ከሸዋ አርበኞች የተላለፈ መልዕክት፤ የጥሪ ወረቀቶች በምንጃር ተበትነዋል – ሙሉቀን ተስፋው

አስቸኳይ ወገናዊ ጥሪ ለምንጃር ሸንኮራ ህዝብ በሙሉ

‹‹ ሸዋ ያላመጠውን በአመቱ ይውጣል›› ይባላል፡፡

ያው እንደሚታወቀው ወያኔ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ በአጠቃላይ በተለይ ደግሞ በዐማራው ህዝብ ላይ እጅግ ዘግናኝ ሰቆቃ እየፈጸመ መሆኑ የአደባባይ ሀቅ ነው፡፡
ወያኔ ዛሬ ለተቆናጠጠው ስልጣን ያበቃው ጀግናው የዐማራ ህዝብ ቢሆንም ቅሉ በምትኩ ግን ላለፉተ 42 ዐመታት ዐማራንና የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሐይማኖትን ቁጥር አንድ ጠላት በማለት በጫካ ቆይታው ባጸደቀው ማኒፈስቶ ጭምር የዘር ማጥፋት አውጆብን ይህንኑ በተግባር እያዋለው ይገኛል፡፡ለዚህም በራሱ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀረበውና ከ 2.5 ሚሊዮን በላይ የዐማራ ህዝብ የት እንደገባ አናውቅም ብሎ ይፋ ያደረገበት ይጠቀሳል፡፡

ነገር ግን ቁጥሩ ከ 5 ሚሊዮን በላይ እንደሆነ ተጨባጭ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ ታዲያ ከዚህ በላይ የዘር ማጥፋት ምን አለ ፣ ዐማራው ለዘመናት በደሙና በአጥንቱ ካቆማት ሀገሩ ኢትዮጵያ ልዩልዩ ክፍላተ ሀገራት እንዲሰደድ ዘሩ እንዲጠፋ ሀብት ንብረት እንዳያፈራ ከሰብአዊነት ዝቅ ባለ ሁኔታ እንዲረገጥ ተደርጎ ቆይቷል፡፡ይህ አልበቃ ብሎት እራሱ ዐማራ ክልል ብሎ ባጠረው አካባቢ ጭምር የሚኖሩትን የወልቃይት፡ የጠገዴ፡ የጠለምት፡የራያ አዘቦና መተከል ዐማራ ወንድሞቻችን ዘራቸውን እያጠፋ መሬቱን ለትግሬ መጤዎች በገፍ እየሸነሸነ አከፋፍሉአል፡፡ ከዚህ በባሰ መልኩ ደግሞ ምእራባዊውን የጎንደር በጌምድር እና የጎጃም ዳሞትን ለም ምድር ለሱዳን አሳልፎ ሰጥቷል ፡፡ ይህ ሳያንሰው ሲለው በድብቅ አሊያም በግልጽ ድንበሩን እናካልላለን እያለ እየታተረ ይገኛል፡፡ጀግናው የአማራ ህዝብ ሆይ ወያኔ የአንተን ታጋሽነትና አስተዋይነት ከፍርሃት በመቁጠር እና በንቀት ጭምር የሚያደረሰውን ጥፋት አጠናክሮ ቀጥሏል ፡፡

አሁን ታዲያ ግፍ በቃን ብሎ ከተነሳው ጀግናው የጎንደር ፡የጎጃም፡እና የወሎ ዐማራ ጋር በአንድነት ወያኔን ከጫንቃህ ላይ አሽቀንጠረህ ጥለህ የቀደመውን ማንነትህን የምታስመልስበት ወሳኝ ወቅት ላይ ነህ፡፡ጀግናው የምንጃር ሸንኮራ ህዝብ ሆይ ፤ወያኔ ከላይ የተጠቀሰውን በደል በመላው የዐማራ ህዝብ ላይ ሲፈጽም በአንተም ላይ እየፈጸመ መሆኑን ትረዳዋለህ፡፡እንዲያው ለአብነት ያህል በወረዳችን ህዝብ ላይ የሚፈጽመውን እንጠቃቅስ፤
1፡በአርሶ አደሩ ላይ እያደረሰ ያለው በደል፤

