አረና ትገራይ  ቡዙ ችግር የነበረው ነባር  አመራሩ  ሽም ሽር በማድረግ  የአረና አማራር  በአብዛኛው  በቡቁ ሙሁራን  ፓለቲከኞችና  ወጣቶች ተቀይሯል

ከአስገደ ገብረስላሴ መቀለ ፣

አረና ትግራይ ከአባታውነትና ከህወሐት ሰርጎ ገቦች ተነጻጻሪ ነጻነት አግኝቷል !! ይህ  ማለት የአረና የሀይል ሚዛን አሰላለፍ  በቅን ፓለቲኮኞችና  አገር  ወዳድ ዲሞክራቲክ  ሀይሎች እጅ ገብቷል ማለት ነው :: የዚሁ ወጤት ደግሞ  ለኢትየጱያ ህዝቦች  በአጠቃላይ   በተለይ ደግሞ በህወሐት አፈና በልዩ መንገድ  ተጨምድዶ  ተይዞ  ያለው የትግራይ  ህዝብ   ትልቅ ተስፋ ነው::

ዓረና ትግራይ ለሁት ቀን  ያህል ለሊትም ጨምሮ  ባደረገው ጉባኤ  የኢትዮጱያ ምርጫ በርድና የውጭ የአመሪካ የጀርመንና  የፋና ብሮድ ካስት    ጋዜጦኞች በተገኙበት ጉባኤው ከተከፈተ በኃላ ለሁለት ቀንና አንድ ለሊት ባካየደው  ዝግ ስብሰባ ቡዙ አገራዊና  አለማዊ አጀንዳዏች  እንዲሁም የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብና  ፕሮግራም  ካየ  በኃላ   የማእከላይ ኮሚቴ  እጩዏች  በሚመለመሉበት  የአሮጌው ማእከላይ ኮሚቴ  አማራር በነበሩት  አባላት  በጉባኤው  ተሳታፊዏች  ከባድ ሂስ ተሰንዝሯል ::

ከባድ ሂስ ከተሰነዘረባቸው  አማራሮች  የአሮጌው አማራር ሊቀመንበር  ነበር  አቶ ብርሀኑ በርሄና  አቶ  ዓንዶም ገብረስላሴ የአረና የህዝብ  ግኑኝነት  ወይ  ፓለቲካ  ሀላፊ  የነበሩ  ይጠቀሳሉ  ::   ሌሎች አማራሮችም በየየነበሩበት የስራ  መስክና  ሀላፍነት  ደካማ ጎናቸው የተገመገሙ ሲሆኑ ፣ የአረና ሊቀመንበር ነበር ቡርሀኑ በርኸ ግን በነበሩበት የአማራር ዘመን  በሚከተሉት  የነበሩ የተበላሸ አሰራር በሽ የመቆጠሩ
የአረና አባላት  እያባሳጩና በተለያዬ ጸረ  ዲሞክራሲ አሰራራቸው እንደ አባረሩዋቸው  በጉባኤው መድረክ ሂስ ተሰንዝሮባቸዋል ።  በመሆኑም በጉባኤው በተሰነዘረባቸው ሂስና ጉባኤተኛው በሂደት እየተከታተለው  በመጣ ትአዝብት  ግምት ላይ በማስገባት  ለብርሀኑ በርሐ  ከሊቀመንበርነትና ከስራ አሰፈጻሚነት  ቦታቸው እንዲወድቁ አድርጓል ። አቶ ብርሀኑ በርሀ ለ13  ወራት ያህል ታመምኩ በማለት ከትግሉ ርቀው ከርመዋል ። ጭራሹም የፓርት አማራሮች  ከማባረርና    መበታተን ካልሆነ  በስተቀር የሚጠቅም አማራር ይሰጡ እንዳልነበሩ ፣  በፓርቲ የተሰጣቸው ሀላፍነት አመራራቸው  እንዳልተወጡ  ። በአንጻሩ የግል የጥብቅና ሰራና ሌላ ቢዝነስ ይሰሩ እንደነበሩተነግራል።
ወደ አቶ ብርሀኑ ለረጅም ጊዜ እየተሰበሰበ የመጣ የአረና አባላት ጥላቻና  መጠራጠር  በኃላቸው አሰልፈዋቸው የነበሩ ጥቂት ቡዱኖችም ተቀባይነት  እንዲያጡ አድርጓል ።

