በአማራ ክልል በተለያዩ ዞኖችና ወረዳዎች የተጀመረው የመምህራን የስራ ማቆም አድማ እንደቀጠለ ነው – ነገረ ኢትዮጵያ

ብዛት ያላቸው መምህራን ታስረዋል በእስራቱ ሴቶችም ይገኙበታል፡፡

(በሰማያዊ ብሄራዊ ሸንጎ የህዝብ ግንኙነት ንዑስ ኮሚቴ)

ለመንግስት ሰራተኞች የተደረገው ሃገራዊ የደመወዝ ጭማሪ መምህራንን አለማካተቱ ተገቢ አይደለም በማለት የተነሳው የመምህራን የስራ ማቆም አድማ አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡በአንዳንድ ወረዳዎች ከሶስት ቀናት በፊት የተጀመረ ሲሆን ተቃውሞውን በሌሎች ወረዳዎች የሚገኙ መምህራን በመቀላቀላቸው በክልሉ በመምህራን ላይ እስራትና ማዋከብ እየደረሰባቸው መሆኑን ምንጮቻች ገልጸዋል፡፡

በምዕራብ ጎጃም ዞን በደጋ ዳሞት ፣በቋሪት፣በደንበጫ፣በአዴት፤በጎንጅ ቆለላ ወረዳዎች የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸውንና መምህራንም እየታሰሩ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡በዳጋ ዳሞት ወረዳ ከሃያ በላይ መምህራን በወረዳው ከሚገኙ የተላያዩ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም በአዴት 7 መምህራን መታሰራቸውን ምንጮች ገልፀዋል፡፡

የስራ ማቆም አድማውን በምስራቅ ጎጃም ዞን እነማይ/ብቸና/፣እነብሴ ሳር ምድር /መርጦ ለማሪያም/፣ስናን፣ሁለት እጁ እነሴ/ሞጣ/ ወረዳ የሚገኙ መምህራን መቀላቀላቸውንና መምህራንም እየታሰሩ መሆኑን ምንጮች ገልፀዋል፡፡በብቸና ከተማ በላይ ዘለቀ መሰናዶ ትምህርት ቤት መምህራን በጋራ ቃለ ጉባዬ በመያዝ አድማውን ማድረጋቸውንና በመርጦ ለማሪያም 18 መምህራን መታሰራቸውን ሌሎችም ከፍተኛ ማዋከብ እየደረሰባቸው መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡በደብረ ወርቅ ከተማ በደብረ ወርቅ 2ኛና መሰናዶ ትምህርት ቤት የተጀመረው የስራ ማቆም አድማ ሶስተኛ ቀኑን የያዘ ሲሆን አስካሁን ድረስ አራት ወንድና ሁለት ሴት መምህራን መታሰራቸውን ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.