ለትግራይ ህዝብ መብት እና ነጻነት ታገልኩ የሚለው ህውሓት ባለቀ ሰአት- ከትግራይ እስከ ኬንያ!!! (ናትናኤል አስመላሽ )

ከትግራይ እስከ ኬንያ!!!

ለትግራይ ህዝብ መብት እና ነጻነት ታገልኩ የሚለው ህውሓት ባለቀ ሰአት ውስጥ የአጥፍቶ ጠፊነት ጨዋታው ቀጥሎበታል። ህውሓት ራሱ ባጸደቀው ህገመንግስት ለመጫወት የወሰኑትን በሙሉ ከጨዋታ ውጭ በማድረግ ሜዳው ውስጥ ብቻውን ይጫወታል፣ ይጫወታል ወይንስ ያብዳል ሁለቱም ያስኬዳል፣ ያብዳል የሚለውን ቃል ግን በደምብ ይገልጸዋል። ህውሓት ዋሸየ ነው ከሚለውን ህብረተሰብ ተፈጥረህ ህውሓትን መቃወም ትልቅ ሃጥያት ነው። ፍራቻው የዋሽውን ጨለማ ማብራት ሞቱ ስለሆነ ከዋሻው ከትግራይ መፈጠር ተፈጥሮም መቃወም ሁሌም ዋጋ ያስከፍላል።

ህውሓት የመድብለ ፓርቲ አገር ይኑረን ብሎ፣ ትግራይ ውስጥ ህገመንግስቱን መሰረት አድርጎ ለሚታገለው ዓረና ፓርቲ፣ በፓርቲው እና በፓርቲው አባላት ጉዳት ሲያደርስ መቆየቱ ይታወቃል። እስካሁን ድረስ ከሰላሳ በላይ አባላቶቹ ታስረው ከሰዎስት በላይ አባላቶቹ ተገድለዋል። ከስር ያለውን ፎቶ የምታዩት የወንድማችን ሕድሮም ሃይለስላሴ ነው። ባለፈው ምርጫ ትግራይ ውስጥ ድብደባ ደርሶበት ደሙ ፈሰዋል፣ ከሞትም ተርፈዋል።መስኖ ተከልክሎ የቤት እንስሳቶቹ ሞቶዋል፣ ገቢ አልባ ሆኖዋል።

ህውሓት በዚህ ብቻ ኣላቆመም፣ ኬንያ ድረስ ሄዶ ህውሓትን የሚቃወመው የትግራይ ተወላጅ እያሳደደ ይገኛል። ዮናስ ሓጎስ አብዛኛዎቻችን በማህበራዊ ሚድያ የምናውቀው የትግራይ ተወላጅ ነው። ህውሓት ዮናስ ለመግደል ያደረገው ጥረት አልተሳካለትም፣ በዮናስ ላይ ግን ከፍተኛ ጉዳት ደርሰዋል። የግለሰብ መብት አከብራለሁኝ የሚለው ህውሓት ከኢፈርት በዘረፈው ገንዘብ ግለሰብን ለመግደል ኬንያ ድረስ ሄደዋል። አሁንም ከእንቅልፍ ያልተነሳህ የትግራይ ወጣት የኢፈርት ገንዘብ የትግራይ ህዝብ ታግሎ ባመጣው ለትግራይ ወጣቶች ማስገደያ እየሆነ ነው እና ነቃ በል። የኢፈርት ገንዘብ ከሚባክንባቸው ምክንያቶች አንዱ ህውሓት ለስልጣኑ ማቆያ ሲለሚያፈሰው ነው፣ ትግራይ ለማልማት ግን ገንዘብ የለውም።

ህውሓት ከዚህም አልፈው ትግራይ ውስጥ ሆነው በማህበራዊ ሚድያ ለሚሳተፉ የትግራይ ወጣቶች በቀጥታ ስልካቸው እየደወሉ ማስፈራራትን ተያይዘዉታል። የዚህ ተጠቂው አንዱ የዓረና ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊው አቶ ዓምዶም ገብረስላሴ ነው። ስልኩ ላይ በቀጥታ በመደውል ዛቻ ያደረሱበት የማረት ሃላፊ የስብሃት ነጋ ዘመድ የሆኑት አቶ ተክለወይኒ አሰፋ ናቸው። አቶ ተክለወይኒ ኢፈርት የትግራይ ህዝብ ነው ያለህ ማነ ብለው በስብሰባ የተናገሩ የህውሓት ከፍተኛ ባለስልጣን ናቸው። እድሜ ልኩ የሚገዛ መንግስት የለም እድሜ ልኩ የሚኖር ህዝብ ግን አለ። ዮኒ አይዞህ በርታ ፈጣሪም ካንተ ጋር ይሁን። የደርሰብህን ሁሉ ለታሪክ አስቀምጠነዋል፣ ነገ ሌላ ቀን ነው።

————

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.