በወልቃይት ከ440 ኩንታል በላይ የወያኔ ጥጥ በእሳት ወደመ፤- በዓለማያ ዪንቨርሲቲ የተማሪዎች ጥልቅ ተሀድሶ ስብሰባ ከሸፈ፤ (ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋው )

በወልቃይት ከ440 ኩንታል በላይ የወያኔ ጥጥ በእሳት ወደመ፤

በወልቃይት የስኳር ፋብሪካ እሠራለሁ በማለት ገበሬዎችንና ከፊል የዋልድባ ገዳምን ያስለቀቀው የትግራይ መንግሥት ፋብሪካው ዕውን ሊሆን ባለመቻሉ ከፍተኛ የጥጥ ምርት እየተመረተበት እንደሆነ የገለጹት ምንጮች ተለቅሞ ሊጫን የተከዘነ 440 ኩንታል በላይ ጥጥ ሙሉ በሙሉ በእሳት ወድሟል፡፡
የእሳት ቃጠሎው የደረሰው መጋቢት 12 ቀን 2009 ዓ.ም እኩለ ቀን ሲሆን እንደሆነ የነገሩን የዐይን ምስክሮች በሌሎች የወልቃይትን ሕዝብ ሀብት እየተቀሙ ባፈሯቸው ንብረቶችም ላይ ተመሳሳይ ጥቃት ሊቀጥል እንደሚችል አስታውቀዋል፡፡

በዓለማያ ዪንቨርሲቲ የተማሪዎች ጥልቅ ተሀድሶ ስብሰባ ከሸፈ፤

በዓለማያ ዪንቨርሲቲ መጋቢት 16 እና 17 ቀን 2009 ዓ.ም ቅዳሜ እና እሁድ ለማካሔድ የተሞከረው የወያኔ ጥልቅ ተሀድሶ ስብሰባ ተማሪዎች በማመጻቸው ምክንያት ሙሉ በሙሉ ከሽፏል፡፡ ቅዳሜ ዕለት ጠዋት ተማሪዎችን ለማስገደድ ሙከራ የተደረገ ቢሆንም ተማሪዎች በማመጽ ሳይገቡ ቀርተዋል፡፡
በቀጣዩ ቀን እሁድ ተጨማሪ የፖሊስ እና የጸጥታ ኃይል መጥቶ እንዲጀመሩ ማስታዎቂያ ቢወጣም ተማሪዎች በበኩላቸው በራሪ ወረቀቶችን በመበተን ማንም ተማሪ ስብሰባው ላይ እንዳይገኝ በማሳሰባቸው ምክንያት የወያኔ ጥልቅ ተሀድሶ ስብሰባ ሳይደረግ ቀርቷል፤ እንደ መረጃ ምንጮቻችን፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.