ደርግ በፍትሀዊነት ያከፋፈለውን ብቸኛ የአርሶ አደሩ የኑሮ መሰረት የሆነውን መሬት ሲለው በጉልበት በመንጠቅ አሊያም በጣም ዝቅተኛ በሆነ የካሳ ክፍያ አርሶ አደሩን ከነ ሙሉ ቤተሰቡ ወደ ድህነት አውርዶአል፡፡ በነጭ ጤፍ አምራችነቱ የሚታወቀው የምንጃር ሸንኮራ ህዝብ እርፍ የሚነቀንቁ እጆቹ ለልመና መዘርጋታቸው አይቀረ ነው፡፡
አርሶ አደሩ ለንጹህ መጠጥ ውሀ ፡መብራት ፡የጤና ተቋማት ና መሰል መሰረተ ልማቶች ባይተዋር ሆኗል፡፡የሚጫንበት የመሬት ግብር እዳና የማዳበሪያ ወለድ ክፍያ ሰርቶ ለወያኔ ሆኖበታል፡፡ለእለት ፍጆታ የሚወሉ እንደ ዘይት ስኳርና መሰል ቁሳቁሶች በጥቅማጥቅም ለተሳሰሯቸው ሆዳም ግለሰቦች ብቻ እንዲደርስ በማድረግ አርሶአደሩን ለብዝበዛ ዳርገውታል፡፡
ሌላው አብቁተ በአካባቢችን አብክተህ የሚል መጠሪያ የተሰጠው የብአዴን የገንዘብ ድርጅት አማካይነት ገበሬው ከ15 ከመቶ በላይ በሆነ ወለድ መጠን ብድር እንዲወስድ በማሰገደድ መክፈል ሲያቅተው መሬቱን በመያዝ፡ከብቱን አሊያ ምርቱን በርካሽ በግድ እንዲሸጥ በማድረግ በየአመቱ የነሱ ጥገኛ ሆኖ የብድር አዙሪት ውስጥ ተዘፍቆ ይገኛል፡፡
2፡ በነጋዴው ማህበረሰብ ላይ እየደረሰ ያለው በደል

ነጋዴው ላይ ከአቅሙ በላይ የሆነ ግብር በመጫን እንዳይሰራ ተደርጓል ፡፡ በአንጻሩ ጥቂት የስርአቱ ተላላኪዎች ምንም አይነት ግብር ሳይከፍሉ ክፍተኛ ገቢ ይሰበስባሉ፡፡
ከአመት እስከ አመት በቀን አስር ጊዜ በሚቆራረጥ መብራት በግል ስራ የሚተዳደረውን ህብረተሰብ ተስፋ አስቆረጥዋል፡፡እንዲህም ሆኖ በአመቱ መጨረሻ ያልሰራበትን ከፍተኛ ግብር በመጣል ለወያኔ ጥይት መግዣና ለራሱ ለዐማራው ልጆች መፍጃ የሚሆን ገንዘብ በግድ እንዲያዋጣ ተደርጉዋል፡፡
3፡በመንግስት ሰራተኛው ላይ እየደረሰ ያለ በደል
የሚከፈለው እጅግ አነስተኛ ወርሃዊ ደመወዝ ከእጅ ወደ አፍ ሆኖ ሳለ ከዚሁ ላይ ለተለያዩ መዋጮዎች እየተባለ ይቆራረጥበታል፡፡ ለምሳሌ ለአባይ ግድብ ፡ለአልማ ፡ለጤና መድህን፡ለድርጅት ወዘተ እየተባለ ሰራተኛው እንዲሽመደመድ እና የዘወትር የወያኔ ጥገኛ እንዲሆን ተገድዋል፡፡ተወልዶ ባደገበት አካባቢ በተለይ በከተማ ክፍሎች አንገቱን ማስገቢያ የመኖሪያ ቤት እንዳይሰራ በልዩ ልዩ የሙስና ማነቆዎች ታፍኖ ይገኛል፡፡የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ ማግኘት እንደ ቅንጦት መታየት ጀምሮአል፡፡ለመብታቸው የሚታገሉ ሰራተኞች ከስራ ገበታቸው እንዲፈናቀሉ ሲደረግ የተቀረውን በጥልቅ ተሃድሶ ና ማለቂያ በሌለው ስብሰባ እያጎሩ ለማሸማቀቅ ከፍተኛ ጥረት እተደረገ ነው፡፡
4፡በተማሪውና በወጣቱ ላይ የሚታይ በደል

