ከብዙ ማጉላላት በኋላ ምርጫ ቦርድ ለመኢአድ እና ሰማያዊ አመራሮች እውቅና ሰጠ – ከታምራት ይገዙ

ከብዙ ማጉላላት በኋላ ምርጫ ቦርድ ለመኢአድ እና ሰማያዊ አመራሮች እውቅና ሰጠ የሚለውን ዜና የሚሊዮንች ድምጽ ሲያበስረን ለረጅም ግዜ ይጠበቅ የነበር ዜና በመሆኑ ለመኢአድ እና ሰማያዊ ድርጅት መሪዎች; አባላቶችና በመላው አለም ለምትገኙ የሰላማዊ ትግል ነፋቂዎችና ደጋፊዎች እንኮን ደስ አላችሁ እያልኩ:  በማስተከል ነገ ዛሬ ስይባል በዊጪ አገር የምንገኝ ሰላማዊ ትግልን ናፋቂ ኢትዮጵያዊን ይህንን የሰላማዊ ትግል ከፍጻሜ እንዲደርስ ቆርጠን የምንነሳበት ሰዓት አሁን ነው እላለሁ: እርግጥ ከዚህ ቀደም ሰላማዊ ትግሉ ሞቅ ሲል የኛም ድጋፍ ሞቅ ይላል ሰላማዊ ትግሉ ቀዝቀዝ ሲል የኛም ድጋፍ ከመቀዝቀዝ አልፎ አንገታችንን አቀርቅረን ምን ዓይነት ትግል ነው እያልን በየቤታችን እንጉርጉሮ እንጀምራለን: ይህ ሁሉ የሆንበት ምክንያት  የሄድንበት መንገድ እልህ አስጨራሽና ቡዙ መሰዋትነት ያስከፈለ  በመሆኑ የሁላችንንም ስሜት በትንሹም በትልቁም ቶሎ ስለምነካ ይመስለኛል: :

እርግጥ ነው ሰላማዊ ትግል ከጦርነት ያላነስ መሰዋትነትን ቢጠይቅ ነው እንጂ አያንስም: ምክንያቱም ጦርነት ያወጀ ድርጅት መሞትም ሆነ መግደል ከአላማው እንደ አንዱ አርጎ ስለሚነሳ   ለድል የምንደርሰው እየገደልንም  እየሞተም ነው ብለው ስለሞያስቡ መገዳደልን እንደ ዓላማ አንግበበው ነው የሚጞዙት::

የሰላማዊ ትግል ታጋዮች ግን የሚሞቱበት ዓላማ እንጂ የሚገሉበት ዓላማ የሌላቸውም በመሆኑ እስከ አፍኝጫው ከታጣጠቀ ከአምባገነን መንግስት ጋር  የሚጋፈጡት እስኪሪቢቶና ወረቀት በመያዝ አሊያም እጃቸውን አጣምረው ወደ ላይ በመዘርጋት ነው::           መቼም  ሁሉም እንደሚያውቀው የሰላማዊ ትግልና የመሳሪያ ትግል የሚለያየው እዚህ ላይ ነው: በሌላ በኩል ደሞ እንደ አካሄዱ ሁሉ ውጤቱም የተለያየ ነው:  ለምሳሌ የትጥቅ ትግል ሲጀመር የጦር አበጋዞቹ የሚነግሩን አንድ ዓይነት ነው እሱም የምንዋጋው ህዝብን ነጻ ለማውጣትና ዲሞክራሲ ለመገንባት ነው ይሉናል::

እንደ እውነቱ ከሆነ አፍሪካ ውስጥ በመሳሪያ ትግል መንግስት ለውጦ ትግሉን ሲጀምር ቃል በገባው መሰረት ለህዝቡ ዲሞክራሲ ያመጣ አንድም አይገኝም:  ለዚህም ቡዙ ምክንያቶች ቢኖሩትም እንደዋንኛ የሚታዩት የሚከተሉት ይመስሉኛል : :

