ዞን ዘጠኞችና ጋዜጠኞች በተገኙበት የሰማያዊ ፓርቲ መሰረታዊ መልሶችን ሰጠ – የሚሊዮኖች ድምጽ

“መሰረታዊ መልሶች!” በሚል የሰማያዊ ፓርቲ የብሄራዊ ምክር ቤት ሰብሳቢና የሕግ ባለሞያው አቶ ይድነቃቸው ከበደ ዛሬ የካቲቲ 19 ቀን ፓርቲው በውስጣዊ ጉዳዮች ዙሪያ በጽ/ቤቱ  ስላደረገ ገለጻ  ማብራሪይ ሰጥተዋል።

የቀድሞ የፓርቲው ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል የፓርቲው የበላይ አካል የሆነውን የጠቅላላ ጉባዬ ውሳኔ አልቀበልም በማለት በተለያዩ ገፆች ላይ በመውጣት፣ “አሁንም የፓርቲው ሊቀመንበር እኔ ነኝ” እያሉ  የፓርቲውን እባላትና ደጋፊዎች ግራ በማጋባት ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል።
ከዛሬ ነገ የፓርቲውን ደንብ አክብረው ወደትግል እንዲቀላቀሉ ቢጠበቁም፣ በብዙ ወገኖችም ትልቅ ተማጽኖ ቢደረግላቸውም፣  “ሊቀመንበር ካልሆንኩኝ ትግሉ ዋጋ የለውም” በማለት ፣ በግል የሚያውቁዋቸዉን ጋዜጠኞች ጋር በመደወልና  ቃለምልልስ በማድረግ  የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችን “ወያኔዎች ናቸው” ብሎ በመክሰስ አፍራሽ ተግባራታ ላይ እየተሰማሩ ነው።

“ነገሮች  በሂደት ሊሰተካከሉ ይችላሉ” በሚል ተስፋ ዝምታን መርጦ የነበረው የፓርቲው አመራር በድርጅቱ የዉስጥ ጉዳይ ያለውን ብዥታ ለማጥራት ነበር ዛሬ ገለጻዎች ያደረገው። የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ፣ የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን፣ እንደ ዶር ያእቆብ ሃይለማሪያም ያሉ አንጋፋ ኢትዮጵያዉያን የተገኙ ሲሆን ለተነሱ የተለያዩ ጥያቄዎችን ግልጽነት ባለው መልኩ ማብራሪያዎች ተሰጥተዋል።

ኢንጂነር ይልቃል አሁን ካለው አመራር ጋር “ማንም አባል” የለም ብለው ከሰው የነበረ ቢሆንም በዛሬ የሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት፣ እንደ አቶ ይድነቃቸው ከበደ የምክር ቤቱ ሰብሳቢ፣ አቶ አበራ ገብሩ የኦዲት ኮሚሽን ሰብሳቢ፣ ብሌን መስፍን፣ ሃና ዋለልኝ፣ አበባ አካሉ፣  ሰለሞን ተሰማ፣ አሮን ሰይፉ ..የመሳሰሉ ከፍተኛ አመራር አባላት ተገኝተዋል።

በዛሬው ስብሰባ ዙሪያ  የሰማያዊ ፓርቲ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ይድነቃቸው የሚከተለውን አቅርበዋል፡
=============================
በዛሬው ዕለት፣ የካቲት 19 ቀን 2009 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 እስከ 6፡00 ሰዓት ፤ በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት የፓርቲው ውስጣዊ ጉዳይ አስመልክቶ ገለፃ ተደረገ።

” ብዙ እየተባለ እና እየተወራ ነው። በሚነገረው ልክ ምላሽ እንስጥ ብንል ትላንት የነበርን ወዳጅነት እና ጓዳዊ ግንኙነት ላለማበላሽት ፣ምን አልባትም አሁን ላይ መለስ ብለን የተሻለ እድል ካላ በሚል የቀናነት መንፈስ በዝምታ ነገሮችን ለማየት ሞክረናል። ይሁን እንጂ የመጀመሪያ ቃል ኪዳናችን (የጋራ አመራር፣ ግልፅነት እና ተጠያቂነት ከምንም በላይ ለፓርቲ ደንብ እና መርህ መገዛት) ሰብረው፤ ባልሆነው ነገር ብዙ እየተፃፈ እና እየተባለ ነው። የሚባለው እና የሚፃፈው ነገር ከዚህ በበለጠ ሰዎችን ማሳሳት ስለሌለበት ፤ በፓርቲያችን ውስጣዊ ጉዳይ ከዚህ በኋላ ተገቢውን ምላሽ እንሰጣለን።” በማለት አቶ የሺዋስ አሰፋ ንግግር አድርጓል ።

በእለቱ የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን እና ጋዜጦች ፣ የፓርቲው የብሔራዊ ምክር ቤት ፣የኦዲት እና ምርመራ ኮሚሽን ተጠሪዎች ፣የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት እና የሽምግልና ጥረት ሲያደርጉ የነበሩ ተገኝቷል።

በነበረው ገለፃ እና ማብራሪያ ሰፊ ሽፋን አግኝቶ ውይይት የተደረገበት፣
አቶ የሺዋስ አሰፋ በሊቀመንበርነት የተመረጡበት የጠቅላላ ጉባኤ ኮረም (ምላዕተ ጉባኤ) ፣ ለጉባኤው ወጪ የተደረገው ገንዝብ ምንጭ ፣ በፓርቲው ውስጥ ይታይ የነበረው የገንዘብ ምዝበራ በተመለከተ ፣ ተፈጥሮ የነበረው ችግር ለመፍታት በብሔራዊ ምክር ቤቱ ይደረግ የነበረው ጥረት እና መሰል ጉዳዮችን አስመልክቶ ማብራሪያ እና ገለፃ የተደረገ ሲሆን። በዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማርያም ይመራ የነበረው የአሸማጋይ ቡድን በመገኘት ጥያቄዎችን በመጠየቅ ተሳትፎ አድርጓል ።

ጦማሪያን እና ጋዜጠኞች ከገለፃው እና ከማብራሪያው እንዲሁም አሉን ባሉን መረጃ መሠረት ፤ጥያቄዎች እና አሰተያየታቸው ያቀረቡ ሲሆን ፤ የሚመለከታቸው አካላት ተገቢውን ምላሽ ሰጥቷል። ጦማሪያን እና ጋዜጠኞች የቀረበላቸውን ገለፃ መሠረት በማድረግ የራሳቸውን ግንዛቤ እንዳገኙ ለማወቅ ተችሏል ።

በተጨማሪ በመረጃ እና በእውነት ላይ የተመሰረት ሃቅ በመሞርከዝ፣ ከዚህ በኋል የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት አስፈላጊ ናቸው ብሎ የሚያምናቸውን መረጃዎችን ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ በእለቱ ተገልፃል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.