አርሶ አደሩ ደክሞና ለፍቶ ያስተማረው ልጁ ከተሳሳተው የትምህርት ፖሊሲ በሚመነጭ የስራ እጦት ጎዳና ላይ ከመዋል የዘለለ አንዳች እድል የለውም፡፡ በዚህ የተነሳ ልዩልዩ ለሆኑ ማህበራዊና ስነልቦናዊ ቀውሶች ተጋልጥዋል፡፡ከዚህ ቀደም በመልካም ሰነምግባሩ የሚታወቀው የአካባቢችን ወጣት በስራ ማጣትና ተስፋ መቁረጥ ምክንያት የልዩልዩ ጎጂ ሱሶች ቁራኛ መሆኑ የእለት ተእለት ክስተት ሆኖአል፡፡ጎበዝ ወያኔ በህዝባችን ላይ ያደረሰውና እያደረሰ ያለው ዘርፈ ብዙ ጭቆና ተዘርዝሮ የሚያልቅ ባለመሆኑ የሚከተለውን ጥሪ አስተላልፈናል ፡፡
ሀ፡ለአርሶ አደሩ የመንግስት ሰራተኛውና ወጣቱ የተላለፈ ጥሪ

በጀግናው የጎንደር ዐማራ ህዝብ በተለኮሰው ና ጎጃም ወሎና ሸዋ በተቀበሉት የነጻነት ትግል ዱር ቤቴ ባሉት የከፋኝ ዐማራ፡የዐማራ ተጋድሎ እንዲሁም መሰል ሀገራዊ አርበኞች ወያኔን ቁም ሰቅሉን እያሳዩት መሆኑን ታውቃለህ፡፡አሁን ይህ ትግል እደጅህ ድረስ በጀግኖቹ ልጆችህ አማካይነት በጎበዝ አለቆች እየተመራ ስለመጣ በምትችለው አቅም ሁሉ ከጎናችን ቆመህ ወያኔን ከስሩ መንግለህ እንድትጥለው የሚያስገድድ ታሪካዊ ወቅት ላይ ነህ፡፡በተለይ ወጣቱ ዱር በተ ብለው በረሃ ከገቡ ጀግኖች ወንድሞችህ ጋር ተቀላቀል፡፡የጎበዝ አለቆች አንተን እየጠበቁ ነው፡
ለ፡ለፖሊስና ሚሊሻ የተላለፈ ጥሪ

እንደሚታወቀው ፖሊስና ሚሊሻ ሀይል ከመንግስት ተጥኖ ውጪ የሆነ የህዝብ አገልጋይ ሲሆን በገዛ ወንድምና እህቱ ላይ ህገወጥ እርምጃ አይወስድም፡፡ሰለሆነም መላው የፖሊስና ሚሊሻ አባላት በሙሉ ስለ ህልውናው ከሚታገለው ወገናችሁ ጋር አብራችሁ በመሰለፍ ይህንን ዘረኛ ሙሰኛ ና የወንበዴዎች ስብስብ በማስወገድ ትተባበሩ ዘንድ ና ሀገራችሁን ከጥፋት ትታደጉ ዘንድ ጥሪ ተላልፏል፡፡የወረዳችን ፖሊስና ሚሊሻ እስካሁን ድረስ እያሳየን ላለው ቀና ትብብር ከልብ እያመሰገንን አሁንም ከዚህ በላይ ከህዝቡ ጎን በመቆም ወያኔን በቃ በሉት፡፡
ሐ፡ ለአመራር አካላት የተላለፈ ጥሪ

ከሞላ ጎደል ሲታይ በወረዳችን የአመራር ቦታ ላይ የላችሁ አካላት በስም መጥቀስ ባንፈልግም ለስራችን መቃናት መልካም ትብብርና እገዛ ከልብ እያመሰገንን አሁንም በበለጠ

እንድትቀጥሉበት ጥሪ እናቀርባለን፡፡ሆኖም ለጊዜያዊ ጥቅምና ስልጣን ብላችሁ በወያኔ ምክንያት በህዝባችን ላይ ላንዣበበው ጥፋት ተባባሪ የሆናችሁ በሙሉ ከዚህ አድራጎታችሁ ትቆጠቡ ዘንድ እያሳሰብን በማትመለሱት ላይ ማንኛውንም እርምጃ ለመውሰድ እንገደዳለን፡፡
በተጨማሪም
1ኛ ለተቀረው ጀግናው የሸዋ ዐማራ ህዝብ
‹‹ዘመቻየ በጥቅምት ወር ነውና የሸዋ ሰው በጥቅምት ወር እኩለታ ወረኢሉ ከተህ ላግኝህ ››ብለው ነበር አምየ ምኒሊክ፡፡ የሰዋ ህዝብም አላሳፈራቸውም ነበር ፡፡ ሰዋ አሁንም አኛን ልጆቹን አያሳፍረንም፡፡ ቡልጋ ፡ተጉለት ፡መንዝ፡መርሀበተ፡ይፋት፡ጅሁር፡እንሳሮ፡ደራ፡አዲስ አበባና ለሎችም ፡፡ የቅዱሳን የነገሰታት እንዲሁም የጀግኖች መፍለቂያ ሰዋ ዛረም እንደጥነቱ ማንነትህን እንዲሁም የጀግንነት ታሪክህን የምታድስበት ጊዘ ላይ መሆንክን ተገንዝበህ በያለህበት ተነቃነቅ፡፡ ከጎናችን መሆንክን በተግባር አስመስክር፡፡ለዚህም በመላው ሰዋ ያለውን ትግል ማእከላዊ በሆነ መልኩ ተቀናጅቶ እነዲካሀድ የተጀመረውን ትብብር በፍጥነት ከግብ አደርስ፡፡