1ኛ በጦርነት ትግል ውስጥ የሚሞተው ጠላት ተብሎ የሚፈረጀው የጠላት የጦር ሰራዊት ብቻ ሳይሆን ከራስም በኩል በጦርነቱ አካሄድ ላይ ያልተስማማና ጥያቄ የነሳ የሰራዊቱ አባል በራሱ የጦር አዛዥ ትግሉን ለመቀልበስ ያሴረ ተብሎ ለመቀጣጫ በጦሩ ፍት ይረሸናል ለዚህም እንደ ማሳያ የሚጠቀሰወ በአሁኑ ሰዓት አገር  እየመሩት ያሉት የTPLF አመራሮች ቡዙ የትግራይን ተወላጆችን በመቀጣጫ መልክ የአሞራ ሲሳይ አድርገው ነው ለስልጣን የበቁት ;;

2ኛው ደሞ በዚህ ዓይነት መጠፋፋት መአከላዊውን መንግስት ማሸነፍ ቢቻልም የተመጣበት መንግድ የኛና የነሱ የሚለው አደረጃጀት ስላለው የነሱ የሚላቸውን ከማጥፋት አይመለሱም ለዚህም TPLF እንደ ምሳሌ መውሰድ ይቻላል ምክንያቱም በአፍሪካ በመከላከያ ሐይል ጠንካራ ከሚባሉት አገሮች  መሃከል የአገራችን  የኢትዮጵያ የመከላከያ ሀይል ሲሆን  TPLF ስልጣን ላይ ሲወጣ የመጀመሪያው ስራ አድርጎ የወሰደው ከንጉሰ ነገስቱ ግዜ ጀምሮ የነበረውንና ከሁለት መቶ ሺ በላይ  የነበረ የመከላከያ ሰራዊ የደርግ ሰራዊት በማለት መሳሪያቸውን ተቀብሉ ካበቃ ቦሃላ ያን ሁሉ ሰራዊት የመንገድ ላይ ለማኝ ነበር ያደረገው::  TPLF ፎች በዚህ መልክ ስልጣን ላይም ከወጡ ቦሃላ በሰሩት ስራ ሰውን አይደለም የራሳቸውን ጥላ እንኮን አለማመን የደረሱት :: ይህንን ለማወቅ ደሞ ቡዙ ምርምር አያስፈልገውም  በአገራችን የመከላከያ ታሪክ ውስጥ ባለፉት ሀያ አመታት ውስጥ ከዘጠና ፐርስንት በላይ ከፍተኛ ሹማምንቶቹ እነማን እንደሆኑ ጸሃይ የሞቀው እውነታ ነው::

በሌላ በኩል  በትጥቅ ትግል የኢህአዴግ መንግስት እንጥላለን የሚሉት ወንድሞቻችን በለስ ቀንቶቸው ቢያሸንፉ እንኮን  አንድ ሰው ሰውኛው ስናበው ከነሱ በፊት እንደነበሩ ላለሞሆናቸው ምንም ማረጋገጫ አይኖርም: ምክንያቱም እነሱም የኛና የነሱ በሚለው መረሆ መሰረት  የአንድ አገር ዜጋ የሆኑትን ወንድም አማቾችና  እህት አማቾች  የሆኑትን የጦር ሰራዊቶችን በማገዳደል ስለ ሆነ ለድል የደረሱት::  በእንደዚህ ዓይነት የተግኘ ድል   እንዴት  ሆኖ  ነው ሰላምና ዲሞክራሲ  ያመጣል ተብሎ የሚለፈፈው?  እነዚህ ወንድሞቻችን እያሉት ያሉት ሰው መሆናችንን እርሱትና እንደ መላእክት ተቀበሉን ማለት ነው የቀራቸው: በሌላው በኩል “ሰው መላእክት ቢሆን መንግስት አያስፈልግም ነበር” የሚለውን አባባል የዘነጉት ይመስላል::  በተጨማሪ በትጥቅ ትግል የኢህአዴግ መንግስት እንጥላለን የሚሉት ወንድሞቻችን የዘነጉት ነገር ቢኖር በትጥቅ ትግል የኢህአዴግ መንግስት  ቢያሸንፉ እንኮን ከተሸናፊው ጎራ በኩል በመቶዎች የሚቆጠሩ የጦር ሰራዊቶች ሸሽተው ከጎረቤት አገር ምናልባት ኤርትራ ቢገቡና  ጦር ቢሰብቁ: በጦርንነት አሸንፈን  ሰላምና ዲሞክራሲ እነመጣለን  ያሉት ሁሉ ከንቱ ሆኖ ቀርቶ ሌላ ዙር ጦርነት ውስጥ ሳይወዱ በግድ መግባታቸው አይቀሬ ነው:  በተጨማሪ እንደ በፊተኞቹ የራሳቸውን ጥላ መሸሽ እንዳለ ሆኖ ማለት ነው:: ለምን ቢባል  የመጡበት መንገድ  የአንድ ሀገርን ህዝብ የኛና የነሱ በሚለው መሮሆ  ነበርና እየተገዳደሉት  የመጡት::  በእኔ እምነት ከእንደዚህ ዓይነት የጦርነት አባዜ ሊወጣ የሚቻለው የሚከፈለውን ሁሉ መሰዋትነት ሁሉ ተከፍሎ በሰላማዊ ትግል  ነው ባይ ነኝ::  እርግጥ ነው የኢህአዴግ መሪዎች የሚጠሉትና የሚፈሩት ነገር ቢኖር   ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ የሚነሳውን ህዝብና ሰላማዊ ትግልን ነው: እነዚህን ሁለት ነገሮች ከሁሉ በላይ እንደሚያስፈሩት ማስረጃ ማቅረብ ካስፈለገ::

