ታላቁ ሌ/ጀነራል ጃጋማ ኬሎ በ96 ዓመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል – የወይንሸት ሞላ

ለኢትዬጵያ ህዝብ እንዲሁም ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን እመኛለሁ::

በጣሊያን ዳግም ወረራ ወቅት በ15ኛ አመታቸው ከፋሽስት ወራሪ ጦር ጋር በተለያዩ አውደ ግንባሮች ተፋልመው ከፍተኛ ጀብዱ የፈፀሙት እና ጣሊያን ከአገር ተሸንፎ ከወጣ በኋላም የአገር ዳር ድንበርን በማስጠበቅ ከፍተኛ ጀግንነት የፈፀሙት የሌ/ጀኔራል ጃገማ ኬሎ በ96 ዓመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል::፡

በ1929 ዓ.ም ጣሊያን ከ40 ዓመታት የአድዋ ሽንፈት በኋላ ዳግም ኢትዮጵያን በወረረበት ወቅት ገና በ15 ዓመት ወጣትነት ዕድሜያቸው የራሳቸውን ጦር በማደራጀት ጠላትን የተዋጉት ሌ/ጀኔራል ጃገማ ኬሎ በወቅቱ በተለያዩ የጦር ውሎዎች በጠላት ላይ ከፍተኛ ጀብዱን ተቀዳጅተዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር ሶማሊያ ኢትዮጵያን በወረረችበት ወቅት የአገርን ዳር ድንበር በማስጠበቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል፡፡

ሌ/ጄኔራል ጃገማ ኬሎ ጥር 20 ቀን 1913 ዓ.ም የተወለዱ ሲሆን የአንድ ወንድና የአምስት ሴት ልጆች እንዲሁም የአምስት የልጅ ልጆችና አራት የልጅ ልጅ ልጆችን አፍርተዋል:: የሌ/ጀነራል ጃገማ ኬሎ በህይወት እያሉ በደራሲ ፍቅረ-ማርቆስ ደስታ “ጃገማ ኬሎ የበጋው መብረቅ” ታሪካቸው ተፅፏል:: ሌ/ጀነራል ጃገማ በ15 ዓመታቸው ወራሪውን የጣሊያንን ጦር ለመዋጋት ከዘመቱበት የአርበኝነት ገድል ጀምሮ እስከመደበኛው የሀገሪቱ መካላከያ ጦር ድረስ ለኢትዮጵያ እና ለህዝቧ ነፃነት እና ክብር ሲሉ በርካታ የጦር ገድሎችን በመፈፀማቸው የነበራቸው የሌ/ ጀነራል ማዕረግም በሀገሪቱ የወታደራዊ ማዕረግ ታሪክ የመጨረሻውና ከፍተኛ እንደሆነም ይነገራል::

ታላቁ ሌ/ጀነራል ጃጋማ ኬሎ ነፍስዎትን በገነት ያኑርልን::

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.