እሁድ ታህሳስ 12 በሚደረገው የህዝብ ታዛቢዎች ምርጫ በእኛ በኩል የሚከናወኑ ተግባራት

  1. የፓርቲ አባላት የሆን ሁሉ በየቀበሌው በሰዓቱ መገኘት፤ ሌሎች የምናውቃቸው ሰዎች ሁሉ ዘመድም ጓደኛም ሊሆን ይችላል በዕለቱ በየቀበሌው ተገኝቶ የህዝብ ታዛቢዎች እንዲመርጡ ማድረግ
  2.  የህዝብ ታዘቢ ሆነው ሊመረጡ የሚችሉት የፖለቲካ ፓርቲ ወይም የቀበሌ ይሁን የወረዳ ካብኔ አባል ያልሆኑ፤ ከማንኛውም ፖለቲካዊ አቋም ገለልተኛ መሆናቸውን የተረጋገጡ ሰዎች ብቻ ናቸው፤ በመሆኑም፤ ከዚህ ውጪ ገዥው ፓርቲ ለማስመረጥ ከተንቀሳቀሰ መቃወምና ማስቆም ይኖርብናል፤ በዚህ መንገድ ገዥውን ፓርቲ ማሳፈርና የህዝቡም ፍርዓት ደግሞ እንዲወገድና በእኛ ላይ እምነት እንዲኖረው ለማድረግ ያግዛል።
  3.  የህዝብ ታዛቢዎች ምርጫ የሚያስፈፅሙት ከምርጫ ቦርድ የተላኩ ሰዎች ብቻ ናቸው፤ በቀበሌ ሰዎች ወይም በካብኔ አባላት አስመራጭነት የሚካሄ ከሆነ ማስቆም ይኖርብናል
  4. በህብረተሰቡ ዘንድ ከበሬታና ተአማሚነት ያላቸው ሰዎች በመጠቀም እንዲመረጡ ማድረግ በዕለቱ የሚኖረን ቁልፍ ተግባር ነው።
  5. እነዚህ ከላይ ያሉትን ተግባራት በግልፅ ማራመድና ማስፈፀም ከቻለን መራጩ ህዝብ አብረነው እንዳለን ይረዳል፤ ለመምረጥ ያለው ፍላጎትም እንዲጨምር ያደርገዋል፤ እኛ በዕለቱ ያደረግነውን ያልተጠበቀ እንቅስቃሴ አጀንዳ አድርጎት በየቤቱ እንዲወያይበትና አቋም እንዲይዝ ጥሩ አጋጣሚ የሚፈጥር ነው የሚሆነው።

12913_744918145593122_1266222571860551173_n

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.