

እንደዚህ ያለው እምቅ የኢትዮጵያ ሃብት በአገዛዙ ባለስልጣናት ብቻ ኢፍትሃዊ በሆነ መልኩ ጥቅም መዋሉ በክልሉ ለሚፈጠረው ተደጋጋሚ የትጥቅ ትግል ዋንኛ ምክንያት ሆኗል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.