ፕሬዚዳንቱ ስደተኞችን አስመልክቶ የሰጡት ትዕዛዝ ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሊያመራ ይችላል ተባለ

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስደተኞችን አስመልክቶ የሰጡት አከራካሪ ትዕዛዝ መጻዒ ዕድል በአሁኑ ወቅት በዩናይትድ ስቴትስ የፌዴራሉ ፍርድ ቤት እጅ ውስጥ ይገኛል። በመጨረሻ ግን ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ሊያመራ እንደሚችል ይገመታል።

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስደተኞችን አስመልክቶ የሰጡት አከራካሪ ትዕዛዝ መጻዒ ዕድል በአሁኑ ወቅት በዩናይትድ ስቴትስ የፌዴራሉ ፍርድ ቤት እጅ ውስጥ ይገኛል። በመጨረሻ ግን ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ሊያመራ እንደሚችል ይገመታል።

ይህ የስደተኞችን ወደ ዩናይትድ ስቴትስ መግባት ያቋረጠውና አብዛኞቹ ሙስሊሞች ከሚኖሩባቸው የሰባት ሃገሮች ዜጎች ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ በጊዜአዊ መልክ የሚያግደው የፕሬዘዳንት ትራምፕ ትዕዛዝ ባለፈው ሳምንት በአንድ የፌዴራል ዳኛ መታገዱ ይታወሳል።

ሁለቱም የሚስተር ትራምፕ ተቺዎችና ደጋፊዎች ይህን ሕጋዊ ጦርነት የሚያዩት በሕገ መንግሥቱ መሠረት ፕሬዚዳንታዊ ሥልጣናቸው የሚፈተንበት የፍትህ ዘርፉ ደግሞ ሕጉን ተመርኩዞ ፕሬዚዳንቱን የመቆጣጠር መብቱ መጠበቁ የሚታይበት ቁልፍ ነጥብ አድርገው ነው የተከራከሩት።

ለፕሬዚዳንት ትራምፕ ስደተኞች ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ለመጓዝ የሚያደርጉትን ጥረት ለማጥበቅ የሰጡት ትዛዝ የአሜሪካውያንን ደኅንነት ለማስጠበቅ በታቀደ ብቻ ነው፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

[jwplayer mediaid=”30240″]

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.