ገንዘቤ ዲባባ በ2000 ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር የዓለም ሪከርድ ሰበረች

ጀግናዋ አትሌት ገንዘቤ ዲባባ በ2000 ሜትር የቤት ውስጥ ሩጫ የዓለም ክብረ ወሰንን ሰበረች:: ከሰዓታት በፊት በስፔን ሳባደል ከተማ በተደረገው የሩጫ ውድድር ኢትዮጵያዊቷ ጀግና በ5:23.75 በመግባት ታሪክ ሰርታለች::

በቤት ውስጥ ውድድር ዛሬ ያስመዘገበችው ሰዓት በተመሳሳይ የውጭ ውድድር ካላት ሰዓት የተሻለ ፍጥነት እንዳለው የስፖርት ባለሙያዎች ተንትነዋል::

ይህ ሪከርድ በገብርኤላ ዛቦ ከ1998 ጀምሮ ተይዞ ነበረ::
በኦሎምፒክ መድረክ ብራዚል ላይ የብር ሜዳሊያ በ1500 ሜትር ያሸነፈችው ገንዘቤ ባለፈው ዓመት በዓለም ሻምፒዮና ወርቅ ማግኝጧ አዘነጋም::

ገንዘቤ በ2015 የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የዓለማችን ምርጥ አትሌት ብሎ እንደሰማት ይታወሳል::

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.