ኦቦይ አዲሱ ለገሰ በመቐለ ወጣቶቹን ሰብስቦ አባበለ ( ዘውዱ ታደሰ )

ኦቦይ አዲሱ ለገሰ

በሀገር ውስጥ የገጠመን ችግር እንዲሁ በቀላል በተሀድሶ የሚል ስም እምንፈታው አይደለም ጥልቅ መሰረታዊ ስራ ይጠይቀናል ከፊታችን ትልቅ አደጋ እንዳለ ማየቱ መልካም ይመስለኛል እኛን እየተቃወሙን ያሉት ድንጋይ ከመወርወር ጀምሮ መሳሪያ ያነገቡት በእኛው ስርዐት የተፈጠሩ አልያም እኛ ስንገባ ዳዴ የሚሉ ወጣቱ ትውልድ እንደሆነ መገንዘብ አለብን በጥቃቅን እና አነስተኛ አልያም ገንዘብ በማበደር ወደ ስራ እንዲገቡ በማድረግ የምንሻገረው እርቀት ያለ መስሎ አይታየኝም ።
“ለምን ” ብሎ እሚጠይቅ ትውልድ ተፍጥራል ይህ ደግሞ ነገ ምን ሊያስከታ እንደሚችል መገመት ቀላል ይመስለኛል በዛላይ OMN .ESAT .Zሀበሻ እና በብርሀኑ ነጋ እሚመራው አርበኞች ግንቦት 7 የመሳሰሉት ለዘመናት የጥላቻ ፕሮፓጋንዳን ሲነዙ በመቆየታቸው የዲያስፓራው መሰሪ ፓለቲካ ዛሬ በሀገር ቤት ነፍስ ዘርቶ መራመድ የጀመረበት ወቅት ላይ እንገኛለን ይህንን ከእንጭጩ ካልቀጨነው ለስርዐቱም ይሁን ለሀገሪቱ እንዲሁም ለእኛ አደጋው የከፍ ይሆናል ጠባብነት ትምክት ጎጠኝነት ለአንዴ እና ለመጨረሻ ግዜ አከርካሪያቸውን መስበር ይገባናል ።
እናንተን የመሳሰሉ ተስፈኛ ወጣቶች ይዘን ማንቀላፍት የለብንም ኢህአዴግ ከእንግዲህ በሀላ የማንም አይደለም አሁን እዚህ አዳራሽ ውስጥ ያላችሁ ወጣቶች ብቻ ነው ይህን ስርዐት ወደፊት ማስቀጠል ምትችሉት በመተካካት ፓሊሲያችን እናንተ እና እናንተ ብቻ ናችሁ
የመጠብንን ችግር በጋራ መክተን ዳግም በሌላ መድረክ እንደምንገናኝ ተስፍ አለኝ ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.