(ሀ) የቀድሞው ጠ/ሚ አቶ መለስ ዜናዊ  ሃገራችንን ኢትዮጵያ በመሩባቸው ዓመታት ሁሉ አውቀው አይደላም ተሳስተው አንኮን አገራችን ኢትዮጵያ ሳይሉ ነው ለሶስት ክንድ መሬት የበቁት: እርግጥ ነው በሳቸው ሂሊና ኢትዮጵያ የሚለውን ቃል ከአንደበታቸው ከወጣ እንድ ብረት ሊያቀልጣቸው እንደሚችል ስለሚያውቁት ያንን ኢትዮጵያ የሚለውን ቃል ከሃያ ዓመት በላይ ሳይጠሩ ነበር አገራችንን መርተው ይህችን ዓለም የተሰነበቱት:: ሌላው ደሞ በአሁኑ ሰዓት ላይ ስልጣን ላይ ያሉት መሪዎቻችን ኢትዮጵያዊ ነት ምን ያህል እንደ ሚያስፈራቸው ለማወቅ በተላያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ” እኛ ኢትዮጵያዊ ነን እንጂ የሻቢያ ተላላኪዎች አይደላንም” በሌላ በኩል ደሞ “የኦሮሞ ወንድሞቻችን ደም ያኛም ደም ነው::” የሚለውን ሲሰሙ የኢህአዴግ ተወካዮች የምናገሩትን እንኮን የሚያውቁ ሆነው አልተገኙም የቀድሞው የኮምንኬሽን ምንስትር የነበሩት ከተናገርት ውስጥ ” ይህ ምን ዓይነት ሞዋርትነው” የሚለውና “እሳትና ጭድ እንዴት ነው እንድ የሚሆኑት” የሚሉት ቃላት ከአንድ ሚንስቴር መስማት ኢትዮጵያዊነትን ሲሰሙ እራሳቸውን እንደሚያስታቸው አንዱ ምስክ ነው ባይ ነኝ::

