የታምፐሬ ዩኝቨርሲቲ ኃይለማርያም ደሳለኝን የክብር ዲግሪ እንደማይሰጥ አስታወቀ

ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋው

በፈረንጆች አቆጣጠር መስከረም 20 ቀን 2016 በፊንላንድ የሚገኘው የታምፐሬ ቴክኖሎጂ ዪንቨርሲቲ ኃይለ ማርያም ደሳለኝን የክብር ዶክትሬት ዲግሪ እንደሚሰጥ ካስታወቀበት ቀን ጀምሮ በርካታ ኢትዮጵያውያን ተቃውሟቸውን ሲገልጡ መቆየታቸው የሚታወስ ሲሆን በዚህ ሳምንት ዩንቨርሲቲው ‹‹ለኃይለ ማርያም ደሳለኝ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ አንሰጥም›› በማለት አስታውቋል፡፡

የፊንላንድ ብሔራዊ መገናኛ ብዙሃን ድርጅት የስዊድንኛ ቋንቋ የዝግጅት ክፍል ለዩንቨርሲቲው ዛሬ መጋቢት 20 ቀን 2009 ዓ.ም ባወጣው ዘገባ ‹‹አወዛጋቢው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስቴር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በታምፐሬ ዩንቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ አይሰጣቸውም›› ሲል ዘግቧል፡፡ የዜና አውታሩ ከዩንቨርሲቲው ተሰጠኝ ያለው መልስ ጠቅላይ ሚንስተር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ሽልማት በሚደረግበት ጊዜ መገኘት ስለማይችሉ ነው የሚል መልስ ቢሰጥም የዝግጅት ክፍሉ የራሱን ትንታኔ ሰጥቷል፡፡

የካሊፎርኒያ ስቴት ዩንቨርሲቲ ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረ ማርያም (አልማርያም)ና ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋውን ዋቢ አድርጎ ‹‹በሽዎች የሚቆጠሩ ዐማሮችና ኦሮሞዎች እየተገደሉ፣ አገሪቱ በወታደራዊ አገዛዝ ሥር ሆና ከ30 ሺ በላይ ሰዎች በየቦታው ታስረው እየተሰቃዩ ያለበትን አገዛዝ ኃላፊ መሸለም ለአፍሪካውያን ስድብ ነው፤ የፊንላንድ መንግሥትም ለአፍሪካውያን ሰብአዊ መብት ጥሰት በይፋ ድጋፍ እንደሚያደርግ ያሳያል›› በማለት ሰፋ ያለ ሐተታ አስፍሯል፡፡

የዜና አውታሩን የስዊድንኛ ቋንቋ ዘገባ በጎግል ወደ እንግሊዝኛ መልሳችሁ ለማንበብ የሚከተለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ https://svenska.yle.fi/…/etiopiens-premiarminister-blir-in

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.