አሳዛኝ ዜና፤ ሰላማዊ የነጻነት ታጋይ ወጣት ዘመኔ ጌጤ በደኅንነት ታፍኖ የደረሰበት እንደማይታወቅ ተገለጸ – – ከሙሉቀን ተስፋው

ሰላማዊው የነጻነት ታጋይ ወጣት ዘመነ ጌጤ ከጥር 22 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ ወደ ቤቱ እንዳልተመለሰ ቤተሰቦቹ ተናገሩ፡፡ ዘመነ ጌጤ በሚያዚያ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. በአዲስ አበባ በአይሲስን ለመቃወም በተጠራው ስብሰባ ሽብር ለመፍጠር አሲረሃል ተብሎ ለአንድ ዓመት ያክል በማዕከላዊ ታስሮ የተፈታ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ የመኢአድ የወጣቶች ክንፍ ኃላፊ በመሆን አግልግሏል፡፡

የአቶ ዘመኔ ጌጤ ቤተሰቦች እንደሚሉት ጥር 22 ቀን 2009 ዓ.ም. ጎንደር ደርሼ እመለሳለሁ በማለት ትንሽ የጉዞ ቦርሳ በመያዝ ከቤቱ እንደወጣ እንዳልተመለሰ ነው የተናገሩት፡፡ ከጎንደር አካባቢ ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው ከጓደኛው ወጣት ክንዱ ጋር በደኅንነት ጥር 24 ቀን 2009 ዓ.ም. ጎንደር ከተማ ውስጥ መታፈናቸውን ነው፡፡
እነዘመነ ጌጤና ክንዱ በደኅንነት ታፍነው ከተወሰዱ በኋላ የደረሱበት እንደማይታወቅ ነው የተነገረው፡፡ የዘመነ ጌጤ ቤተሰቦች ወንድማቸውን የት ብለን እንደምንፈልግም አላወቅንም ሲሉ በሀዘን አስታውቀዋል፡፡ ወጣት ዘመነና ወጣት ክንዱ ወደ ማዕከላዊ ወይም ወደ ትግራይ ሊወሰዱ እንደሚችሉ ጥርጣሪያቸውን መረጃውን የሰጡን ሰዎች ገልጸዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.