አንዲት ሴት ክርስቲያኖ ሮናልዶ 300 ሺ ፓውንድ ካሳ ካልስጠኝ ፍርድ ቤት አቆመዋለው አለች l ክርስቲያኖም የተባለውን ብር ሊሰጣት ተሰማምቷል ፤ ለምን?  【በቶማስ ሰብስቤ】

ክርስቲያኖ በተለያዮ ጊዜ የተለያዪ ክሶች ቀርበውበታል።አብዛኛዎቹ ክሶች ከሰም ማጥፋት ጋር ቢያያዙም የተጫዋቹ ስህተቶችም ያሉበት ታሪኮች ሰምተናል።ብዙም በግል ህይወቱ ቁጥብ ያልሆነው ፖርቱጋላዊው አጥቂ ብዙ ጊዜያት በሴቶች ይከሰሳል።ፍቅረኛው ነኝ የምትል ፤ ወልጄለታለው ብላ የምታወራ እና ብዙ ሞዴሎች ጋር ያለው የፍቅር ህይወቱ ገቢያ ላይ በመረጃ ይቀርባል።በፍቅር ህይወቱ ቁጥብ ያለመሆኑ ደግሞ አንዳንዴ አሁን እንደምነግራቹ አይነት ጠንከር ያለ ውንጀላ እንዲስማበት አድርጎታል።
ቦታው የአሜሪካኗ ዘናጭ ከተማ ላሰ ቬጋስ ነው ተጫዋቹ እና ቆንጆዋ ሴት የተገናኙት።ስሟ ያልተጠቀሰው ይቺ የቬጋስ ነዋሪ ሮናልዶ በ2009 ሰኔ 13  እንዳገኘቸው ትናገራለች ።በዚሁ ቀን በራሷ ቅንጡ ሆቴል ተቀምጣለች።ተጫዋቹ ለመዝናናት ወደ ሆቴሏ እንደመጣ እና እንደ ተዋወቁተ ትናገራለች።በዚያው እለት እንዲህ ባለው ግንኙነት ብዙ ነገሮች ተግባብ ፤ በመጨረሻ ግን ነገሩ ተበላሽ።ቆንጆዋ ሴት ስፔን መቀመጫው ላደረገው ኤል ሙንዶ ጋዜጣ የምታመራበት ክስተት ምሽቱን ገጠማት።የአራት ጊዜያት የባላንዶር ባለቤት ምሽቱን ባሮናልዶ ያለ እኔ ፍቃድ ደፈረኝ ብላ ተናገረች ለጋዜጣው።
ከዚህ በሃላም ቆንጆዋ ሴት ጉዳዮን ወደ ፍርድ ቤት እንዳትወስደው  ድርድር ተጀመረ ትላለች።እሷ እና የእሱ ተወካይ ያለ ፍርድ ቤት ጣልቃ ገብነት ለመጨረስ ተሰማሙ።በ2010 ጥር ወር ያለ ፍርድ ቤት ጣልጋ ገብነት ተሰማሙ።በሶስት ገፅ የሁለትዮሽ ሰምምነት መሰረት ፖርቱጋላዊው ለሰራው አፀያፊ ሰራ 300 ሺ ፓውንድ ካሳ እከፍላለው። እሷም ነገሩም ወደ ፍርድ እንደማትወሰደው ተሰማማች።እሷም ለሰጋዮ ይገባኛል ብላ ለነብስ የማይሆናትን ብር ለመቀበል ተሰማማው አለች።ከዛን ምኑም ባልታወቀ ሁኔታ ሁለቱም አካላት ሳይሰማሙ ቀሩ።
የሮናልዶ ጠበቃ ካርሎስ ኦሶሪዮ የጀርመን ጋዜጣ ዛሬ በጉዳዮ ዙሪያ ምላሻው ጠየቃቸው “ይህ ስም ማጥፋት ነው አሉ።ተጫዋቹ የተባለው ክስ ሙሉ ለሙሉ አላደረገው።ሰም የማጥፋት ዘመቻ እና ብር ያለ አግባብ ለማግኘት የተፈጠረ ታሪክ ነው” አሉ።ጠበቃውም አክለው ምንም አይነት ሰምምነት በዚህ ጉዳይ ከማንም ጋር የለንም ብለዋል።
የጀርመኑ ዴር ስቴግል ከከሳሻ የራሱን ማስረጃ ይዟ ጠበቃውን ስለ ደንበኛው ክስ ቢጠይቅም ምላሹ ሮናልዶ አላደረገውም ሀኖል።ከሳሽ በበኩሏ አሁንም የካሳዮ ብር ካልተሰጠኝ ወደ ፍትህ አመራለው ብላለች።የፖርቱጋል ጋዜጦች ተቀባይነት እና ታማኝነት የሌለው ውንጀላ ብለውታል።የስፔኑ ሙንዶ ጋዜጣ ለባርሴሎና ቅርብ መሆኑ ጉዳዮን አካብዶታል የሚሉም አሉ።ተጫዋቹ ያለው የተለያዮ የፍቅር ህይወቱ እና ቁጥብ ያለመሆኑም ግን ከጋዜጣው በላይ ችግር ፈጥሮበታል።
ምንም እንኳን የተጫዋቹ ጠበቃ ክሱን ቢያጣጥልም በድብቅ ነገሩን ለመጨረስ 300 ሺ ፓውንዱን ሊሰጡ ተሰማምተዋል ።ከሳሽም ብሩን ተቀብላ ጉዳዮን እንድዘጋላቸው ይፈልጋሉ።ሮናልዶም ጉዳዮ ረጅም አመት ሰለፈጀ በገንዘብ በድብቅ እንዲያልቅ ይፈልጋል ነው የተባለው።ከሳሽም በድብቅ እና ነገሩን ወደ ፍርድ ቤት ሳትወስደው ገንዘቡን ለመቀበል የመሰማማት ፍላጎቷ ይኖራታል ሲል ዴይሊ ሜል ነው ያሰነበበው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.