ታላቅ ህዝባዊ ስብሰባ በኢትዮጽያ ሰባዊ መብት ገፈፋ ላይ በመረጃ እየተደገፈ ውይይት በዋሺንግተን ዲሲ

አገራችን ኢትዮጱያ የልጆች መካን አይደለችም። ጥቂቶች በሕዝብ ላይ የግፍ ቀንበር ጭነው፣ የሕዝብን ሃብት እየመዘበሩ፣ ዜጎችን ለስቃይና ለእንግልት እየጋረዱ ባሉበት ወቅት፣ ብዙዎችም ለጥቅም ሲሉ እንዳላዩ ሆነው ዝምታን በመረጡበት ወቅት፣ ለሕዝብ የቆሙ፣ ለመበለቶች የሚሟገቱ፣ የሚሰሩትን ግፍና በደሎች ሳይፈሩና ሳይሸማቀቁ የሚያጋልጡ፣ ከራሳቸው ጥቅም ይልቅ የአገርንና  የሕዝብን ጥቅም ያስቀደሙ በርካታ የዘመናችን ጣይቱዎች፣ የዘመናችን ባልቻ አባነፍሶዎች አሏት።
ከነዚህ ብዙ ጀግና ኢትዮጵያዊያን መካከል  ወጣት ሃብታሙ አያሌው አንዱ ነው። ሃብታሙ አያሌው የቀድሞ የአንድነት ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊና በተለያዩ የአገራችን ክፍልች ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ያደረገው የሚሊዮኖች ድምጽ ሰብሳቢ ነበር። ሆኖም በፈጠራ የሽብርተኝነት ክስ ለሁለት አመት ታሰረ። በወህኒም በደረሰበት ቶሮቸር ለከፍተኛ ሕመም ተጋረደ። ከብዙ ስቃይ በኋላ፣ በፈጣሪ ቸርነት፣ በኢትዮጵያዉያንም ድጋፍ ወደ አሜሪካ መጥቶ ሕክምና ሲከታተል ቆይቶ  ጤንነቱ በአሁኑ ወቅት በተሻለ ደረጃ ላይ ይገኛል።
አገዛዙ ይሄን ሁሉ ስቃይ ሃብታሙ ላይ ያደረሰበት፣ ተማሮ ዝምታን እንዲመርጥ ነበር። ሆኖም ግን ሃብታሙ አያሌው፣ ምንም እንኳን እርሱ ጤንነቱ ቢመለስለትም፣ በጠና፣ በድህነት፣ በአምባገነንነት፣ በዘረኝነት፣ በኢሰባአዊነት፣ በኢፍትሃዊነት የታመመችው ኢትዮጵያ እስክትድን ድረስ ትግሉን ለመቀጠል ቆርጧል።
ትግሉ ምን ደረጃ ላይ እንዳለ፣ ወደፊትስ እንዴት መቀጠል እንዳለበትና በተለያዩ የአገራችን ወቃታዊ ጉዳዮች ዙሪያ፣ ከኢትዮጵያዉይን ጋር ለመመካከር፣  ሃብታሙ አያሌው የአሜሪካ የመጀመሪያውን  ሕዝባዊ ስብሰባ በዋሺንግተን ዲሲ ያደርጋል።
በዲሲና አካባቢዋ የምትገኙ ኢትዮጵያዉይን ሁሉ በዚህ ስብሰባ ትገኙ ዘንድ ተጋብዛቹሃል።
HERATON PENTAGON CITY HOTEL
900 South Orme Street, Arlington, VA 22204
Sunday April 9 at 1:30 pm

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.