በአማራው ክልል ያለውን ቀውስ በተመለከተ #ግርማ_ካሳ

 

ገዢው ፓርቲ ሕወሃት/ኢሕአዴግ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጆ በአሥር ሺሆች የሚቆጠሩትን አስሮ፣ ብዙዎችን ገድሎ መረጋጋት በአገሪቷ አምጥቻለሁ እያለ ነው። ሆኖም ግን ከአማራው ክልል የሚደርሰን ዘገባ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አራት ወር ሆኖትም ችግሮች እንዳሉ ነው። ከተላልቅ ከተማዎች ዉጭ በገጠር ትጥቅ ያነሱ ወገኖች የአገዛዙን ታጣቂዎች እየተዋጉ ሲሆን ብዙ ወታደሮች እየሞቱ እንደሆነም እያነበብን ነው።

ይሄ ሰዎችን ሊያስደንቅ አይገባም። ዘለቄታ ያለውን መረጋጋት ማምጣት የሚቻለው ዜጎችን በማሰር፣ በመገደል፣ በአስቸኳይ ጊዜ በማወጅ ..አይደለም። ሕዝብን በማክበር፣ ያሉ ችግሮች በዉይይት ለመፍታት በመሞከር ነው።

ሕወሃት/ኢሕአዴግ ከተቃዋሚዎች ጋር ድርድር ጀምሯል። ይሄ ድርድር የሕዝብን ጥያቄ ባስተናገደ መልኩ ከቀጠለ፣ ሕዝብ አገዛዙ ለሰላም ቁርጠኛ መሆን የሚያሳዩ ፍንጮች ካየ ያኔ መረጋጋት ሊመጣ ይችላል። ይሄን መልካም አጋጣሚ አገዛዙ ባያበላሽና በድርድሩ ችግሮችን በሰላም ለመፍታት serious ቢሆን ይሻለዋል።

በአማራው ክልል ስላሉ አለመረጋጋቶች፣ የሚያሳዪ ፣ ባለፉት ጥቂት ቀናት ዉስጥ የተለቀቁ አንዳንድ ጦማሮች እንደሚከተለው ቀርበዋል።

==================

#ሰበር_ዜና # ከፋኝ
#ዛሬ 8:30 ላይ የ # ከፋኝ_አማራ_ሀይል አንዱ ክንፍ የሆነው በ________የሚመራው ጦር በወያኔ
የተደረገበትን የደፈጣ ውግያ እንደተለመደው በድል አሸንፎ ተመልሶአል። ከወያኔ ወታደሮች ብዙው
ቁስለኛ ሲሆን ወደ አስር ሚሆኑ የአገዛዙ ወታደሮችም በነበረው ውግያ እስከወድያኛው
አሸልበዋል። ከከፋኝ የአማራ ሀይል አንድ ቀላል ጉዳት ደርሶአል።
#ቀኘው
©ከፋኝ
====

#አሁን_የደረሰን_ዜና
#በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር #ጋይንት አካባቢ #በጋይንቱ #ቴዲ የሚመራው ቡድን ከወያኔ
ወታደሮች ጋር ባደረገው ውጊያ 10 የወያኔ ወታደሮች ሲገደሉ 20ዎቹ ኩፉኛ ቆስለው # አንድ
የወያኔ 10 አለቃ ወታደር ተማርኳል፡፡
#ድል ለሰፊው!!!
© Tlaye Tlaye
=====

#የድል ዜና
#በሰሜን ጎንደር በምዕራብ # በለሳ አርሶ አደሩን ትጥቅ ለማሰፈታት የወያኔ ጦር ከበባ
ቢያደርግም ከአካባቢው በተጠራሩት አርሶ አደሮች የአፀፉ እርምጃ ተወሰዶባቸው ብዙ የጠላት
ጦር ሙትና ቁሰለኛ ሲሆኑ የቀረው እግሬ አውጭኝ ብሎ ፈርጥጧል።
እንዲህ ነው በለሶች ሲነሱ!
ምንጭ፡) ዞብል
©ሙሉነህ ዮሃንስ
======

#ትላንትና ጥር 27/2009 ዓም #በበላሳ ወረዳ ኮዛ አቦ በተባለ ቀበሌ የአማራ ንቅናቄ ሀይል
የተባለ ሀይል በመላ ሀገሪቱ
የሚንቀሳቀሱ የነጻነት ሀይሎችን ለዛሬ ስብሰባ ጠርቶ እንደነበረ ታወቋል:: የዚህ ስብሰባ አላማ
በመላ ሀገሪቱ በተለይም በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ ሀይሎችን በአንድ እዝ ስር ለማድረግ
የታሰበ ሣይሆን እንደማይቀር ይታመና::ል ይህንን እቅድ ለወያኔ ማን አሳልፎ እንደሰጠ ለጊዜው
አልተገለፀም:: የወያኔ ሠዎች ይህንን ሀይል በአንድ ላይ ለመደምሰስ አስበው በበርካታ ሰራዊት
ከበባ በማድረግ ለማፈን ያደረጉት ሙከራ ከሽፎባቸዋል:: ከነጻነት ሀይሎቹ እስካሁን ጉዳት
የደረሰበት አካል እንደሌለ ተገልጿል:: በወያኔ በኩል ለጊዜው ቁጥራቸው ያልታወቀ ወታደሮች
መማረካቸውም ታውቋል:: እስካሁን መረጃውን ለወያኔ አሳልፎ የሠጠው አካል በትክክል
ባይታወቅም ጥርጣሬዎች አሉ::
ይህንን ስብሰባ በዋናነት የጠራው ግለሰብ ጋበው የተባለ ሲሆን ለዛሬ የተጠራው ስብሰባ
በታቀደለት መሠረት መካሄድ አልተቻለም፡፡
©ለገሰ ወልደሃና

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.