ዘመቻ አድዋ! (ፈትለ እና ወርቀ)  – አስራት አብርሃም

አስራት አብርሃም
አስራት አብርሃም

ፈትለ እና ወርቀ የተንቤን ገበሬዎች ናቸው። ሁለቱም አድዋ ዘምተዋል፣ ፈትለ እዚያ ሲሰዋ፣ ወርቀ በህይወት ተመልሰዋል። እንዴት ሊዘምንቱ እንደቻሉ እንዲህ በምናባዊ ወግ አምጥቼዋለሁ።

ወርቀ፦ “ደጃዝማች ‘ለዘመቻ ተዘጋጁ’ ብለዋል።”

ፈትለ፦ “ወየት ሊዘምቱ ነው?”

ወርቀ፦ “አድዋ! ጥሊያን የሚባል ጠላት ባህር ተሻግሮ መጥተዋል አሉ።”

ፈትለ፦  “እንዴት ያለ ነው ይሄ ጥሊያን  ደሞ? እንደ ድርቡሽ ነው?”

ወርቀ፦ “አይደለም እንደ ቱርክ ያለ ሳይሆን አይቀርም፣ ‘ኃይማኖቱ ግን ኮቶሊክ ነው’ ተብለዋል።”

ፈትለ፦ “ኮቶሊክ?! እግዚኦ መሀረነ ክርስቶስ! ታዲያ እኛ ብቻችን እንችለዋለን?” አለ በእጁ እያማተበ።

ወርቀ ፦ “ኧረ ንጉሰ ነገስቱ ራሳቸው ጦራቸውን ይዘው መጥተዋል ነው የሚባለው፣ ጦጲያ ሙሉ ነው

የተሰፈው አሉ። ራስ አሉላም፣ ራስ መንገሻም አብራችው ናቸው።”

ፈትለ፦ “አፄ ዮሃንስ?!”

ወርቀ፦ “ምን ሆነሃል አንተዬ፣ አፄ ዮሃንስማ መተማ ሲዋጉ ድርቡሽ ገደላቸውማ አይደለ! አፄ ምኒልክ ናቸው እንጂ!”

ፈትለ፦ “እንዲያ ነው?! ደግ። እንዘምታለን እንግዲያውስ ። ወለተኪዳንን ስንቅ እንድታዘገጃጅ አሁኑኑ ነግራታለሁ፣ የአጥቢያ ኮከቡ ብቅ ሲል፣ መጥተህ ጥራኝ፣ ፀሐዩ ሳይበረታ መገስገስ አለብን፤ አለ” የሕዳር ፅዮን አክሱም ሊሳለም ሄዶ ያያቸውን የአድዋ ተራሮች በምናቡ እያሰበ።

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.