(ለ) ሌላው የኢህአዴግ መንግስት የሚፈራው ሰላማዊውን ትግል ነው አሁንም ማስረጃም ከስፈለግ ሞቹ ጠ/ሚ አቶ መለስ ዘናዊ በ2005ዓ/ም አገራዊ ምርጫ ወቅት በአንደበታቸው በሰላማዊ ትግልና በመርጫ ኢህአዴግ የሚያሸንፍ ተፎካካሪ ድርጅት ካለ ግማሽ መንግድ ሄጄ እቀበለዋለው እንዳላሉ ሁሉ ከምርጫ 2005   ምሽት ጀምሮ ሰላማዊ ትግሉንና ታጋዮቹን በምን ሰበብና እንዴት እንደሚያጠፉቸው  ነበር  በቀንም በሌሊትም የሚያስቡት የነበረውና ያሰቡትንም ያሳኩት::   ከሳቸው እርፍት ቦሃላ ስልጣን ላይ የመጡት ጠ/ሚ ሆኑ ሌሎች ሹሞኞች ሌት ተቀን ይሰሩት የነበረው ሰላማዊ ትግሉ እንዴት እንደሚጠፋ ነበር ሌላው ቢቀር ያለፉት ሁለት ሶስት ዓመታቶች የተቀሰቀሱት ህዝባዊ አመጾች ምን ያህል አንደረበሻቸውና እነሱም በተቻለ አቅማቸው ሁሉ ሊቆጣጠሩት  የሚችሉባቸውን ዘዴ ሁሉ ለማደረግ ሲሞክሩ ነው  እያየነው ያለው::

በአጠቃላይ የኢህአዴግን አካሄድ ስመለከተው ከጎረቤት አገር ከኤርትራ በኩል የሚመጣ ሃይል ለስልጣኑ እንደ ማያስፈራው እርግጠኛ ሆኖ መናገር ይቻላል ባይ ነኝ ለዚህም በማስረጃ ሊቀርብ የሚችለው  አቶ ነአምን ዘላቀ የግንቦት ሰባት ከፍተኛ አመራር ባለፈው ሰሞን በአትላንታው ስብሰባ አድርገው በነበረበት ወቅት እንዲህ ብለው ነበር ” በአሁኑ ወቅት ከሕወሓት መንግስት ጋር እየተደረገ ያለው ትግል ላይ ድርጅታችን አርበኞች ግንቦት 7 በክፍለ ጦር፣ በብርጌድና በሬጅመንት አቋም የተደራጀ  በከባድ መሣሪያዎችን የተቀነባበረ ትግል ለማድረግ በአሁኑ ወቅት አቅም እንደሌለውና በተጨማሪም በዚያ አካባቢ ያለው የጂኦ ፖለቲክስ በራሱ  ችግር እንደሆነ አስርግጠው ነበር የተናገሩት”:: ነገር ግን የኢህአዴግ መንግስት ላለፈው አራት ዓመት የሚያወጣውን መግላጫ ከተመለከትን ቢያንስ በየስድስት ወሩ የሚያውጣው መግለጫ ጸረ ሰላም ሃይሎች በሻቢያ መንግስት እየታገዙ ሰላማችንን ላማደፍረስ ድንበር ጥሰው እየገቡ ነው በሚል የውሸት ዜና ህዝብንና ሀገርን ሲያሸብር ነው የከረመው  ይህም አባባሉ ” ላም  ባልዋለበት ኩበት ለቃማ እንደሚሉት” መሆኑ ነው:: እውነቱ ግን አቶ ነአምን የነገሩ ነው ድርጅታቸው አርበኞች ግንቦት 7 በክፍለ ጦር፣ በብርጌድና በሬጅመንት አቋም የተደራጀ  በከባድ መሣሪያዎችን የተቀነባበረ ትግል ለማድረግና  የኢህአዴግን መንግስት ለመጣል አቅሙም ጉልበቱም እንደሌለውና በአስቸኮይ አቅጣጫ መለውጥ እንዳለባቸው ነው አበክረው ለታዳሚው የተናገሩት: በዚህ አነጋገራቸው አቶ ነእምን ዘለቀ ካፈርኩ አይመልሰኝ የሚባለውን የፖለቲካ  መረሆ በድፍረት ሰብረው  የወጡና ድርጅታቸውን በሚገባ የገመገሙና ሰው በመሆናቸው: ሊሎች እርምጃዎችንም እንዲወስዱ የሚበረታቱ ሰው ናቸው::

