አዲረመጥ ዛሬ የነዋሪዎቿን ጨፍጫፊ አባይ ወልዱን ቄጤማ ጎዝጉዛ፣ የትግራይ ከበሮ እየመታች፣ ፈንድሻ እየረጨች እንድትቀበልአዲረመጥ ዛሬ የነዋሪዎቿን ጨፍጫፊ አባይ ወልዱን ቄጤማ ጎዝጉዛ፣ የትግራይ ከበሮ እየመታች፣ ፈንድሻ እየረጨች እንድትቀበል አምስት ኦራል መኪና ሙሉ ሰራዊት ቀደም ተብሎ ተልኳል። ህዝቡ በሙሉ በነቂስ ወጥቶ እየዘፈኑ አባይ ወልዱን በመቀበል ትግሬ ነን፣ እንኳንም እያሰርክ፣ እየገረፍክ፣ እየገደልክ ገዛኽን በሉ ተብሏል።
አየተገረፉ ፣ እየተራቡ የሚዘፍኑበት ዘመነ ወያኔ እንዲያበቃ ህዝብ አንድ ሆኖ እንዳይነሳ ሳይገድል ጎፈሬው በዛ ፣ የማይጨበጥ ፣የማይዳሰስ የድል ተስፈ ሰፋሪው ምላሱ ረዘመ፣ መጠላለፍ በዛ ፣የኢትዮጵያ ህዝብ መከራው አላበቃም አለ።
አዲረመጽ፣ በይ ከበሮሽን ይዘሽ ” አማራ ገዳይ ፣እንደ ፋሽሽት ኢጣሊያ ግዛን” እያልሽ እንባሽን እያዘራሽ ግን የተዘጋጄልሽን የመቀሌ ከበሮ ይዘሽ ወስከንቢያሽን እራስሽ ላይ አድርገሽ ተሽከርከሪ።
ብርታት እና መጽናናት ለአዲረመጽ ህዝብ እመኛለሁ፣
ልያ ፋንታ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.