ሰበር ዜና – ሁለት የኢትዮጵያ አየር ሀይል ኤም አይ 35 ሄሊኮፕተር አብራሪዎች የሚያበሩትን ሄሊኮፕተር ይዘው ጠፉ

 hqdefaultሁለት የኢትዮጵያ አየር ሀይል ኤም አይ 35 ሄሊኮፕተር አብራሪዎች የሚያበሩትን ሄሊኮፕተር ይዘው ጠፉ።የት እንደገቡ እስካሁን አልታወቀም።
ለኢሳት በደረሰው መረጃ የ ኤም አይ 35 ተዋጊ ሄሊኮፕተር አብራሪዎቹ ሻምበል ሳሙ ኤል ግደይ እና መቶ አለቃ ቢልልኝ መኮንን ትናንት ጧት ለልምምድ እንደወጡ ነው ጠፍተው የቀሩት።
አብራሪዎቹ ከ 30 ደቂቃ በላይ እንዲቆዩ ከማይፈቀድላቸው የበረራ ራዲየስ በመውጣት የሚያበሯቸውን ተዋጊ ሄሊኮፕተሮች ይዘው መጥፋታቸው ተረጋግጧል።
ይህ ሪፖርት እስከተጠናቀረበት ድረስ አብራሪዎች የት እንዳሉ አልታወቀም።
ሁለቱ ከፍተኛ የ ኢትዮጵያ አየር ሀይል አብራሪዎች በስልጣን ላይ ያለውን ስር ዓት በመክዳት ከጎረቤት ሀገሮች በአንድኛቸው ሳያርፉ እንዳልቀረ ግምት አለ።
ኢሳት ዜና