በዚህ አጋጣሚ ላስተላልፍ የምፈልገው መልእክት ቢኖር የሚከተለው ነው:  ይህውም ከሀገራችን ውጪ በመላው አለም የምንኖር ኢትዮጵያውያን በተለይም የሰላማዊ ትግል ናፋቂዎች የሁንን ሁሉ አገራችን ኢትዮጵያ ከአምባገነን ስራዓትና ከጦርነት አዙሪት መውጣት ያለባት ወቅት አሁን በመሆኑ በአገር ቤት ሆነው ሰላማዊ ትግል ለሚያደርጉት ድርጅቶች አለንላችሁ የምንላቸው ግዜው አሁን ነው ባይነኝ: ስለሆነም በመላው ዓለም የምንገኝ የሰላማዊ ትግል ደጋፊዎች በተቻለው ፍጥነት በሚሊዮንች ድምጽ ስር ተሰባስበን የአገር ቤቱን ሰላማዊ ትግል በተቀላጠፈ መንግድ  በመርዳት ኢትዮጵያ ውስጥ የዲሞክራሲ ሀሁ እንዲጀመር ጠንክረን መስራት አለብን እላለው::

በሌላ በኩል ይህንን የአገር ቤቱን ትግል ለመርዳት በሚሊዮንች ድምጽ ስር መሰባሰብ አለብን የምልበት ዋና ምክንያት እንደሚታወቀው  በ2015 ዓ/ም በተደርገው ሀገራዊ ምርጫ ላይ እንድነት ፓሪቲ (U D J) ከሌሎች ተፎካካሪ ድርጅቶች በገንዘብ አቅምም ሆነ በቁሳቁስ ጠንክሮ እንዲወጣ ያደረገው  በሚሊዮንች ድምጽ ስር የተሰባሰበው ግብረ ሀይል ነበር::  እንደ እውነቱ ከሆነ በመላው አገሪቶ  ውስጥ ቢሮ ከፍቶና በተለያዩ ትላልቅ ከተሞች ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍችን እንዲያደርግ ከፍተኛ ገንዘብ እያሰባሰበ ይልክ የነበረው በሚሊዮንች ድምጽ የተሰባሰበው ግብረ ሀይል ነበር::   በሌላ በኩል ደሞ የአንድነት ፓሪቲ የራሱ ድምጽ እንዲኖረው ፍኖተ ነጻነት የሚል ጋዜጣን የማተም አቅም እንዲኖረው ማተሚያ ማሽኑን ገዝቶ የላከው በሰሜን አሜሪካ በሚሊዮንች ድምጽ የተሰባሰበው ግብረሃይል ነበር:: ይህም ግብረ ሃይል የተሰባሰበው ከአሜሪክ; ከካነዳና ከአሮፓ ነበረ::  ያንን ያደርጉ የነበሩ ወንድሞችና እህቶች አሁንም አሉ ወደ ፊትም ይኖራሉ ይህንን ሰላማዊ ትግልም ከመደገፍ ወደ ሓላ አይሉም የሚል ጽኑ እምነት አለኝ : የሚያስፈልገው ነገር ቢኖር ይህን ስብስብ በቶሎ የሚሰባሰብበትን መንገድ ማመቻቸት ብቻ ነው: :  ይህኘውን ስብስብ ትንሽ ለየት ሊልና የበለጠ ጥንቃቄ ሊደረግበት ይገባል እላለሁ ምክንያቱም  በእኔ እምነት በግልጽነትና በድፍረት ልንናገረ የሚገባው ነገር ሊኖር ይገባል ይህውም   የኢህአዴግ መንግስት በአገር ቤት ባሉት ተፎካካሪ ድርጅቶች ውስጥ እየገባ እስነዋሪ ነገሮችን እንደሚያደርገው ሁሉ የአንድነት ደጋፊዎች ነን በማለት የግንቦት ሰባት አባላቶችም አንድነት ውስጥ ( U D J) ውስጥ በመግባት የኢህአዴ ዓይት አስነዋሪ ተግባር ይፈስሙ እንደነበር እኔ ምስክር ነኝ: ሌላ ሰውም በአንድ ወቅት ጽሁፉ ” አሁንስ ግንቦት ሰባት የድሮውን EPRP” ሆነ ብሎ ነበር::

