በእነ መላኩ ፈንታ አንደኛው የክስ መዝገብ ላይ ብይን ተሰጠ

BBN February 20/2017
የቀድሞ የገቢዎች እና ጉምሩክ ባለስልጣን ኃላፊዎች በአንደኛው የክስ መዝገባቸው እንዲከላከሉ ብይን ተሰጠ፡፡ ብይን የተሰጠው በአቶ መላኩ ፈንታ ስም በተከፈተው የክስ መዝገብ ቁጥር 56 ላይ ሲሆን፣ በዚህ መዝገብም ተከሳሾቹ እንዲከላከሉ ተነግሯቸዋል፡፡ የፌደራል ዓቃቤ ህግ የቀድሞ የገቢዎች እና ጉሙሩክ ኃላፊዎች እና ነጋዴዎች ተባብረው የሙስና ወንጀል ፈጽመዋል ሲል ክስ መመስረቱ ይታወቃል፡፡
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ የወንጀል ችሎት ተካሳሾች እንዲከላከሉ ብይን በሰጠበት የክስ መዝገብ አቶ መላኩ ፈንታና አቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስን ጨምሮ 10 የባለስልጣኑ የቀድሞ የስራ ኃላፊዎች እና ባለሃብቶች ተካትተዋል፡፡ ዓቃቤ ህግ ‹‹አቶ መላኩ ፈንታና አቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስን ጨምሮ ሌሎች የቀድሞ የኢትዮጵያ ገቢዎች እና ጉሙሩክ ባለስልጣን የስራ ኃላፊዎቹ በሚሌ ቅርንጫፍ በኩል ከ2003 እስከ 2005 ድረስ የባለሀብት ኩባንያዎች ዕቃቸውን ሳያስፈትሹ እንዲያስገቡ አድርገዋል፡፡›› የሚል ክስ አቅርቧል፡፡
ዓቃቤ ህግ በከፈተው የሙስና ወንጀል ክስ ላይ፣ ዛሬ የዋለው የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 15ኛ የወንጀል ችሎት ተከሳሾቹ በተከሰሱበት የሙስና ወንጀል ላይ የዓቃቤ ህግን ማስረጃዎች ይከላከሉ ሲል ብይን መስጠቱን መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡ በዚህም መሰረት ፍርድ ቤቱ ከሰኞ የካቲት 20 ቀን 2009 ጀምሮ ተከሳሾቹ መከላከያቸውን እንዲያቀርቡ ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን ለማወቅ ተችሏል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.