2ኛ ለተቀረው ጀግናው የዐማራ ሕዝብ፤ ከ እምየ ምኒሊክ አገር የተላለፈ ጥሪ
አጽመ ርስታችን የሆነውን ወልቃይት፡ሑመራ፡ጠገዴ፡ጠለምት፡ራያ አዘቦና መተከልን ገምሶ ወስዶ ታላቅዋ ትግራይን ለመመስረት የሚፍጨረጨረው ወያኔ በጀግኖቹ የተዎደሮስ ልጆች የጎንደር ዐማሮች የተለኮሰውን በመቀጠልም በአባ ኮስትር አገር ልጆች የጎጃም ዐማሮች የተስፋፋውን ሁሉአቀፍ የነጻነት ትግል እኛ የሸዋ ዐማሮች በይፋ እንደተቀላቀልነው እያሳወቅን፤ የተቀረው ዐማራ የንጉስ ሚካአል ወሎን ጨምሮ በአንድነትና ማእከላዊ በሆነ መልኩ ትግሉን አስተሳስረን ወያነን ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አስቀንጥረን እንጣላት፡፡በየቦታው ያላችሁ የጎበዝ አለቆች ና አርበኞች ቀደም ሲል ተጀምሮ የነበረውንና ወያኔ ያደናቀፈችውን በአንድ ማእከላዊ ትግል ስር የመሰባሰብ ስራ በድጋሜ በቶሎ እውን እንዲሆን እንረባረብ፡፡

3ኛ በዐማራው ስም ተደራጅታችሁ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር ለምትንቀሳቀሱ ወገኖች
ህዝባችን ከወያኔ ሽፍቶች አራሱን ለማላቀቅና ህልውናውን ለማስጠበቅ እያደረገ ያለውን ተጋድሎ ቀደም ብላችሁ የጀመራችሁት ሁለንተናዊ ድጋፍ ተጠናከሮ ይቀጥል፡፡ትግላችን በአጭር ጊዜ ውጤታማ ይሆን ዘንድ ሁላችሁም ተቀራርባችሁ በአንድነት፡ በታማኝነት፡ በመከባበርና በፍቅር ርብርብ እንድታደረጉ አደራ እንላለን፡፡ድጋፋችሁም አይለየን፡፡

4ኛ ለፈደራል ፖሊስና የሀገር መከላከያ ሰራዊት
ከህዝብ አብራክ የወጣችሁ የህዝብ ልጆች ናችሁና ከዘረኛው ወያነ ይልቅ ለህዝባችሁ ወግናችሁ እስካሁን እያደረጋችሁ ካለው በላይ በተጠናከረ መልኩ ወገንተኝነታችሁን ለህዝባችሁ ታደረጉ ዘንድ አደራ አንላለን፡፡ለዚህም ቀደም ብሎ በተዘረጋው መረብ የህዝባችሁን ትግል በነቂስ ተቀላቀሉ፡፡

5ኛ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ
በአራቱም ማእዘን ያለከው መላው የሀገራችን ህዝብ ሆይ ከዚህ ዘረኛና ሀገር አጥፊ የሽፍቶች ስብስብ ራስህን እያደራጀህ በመታገል ለነጻነትህ ተዋደቅ፡፡በዚህም ሁሉን አቀፍ ፍትሀዊና ደሞክራሲያዊት ሀገር እንደትመሰረት የበኩልህን ድርሻ ተወጣ፡፡
‹‹ሰልፍ የጀግና ነው ድል የእግዚአብሐር ነው›› ድል ለመላው የዐማራ ህዝብ ፣ ድል ለመላው የ ኢትዮጵያ ህዝብ፡፡››
 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.