         የአቶ ብርሀኑ  ቡዱን  ወደ ጉባኤው ሲመጣ   ስልጣን በበላይነት ለመቆጣጠር  እና እስከመረበሽ  ድረስ ታሳቢ አድርገው  በጉባኤው  አዛጋጅ ኮሚቴ ወክልና ሳይሰጣቸው ወደ  ጉባኤው በሀይላቸው  ጥሰው የገቡ ሰርጎ ገቢዎች  እንደነበሩ  በጉባኤው ውስጥ የነበሩ ምንጮች ተናግረዋል ።  ሆኖም ግን በዲሞክራቲክ ሀይሎች ጠንካራ ትግል  አልተሳካላቸውም ። የማይናቅ ቁጥር ያላቸው አመራሩ እንደቁማር ሊወሩት  የመጡ ግማሾቹ የማእከላይ ኮሚቴ  ማጨት ሲጀመር ቡዛሀኑ ድምጻቸውን  ሰለከለከሉዋቸው  ጉባኤው አቋርጠው ወጥተው  ሄደው በማህበራዊ ሚድያ ስድብ ጀምረዋል ።  ሌሎች ደግሞ  አቅጣጫው በመታዘብ  ሳይዋረዱ  አሰቀድመው  ወደ ማእከላይ ኮሚቴ  ምርጫ  አንወዳደርም ብለው ከውድድሩ  ራሳቸው አግልለዋል ። በመጨረሻ የብርሀኑ በርሀ ቡዱኖች በሙሉ  ለማለት ይቻላል  ያሰቡት  ከሽፎባቸው ሞራላቸው ወደ ዜሮ ወርዳል ።

በመጨረሻ የጉባኤ ሂደት  በ28 /5 / 2009  ወደ
29/  5።/209  ዓ ም  አጥብያ 8  ሰአት ለሊት ተጣናቅቋል።
በመጨረሻ የሚከተሉት ማእከላይ ኮሚቴ በመምረጥ  ጉባኤው ተጠናቅቋል ።
1 አብርሀ ደስታ ከመቀለ ዩንቨርሲቲ  በከፍተኛ ድምጽ
2 ጎይቶኦም ጸጋይ የአረና መስራች. በከፍተኛ ድምጽ
3ደጉተር ማርቆስ ገሰሰ በከፍተኛ ድምጽ
4  ዓንዶም ገብረስላሴ  በከፍተኛ ድምጽ
5። መምህር የውሀንስ ከመቀለ በከፍተኛ ድምጽ
6 ካህሳይ ዘገዬ ከአጽቢ ደራ በከፍተኛ ድምጽ
7   አቶ ገብሩ  አስራት ከአዲስ አበባ  በከፍተኛ ድምጽ
8  ወይዘሮ  አረጋሽ አዳነ በከፍተኛ ድምጽ
9  ተክለዝጊ ወልደገብሪኤል ከፍተኛ ደምጽ ከተንበ
10 ኪዳነ አመነ ከጉሎ መኸዳ ብዘት
11 ዘነበ ሲሳይ ከወልቀይት  ዳንሻ አውራ
ከዚህ በላይ የተዘረዘሩ ስራ አስፈጻሚ ሲሆኑ ቀጥለው የተዘረዘሩ ደግሞ ማእከላይ ከሚቴ ናቸው ፣
12  ወይዘሮ   አብረኸት ረዳ ኩናማ ከሸራሮ
13 ክብሮም በርኸ ከጉሎ መኸዳ አዲስ አበባ
14 መሐመድ ጅሀር ከግጀት
15  አድሀና አብርሀ ከማይጨው
16   አቶ ብርሀነ በርሀ ከመቀለ ወይ ሳምረ
17  ሕድሮም ሀይለስላሴ ከአጽቢ ደራ
18 ሀፍታይ ገረርፋኤል ከሀውዜን
19 ሀይለኪሮስ ታፈረ ከውቅሮ ክልተውለዕሎ
20 አሰፋ ተካ ከውቅሮ “””””””””
21 ዜናዊ አስመላሽ ከተንቤን ዓብይ ዐዲ
22 አውዓሎም  ወልዱ
23. ሀብተ ግርማይ ከማይጨው
24 ተስፋስላሴ  ከሳምረ ሰሐርቲ
25 ጸጋይ ሕሉፉ ከአበርገለ

የቁጥጥርና የኦዲት ኮሚቴ ሆነው ከተመረጡት ሰባት ሰዏች አራቱ የሚከተሉት ናቸው ።
1  አማረ ተወልደ ከመቀለ ወይ አድዋ
2 ጽጋቡ ቆባዕ ከመቀሌ ኩሐ
3  ሱሙር አባዲ ከተንቤን
4  ወልደገብርኤል ሀይሉ  ሌሎች ሰወስት ሰወች ተመርጠዋል  ።

ጉባኤው በመጨረሻ  በኢትየጱያ ካሉት ሰላማዊ ተወዳዳሪ ፓርቲዏች በተወሀደ አንድነት አብሮ እንደሚታገል ወስኖ እንደወጣ ታውቃል
ለዛሬ ይብቃኝ
ከአስገደ ገብረስላሴ መቀለ ፣
29 /  5/  2009   ዓ ም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.