በጠዋት ውሃ መጠጣት የሚያስገኛቸው 5 በረከቶች

 

1. በባዶ ሆድ ውሃ መጠጣት ትልቁ አንጀትን በማጽዳት ንጥረ ነገሮች በቀላሉ ወደ ሰውነት ውስጥ ተመጥጠው እንዲገቡ ያደርጋል፡፡

2. አዳዲስ የደምና የጡንቻ ህዋሳት እንዲመረቱ ያደርጋል፡፡

3. ክብደት ለመቀነስ ይረዳል፡፡ 450 ሚሊ ሊትር (ከግማሽ ሊትር ጥቂት የሚያንስ) ቀዝቀዝ ያለ ውሃ ጠዋት ላይ መጠጣት የምግብ መፈጨትና መዋሀድ ሂደትን በ26% ያሳድገዋል፡፡

4. ለቆዳ ጥራት እጅጉን ተመራጭ ነው፡፡ በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ሰውነታችን ገብተው ደም ውስጥ የሚገኙትን መርዛማ ኬሚካሎች በማጽዳት ቆዳን የጠራና የተዋበ እንዲሆን ያደርጋል፡፡

5. በሰውነታችን ውስጥ ያለውን የሊምፍ ስርዓት (Lymph System) በማስተካከል ሰውነታችን በውስጡ ያሉትን ፈሳሾች ለማመጣጠን እንዲችልና በትጋት ኢንፌክሽንን እንዲከላከል በማድረግ ሰውነታችን የየቀኑን ተግባሩን በጥሩ ሁኔታ እንዲያከናውን ይረዳል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.