ወያኔ ገደብጌ ላይ ስትገረፍ አደረች – ልያ ፋንታ

የጎንደር የነጻነት ኃይሎች ከጎንደር ወደ ዳባት መስመር 60 ኪሜትር ርቀት ላይ የምትገኜውን የገደብጌን ከተማ በመውረር በወያኔ ግፍ መፈጸሚያ የፖሊስ ጣቢያ እና አስተዳደር ላይ ከፍተኛ ጥቃት ፈጽመው በድል ተመልሰዋል።

ከወያኔ ጋር ሲላላኩ እና ሲሞዳሞዱ የነበሩት መደበቂያ ወገን አጥተው ማለፊያ ቅጣት አግኝተዋል።
የጎንደር ህዝብ ወደ ትጥቅ ትግል ሆ ብሎ ከዘመተ ዘጠኝ ወራት አለፉት። ከጎጃም ውጭ ያለው የማህል ሀገር ፣እና ቀሪው ክፍለሀገር ምን እንደሚጠብቅ አይገባኝም።
በርካታ መንግስትን ከስልጣን ለማስወገድ በቂ ምክንያቶች ቢከሰቱም ህዝቡ በፍርሀት ተውጦ ወያኔን ማስዎገድ ተስኖታል።
እንደ ምሳሌ የቆሼ ተራው የወገን እልቂት እንኳ ይህን ዘረኛ እና የሀገሪቱን ህዝብ ገንዘብ ዘራፊ፣ ወንበዴ መንግስት ለማስዎገድ በቂ ምክንያት ይሆን ነበር።
ኧረ ባካችሁ መጠላለፉን እንተው እና ለድል እንነሳ?

የጎንደር የነጻነት ታጋዮች አበጃችሁ!

ልያ ፋንታ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.