የልብ ድካም – በዶ/ር አቤል ጆሴፍ

አንዴ አበሾች ከበዉ የአሜሪካን ኳስ (American football) ጨዋታ ሲያዩ ቆይተዉ ከተለያዩ በህዋላ አንዱ ግዋደኛቸው ከተኛበት ሞቶ ተገኘ፤ ይህም በሆነ ጊዜ ሁሉም በድንጓጤ ትላንት ከኛ ጋር ነበር፤ ሲዝናና ሲጫወት እንደነበርና ምንም አይነት የህመም ስሜት እንዳለነበረዉ ነገሩን።

ይሁንና ሰዉየዉ ወደ ስልሳወቹ የተቃረበ፤ ምንም የንት ህምም ያልነበረበት ነበር።
ከዶክተር ሂዶም ስለማያዉቅ ቢኖርበትም የሚነግረዉ የለም።
በኛ ባህል ሰዉ ወደ ዶክተር የሚሄደዉ ከተመመ ብቻ እንደሆነ ነዉ የሚታወቀዉ፤ እንደ ምእራቡ አለም በ አመትም ሆነ በስድስት ወር ለቸክ አፕ ብሎ መሄድ የሚባል ነገር የለም።
የራስ ምታት ያለበትም፤ በእንቅልፍ ወይም ትንሽ አልኮል መሳይ ጎንጭቶ መተኛት የተለመደ ነዉ።
እንግዲህ ወደ ቁም ነገሩ ለመመስለና ወንድማችን የሞተዉ በልብ የሚገኘዉ የደም ቅዳ ክፍል ተዘግቶና ደም ወደ ልቡ ጡንቻ መድረስ ሳይችል ቀርቶ ነዉ።

የልብ ድካም ምንድን ነዉ (what is heart attack also called myocardial infarction)

የልብ ድካም ማለት የተወሰነዉ የልብ ጡንቻ በደም ቅዳ አማካኝነት የሚደርሰዉ ደም ሆነ አየር ኦክስጅን (oxygen) ሳይደርሰዉ ቀርቶ ሲጎዳና ሲሞት ነዉ፤ ይህም በሚሆንበት ጊዜ በቀጥታ የልብን ስራ ሲለሚያደናቅፈዉ ደምም ኦክስጅን ወደ ሌሎች ሰዉነታችን ክፍል አይዳረስም።
ብዙ ጊዜ የልብ ድካም የሚደርሰዉ የደም ቅዳ ብዋንብዋ (coronary arteries) ሲዘጋና የደም ማቀበል ተግባሩ ሲቋረጥ ነዉ።
የልብ ድካም በጊዜዉ ከታወቀ በህክምና እርዳታ ሊረዳ ይችላል፤ ካልሆነ ግን ቋሚ ጉዳት ያደርሳል፤ ወይም በሽተኛ ሊሞት ይችላል።

ምልክቶቹ ምንድን ናቸዉ (what are the symptoms of heart attack?)

1.ደረት አካባቢ የሚሰማ ስሜት፤ (chest discomfort-like pain, pressure tightness, heaviness or burning).
2. በአንገት፤ በ ግራ ትከሻ፤ምንጋግ በኩልና በ እጅ አካባቢ ስሜት መሰማት (pain or discomfrot in the neck, left shoulders, lower jaw, arms).
3. የእስትንፋት ማጠር (shortness of breath).
4. ምዝዋር ርእሲ መስማት (dizziness or feeling lightheaded)
5. ማጥወልወልና አንዳንዴም ማስታወክ (Nausea and vomiting)
6. ያላተሰበ ምክንያቱ ያልታወቀ ድካም (fatigue)
7. የልብ በሃይል መምታት (feeling like your heart is beating really fast).

