የማይተላለፍ እና ቴዲ አፍሮ 『ጋዜጠኛ ቶማሰ ሰብሰቤ』

。ለአንድ ደቂቃ በሬድዮ መክፈት የተከለከሉት አምሰቱ የቴዲ ዘፈኖች

。አከፋፋይ ለሸያጭ በበአላት የቴዲን ሰራ ማቅረብ እና የዛ ሰፈር ጩህት

。ፍቅር እሰከ መቃብር ሊታገድ ይሆን?

 

በዛ የጎልማሳ እድሜዮ ያጣጣምኩት ነብሰ ነጣቂው ዘፈን ያሰተሰሪያል ዛሬም ቢናፍቀኝ ማንም አይፈርድብኝም።እውነት ፣ፍቅር ፣የወገን አልቂት እና ፖሎቲካ አንድ ላይ በ7 ደቂቃ የ17 አመት ቁሰላችንን የገለፀች መፅሃፍ ነወ  ያሰተሰርያል ዘፈን።

 

ከቀዳማዊ ሃይለ ሰላሴ እሰከ መለሰ ዘመን የተገመገመበት ፣ የተማሪ ውለታ የተነሰታል ፣ ለለውጥ ወጣው ያለ ሁላ የታል የተባለበት  ፣ ቂም በቀል ይቅርና ፍቅር ያሸንፋል ብሎ ቴዲያችን ማዲባ ማንዴላን ሆነልን።

 

በተለይ ይህን ትላልቅ ሀሳቦች በተዋጠጣለት ግጥም እና ዜማ መሰራት ይፈልጋል የካሳውንን ልጅን ጭንቅላት።

 

መፃፍ የሆነ ሀሳብን ዘፈን አድርጎ በሚያምር ድምፅ ማሰደመጥ የቻለው የሙዚቃው ንጉሰ አፍሮ ብራንድ ሁሌም በልባችን አለ።ይህን አልበም ምን ያህል ተፅኖ ፈጠሪ መሆኑን የሚያውቁት አፍቃሪዎቹን ሲያዮ ወይም ሲያደምጡት ብቻ ሳይሆን የመንግሰት ሚዲያዎች ሲያደምጡ ነው።

 

ከዚህ አልበም ከግማሸ በላዮ ዘፈኖች በመንግሰት ሚዲያ እና በደጋፊዎች ብዙሃን መገናኛ በምን አይነት መልኩ አይቀርቡም።

 

ህዝቡ ሰራውን ወዶታል፤ ሚዲያው ደሞ የመንግሰት መኝታ ቤት ሰለሆን ፍንክች አይልም።『ሸገር እና የተወሰኑትን ሳይጨምር』 አይጨምርም።

 

በአንድ ወቅት የቴዲ አፍሮ ዘፈኖች ያሉበት ሬድዮ አርካይፍ መፈለግ ጀመርኩ ።ከአብዛኛውቹ ዘፈኖች ጎን በቅንፍ ” የማይተላለልፍ” የሚል ፅሁፍ አለው።አይ ፖለቲካ !

 

እቴጌ(የማይተላለፍ ወይም ልዮ ፕሮግራም ከሆነ ብቻ)… … …ባልደራሱ(የማይተላለፍ)… … ……ካብ ዳላክ(የማይተላለፍ)… ……ሰሚ ለሌለ አፌ(የማይተላለፍ)… …ላምባዲና(ልዮ ፕሮግራም ከሆነ ብቻ) …ያሰተሰሪያል(የማይተላለፍ) በሚል በፍፁም ተከልክለዋል።ግን ያሰተሰሪያል ጎን የማይተላለፍ ብቻ መቀመጡ ራሱ ብቻ አነሰው በዚህ አየነት አልኩኝ።የጥይት ምልክት አጠገቡ ጠብቄ ነበር…እ…እ…

 

97 ሳሰብ ምርጫ ፣ የቴዲ አልም ፣ የፕሬሰ የነፃነት መብት መታፈን ፊቴ ድቅን ይላል።ወደ ጉዳዮ ልመለሰ……

 

ጋዜጠኛው «ሼመንደፍር» እንኳን ቢጋብዝ።ወደ ቢሮ ሲገባ ቁርሱን ባልበላ አንጀቱ አለቃው” በሼመንደፍር የጀመርክ በያሰተሰሪያል እንዳትወጣ “በሚመሰል ግልምጫ ይጥለዋል።አን

 

አንድ የድሮ ባልደረባዮ እንዲህ አለችኝ “ቴዲን ሰለምወደው ሬዲዮ ላይ ሰገባ እሱ ምርጫ ነበር።በተለይ “በል ሰጠኝ ” በተደጋጋሚ እጋብዛለው ለአድማጭ።አንድ ቀን አለቃዮ “ምንድ ነው አምላክ  የሚሰጥሽ ባል ነው ወይሰ አሁን የሚያሰተዳድርሽ ልኬ አይደለም ለማለት ነው።ለአንድ ሴት ፍለጋ ዘፈን ሳይሆን ነገር ፍለጋ ነው ” አለኝ ያለችኝን አሰታውሳለው።

 

 

 

ፍቅር ፖለቲካ የሆነበት ሀገር… … ባንድራ ቦለቲካ…  የሀገር ፍቅር ቦለቲካ… 70 ደረጃ ቦሎቲካ… ንጉስ መጥራት ቦለቲካ የሆነበት መንግሰት እና አሰተምህሮት በሰው ውሰጥ በዛ።

 

በቃ ሰለ ሴት ብቻ ይዘፈን ባይ …በቃ ሰለ ምንትሰ ይዘፈ… ለማሬ እንዲዘፈንለት የሚፈልግ ንብ መንግስት።ከደቂቃ በሃላ እጅ እጅ የሚል ሰራ የሚሻ ንጉሰ የቴዲን የግጥም ፣የዜማ አና የድምፅ ተወዳጀነትን መቀበል ይከብደዋል።

 

ቴዲ በጥቂቷ በ7ደቂቃ ወርቃማ ሀሳቦችን በሙዚቃ ያናግራል እኛ ግን አመታት ሰለ እሱ ያልሆነ የሆነ እናወራለን።ብዙ ሲዋራ ደሞ ጭንቅላይ ይታያል።ከሰራው በላይ እኛ አንዘባርቃለን።ገቢያተኞች በአልን ምክንያት አድርገው በቢዝነሰ ማይንድ ካሴቱን ሲሸጡ እዛ ሰፈር ያሉ ከእምነት ጋር አገናኝተው ይዘባርቃሉ።ክብር ለሚገባው ክብር እንሰጣለ።ጀግና አንዴ ነው።ቴዲ ካሳሁን ግርማሞ ነን።ወሬ አንፈልግም።

 

እየጠበኩት ያለውት አሁን ከአዲሱ አልበሙ ሰንቶቹ በጭፍን ተፈርጀው ይታገዱ ይሆን? ፍቅር እሰከ መቃብር እንዳይታገድም ሰጋት አለኝ … … ሲዳማዎች እናተም ሰጉ ትንሽ……ቴዲ አፍሮ ዘፋኝ ብቻ ሳይሆን የዘፋኝ መሰፈሪያ ነው።

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.