በአሁን ሰአት ግን የግንቦት ሰባት አመራሮችም ሆኑ አባላቶች ካለፈው ስህተታቸው ተምረውና የሚሄዱበትም የትግል መስመር እንደማያዋጣ ተገንዝበውና የከፍተኛ አመራራቸውን የአቶ ነዓምንን ቃልም በመስማት ከአሁን ቦሃላ ያላቸውን እውቀትም; ጉልበትም ሆነ የገንዘብ ሀይል ወደ ሰላማዊው ትግል ለውጥው በሙሉ ሀይላቸው ሰላማዊ ሀይሉን ቢቀላቀሉ የኢትዮጵያንና የኢትዮጵያኖችን የነጻነት ትንሳኤ ሁላችንም ለማየት እንበቃለን ማለት ነው::

በመጨረሻም የዝህን ትግል አካሄድ ማድረግ ያለብን እንደ እውነቱ ከሆነ በእሰር ቤት እየማቀቀ ያለውና በአንደበቱ እንደተናገረው “እኔ በሰላማዊ ትግል የቆረብኩኝ ሰላማዊ ታጋይ  ነኝ እያለ በሽበርትኝነት ተከሶ የእዲሜ ለክ ብይን የተበየነበት አቶ አንዱዓለም አራጌ በመጽሃፉ እንዳስተማረን ያልተሄደበት መንገድ መጀመር አለብን:: ”  ሌላው በሰላማዊ መንገድ የቆረበውና የአንድነት የ(U D J) ህዝብ ግኑኝነትና በ2015ዓ/ም በሚሊዮንች ድምጽ ስም በተለያዩ ትላልቅ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ ይመራ የነበረው ወንድማችን አቶ ሀፍታሙ አያሌው በአሁኑ ሰዓት  ለህክምና አሜሪካ የሚገኝ ሲሆን ህክምናውን በፈጣሪ ርዳታ በሚገባ ካጠናቀቀና በጥሩ ሁኔታ ካረፈ ቦሓላ በተለያዩ የአሜሩካ ከተሞች ; በተለያዩ የካናዳ ከትሞች ከተቻለውም በተለያዩ አውሮፓ ከተሞችና እንዲሁም በአፍሪካ:  እየተዘዋወር ወንድሞቹና እህቶቹ እንዲሁም እሱ እራሱ ቡዙ መሰዋትነትን የከፈለበትን ሰላማዊ ትግል ጥንክሮ እንዲወጣና በሚሊዮንች ድምጽ ስምም ያገር ቤቱን  ሰላማዊ ትግል በእውቀት; በገንዘብና በጉልበት ሊረዱ የሚችሉትን ሁሉ  እንደሚያሰባስብ   ከፍተኛ እምነት አለኝ:: በተለይም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሰላማዊውን ትግል መርዳት እየፈለጉ በተለያየ ምክንያት ከመርዳት የተቆጠቡ (ሳይለንት ማጆሪቲ) የሚባሉትን ወደ ሰላማዊ ትግሉ እንዲገቡና ሰላማዊውን ትግል እንዲረዱ እንደሚያደርግ አልጠራጠርም ዋናው ነገር አምላክ ጨርሶ ይማራው: እንጂ::

በሌላ በኩል አገራችን ኢትዮጵያ ከአምባገነን ስራአት ከወጣችና ህዝቦቾ በሰላም; በፍቅርና በዲሞክራሲ መኖር ከጀመሩ አምላክ በቸርነቱ በውጪው  አለም ተበትነን የምንኖረውን ኢትዮጵያኖች ስደታችንን ከባረከልንና በሰላምና በፍቅር በተሰደድንበት አገር መኖር ከጀመርን:  አገራችን ኢትዮጵያ አንድ ቀን አዋን አንድ ቀን በፈጣሪ ቸርነትና  በልጆቾ ጥንካሬ  አፍሪካ ውስጥ የምትገኝ እስራኤልን (Israel )ትሆናለች የሚል እምነት አለኝ::

ድል ለህዝባችን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.