የልብ ድካም መኖርውን ካወቁ ምን ማድረግ አለብወት ( what should id if I have symptoms of heart attack)

911 መደወል ወይም አምቡላንስ ጠርቶ ቶሎ ወደ ሆስፒታል መሄድ
አስፕሪን በእጅዎ ካለ አንድ አስፕሪን ማለትም መዋጥ

ምንድን ነዉ ልብ ድካም የሚያስከትለዉ (what causes heart attack?)
ከላይ እንደገለጽኩት የልብ ድካም የሚደርሰዉ ወደ ልብ ደምና ኦክስጅን የሚወስደዉ ደም ቅዳ ተዘግቶ ልብ ተገቢዉን ኦክስጅን ማግኘት ሳይችል ሲቀር ነዉ።
የመዘጋቱን ተግባር የሚያደርሰዉ በደም ስሮች የሚጠራቀመዉ የስብ መጠን ነዉ፤ ልክ ዉሃ የሚያልፈበትን ቶቦ እንደሚደፈንዉ ቆሽሻ ስብም የልባብን ደም ቅዳዎች እንዲሁ ይደፍናቸዋል፤ በዚህም ምክንያት የደምን በደንብ መተላለፍ ይገታል፤ ወይም በጠቅላላ ያቆመዋል፤ ያው ልብ ድካም ያስከትላል።

ለልብ ድካም የሚያጋልጡን ምክንያቶች ምንድን ናቸው (risk factors for a heart attack)
1.ሲጋር ማጨስ
2.ስክዋር በሽታ፤ በተለይ ህክምና የማንከታተልና ስኳሩን ማቀም ያልቻልን የበለጠ እንጋለጣለን
3. እድሜ ወንዶች ከ አርባ አመስት አምት ሲያልፈን ሴቶች ደግሞ ከ ሃምሳ አምስት አመት ሲያልፈን 4. ለልብ ድካም የተጋለጥን እንሆናለን
5. ብዙ ስብ በሰዉነታችን ሲኖር
6. የደም ግፊት ካለብን
7. የቤተሰብ ታሪክ፤ ቅርብ ዘመድ ከዚህ በፊት ልብ ድካም ካለበት
8. ስፓርት የማንሰራ ከሆነ
9. የኑሮ ግፊት ያለብን
10. መወፈር በተለይ ከሆዳችን አካባቢ

እንዴት መመርመር ይቻላል (How is heart attack diagnosed?)

ልብ ድካም እንዳለበት አንድ ሰዉ የተለያዩ የደም ሆነ ሌሎች ምርመራዎች ይካሄድሉ፤ እነሱም
ኢኬጅ ማለትም የልብን እንቅስቃሴ የሚያሳይ
የደም ምርመራ ማለትም የልብ ጩንቻ መቁሰል ወይም አለመቁሰሉን የሚያሳይ
ኢኮካርድዮግራም የልብን ድምጽን በመጠቀም የልብን ምስል የሚያነሳና በትክክል ደም መግፋት ስራዉን መስራቱን የሚለካበት መሳሪያ ነዉ
ራጅ ማንሳት በዚህም ዘዴ የልብን ቅርጽና መጠኑን ማወቅ ይችላል
ለላዉ በልብ የደም ስሮች ቱብ በመላክና በቱቡ ዉስጥ የሚያልፍ መሪ ሽቦ በምላክና ለራጅ አምች ይሆነ ነገር በምዉጋት የልብ ብዋንብዋ የተዘጋበትን ቦታ ማየትና ብሎም ማጽዳት ይሆናል።

የልብ ድካም እንዴት መታከም ይችላል ( how is heart attack treated)

ልብ ድካም በመድሃኒትና በወዶ ጥገና የሚታከም ሲሆን ይምህ የሚሆነዉ እንደ አደገናነቱ ታይቶና ተመዝኖ ነዉ።

ልብ ድካም እንዴት መከላከል ይቻላል (prevention)

1.ሲጋራ ማጨስ ማቆም
2.ጤነኛ የሆነ ምግብ መመገብ በተለይ የስብ መጣኑን መቀነስ
3. ስፖርት ሁሌ መስራት
4. ኑሮን የሚያዛቡ ነገሮችን መራቅ
5. የደም ግፊትን መቆጣጠር
6. የስክዋር በሽታ ያለባቸው የስኳር መጠናቸውን መቆጣጠር
የግል ዶክተርን በቀጠሮ ማየትና ዶክተር የሚነግረነን መከታተል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.