ለኢትዮጵያ ነፃነት አበክረዉ ይታገሉ ከነበሩት ሪቻርድ ፓንክረስት አረፉ (እሸቴ በቀለ & ነጋሽ መሐመድ)

ሪቻርድ ፓንክረስት

ኢትዮጵያ በፋሺስት ኢጣሊያ በተወረረችበት ወቅት ለኢትዮጵያ ነፃነት አበክረዉ ይታገሉ ከነበሩት ከብሪታንያዋ ዶክተር ከሲልቪያ ፓንከርስት የሚወለዱት ሪቻርድ ፓንክረስት እንደ ጎርጎሪያኑ አቆጣጠር ከ1956 ጀምሮ የሚኖሩት ኢትዮጵያ ዉስጥ ነበር።
አንጋፋዉ የኢትዮጵያ ታሪክ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት አረፉ።ዘጠና ዓመታቸዉ ነበር።የኢትዮጵያን ታሪክ በማጥናት አቻ የማይገኝላቸዉ ፓንክረስት በኢትዮጵያ እና ሥለ ኢትዮጵያ ጉዳይ ብቻ ከ20 በላይ መፅሐፍት ያሳተሙ በሳል ሙሕር፤ ኢትዮጵያን አፍቃሪና ለኢትዮጵያ ታላቅ ባለዉለታ ነበሩ።ፓንክረስት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን በፕሬዝደትነት የመሩ እና የዩኒቨርስቲዉን የኢትዮጵያ ጥናት ተቋምን የመሠረቱ ምሑርም ነበሩ።ኢትዮጵያ በፋሺስት ኢጣሊያ በተወረረችበት ወቅት ለኢትዮጵያ ነፃነት አበክረዉ ይታገሉ ከነበሩት ከብሪታንያዋ ዶክተር ከሲልቪያ ፓንከርስት የሚወለዱት ሪቻርድ ፓንክረስት እንደ ጎርጎሪያኑ አቆጣጠር ከ1956 ጀምሮ የሚኖሩት ኢትዮጵያ ዉስጥ ነበር።ፓንክረስት የአንዲት ሴት እና የአንድ ወንድ ልጅ አባት ነበሩ።ወንድ ልጃቸዉ ዶክተር አሉላ ፓንክረስት በኢትዮጵያዊዉ ጀግና ስም ከመሰየማቸዉም በላይ የአያት አባታቸዉን ፈለግ ተክትለዉ የኢትዮጵያን ጉዳይ የሚያጠኑ፤ ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚያስተምሩና የሚኖሩ ምሁር ናቸዉ።እሸቴ በቀለ የፓንክረስትን የቀድሞ ባልደረባ ዶክተር ኤልሳቤጥ ወልደጊዮርጊስን በስልክ አነጋግሯቸዉ ነበር።

እሸቴ በቀለ

ነጋሽ መሐመድ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.