ኤርትራን በሚመለከት የሕወሐት “አዲስ ፖሊሲ” ምን ሊሆን ይችላል? (ዮፍታሔ)

‘በኤርትራ አዋሳኝ የትግራይ ወረዳዎች ሰዎች እየታፈኑ ይወሰዳሉ፣ ሰላም ባለመኖሩ እነዚህ ወረዳዎች በልማትም ወደኋላ ቀርተዋል’ በማለት በኤርትራ ላይ “ጠንከር ያለ ርምጃ” እንዲወሰድ ethiopiafirst የተባለው የወያኔ ደጋፊ የሚዲያ ተቋም ሰፊ የቪዲዮ ዘገባ የሠራበትና ከርሱ በፊትም በ Facebook ታዋቂ የሆኑ የወያኔ ደጋፊዎች ይህንኑ “ጠንከር ያለ ርምጃ” በተደጋጋሚ ሲያቀነቅኑት የነበረ መሆኑየሚታወስ ነው። ያንን ተከትሎም የአገዛዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ኤርትራን በሚመለከት እስካሁን የተደረገው “ተመጣጣኝ ርምጃ” ስላልሠራ ሕወሐት “አዲስ ፖሊሲ” እንደሚከተል አስታውቋል።

ከዚህ መግለጫ በኋላ የሕወሐት አገዛዝ ተከታታይ የዲፕሎማሲ ዘመቻ ላይ መሆኑን የሚጠቁሙ በርካታ እንቅስቃሴዎች እየታዘብን እንገኛለን። የቱርክ መሪ ጉብኝት፣ የሳውዲና የተባበሩት አረብ ኤምሬት ከፍተኛባለሥልጣናት ጉብኝት፣ የሱዳኑ አልበሽር ጉብኝት፣ የኳታር መሪ ጉብኝት፣ ከደቡብ ሱዳኑ መሪ ሳልቫ ኪር ጋር የተደረገ የወታደራዊ ትብብር ቃልኪዳን፣ የሕወሐት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በአልጀሪያ ያደረገውጉብኝት፣ ወዘተ በጣም በአጭር ጊዜ በተከታታይ የተደረጉ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች ናቸው።

እነዚህ ጉብኝቶችና የዲፕሎማሲ ግንኙነቶች በአጭር ጊዜና በተከታታይ የተደረጉ መሆናቸው ብቻ ሳይሆን አብዛኞቹ በመሪዎች ደረጃና በዝግ የተደረጉ ግንኙነቶች ከመሆናቸው በተጨማሪ በመግለጫቸው ላይ ሁሉምበ”ጸጥታ”ና የአካባቢውን ፖለቲካ በሚመለከት በትብብር ለመሥራት መስማማታቸውን የሚገልጹ ናቸው።

በዚሁ ተመሳሳይ ጊዜ የሳውዲ መንግሥት ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በሦስት ወር ውስጥ ወደአገራቸው እንዲመለሱ የወሰነ ሲሆን ውሳኔው ከሀገር ጸጥታ ጋር የተገናኘ እንደሆነም አልሸሸገም። ሕወሐትም መጀመሪያበኮሚኒኬሽን ሚኒስትሩ በነገሪ ሌንጮ፣ በትናንትናው ዕለት ደግሞ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቃል አቀባይ በመለስ ዓለም በኩል ኢትዮጵያውያን ከሳውዲ ወደኢትዮጵያ እንዲመለሱ ባልተለመደ መልኩ ከማስጠንቂቂያጋር እየወተወተ ይገኛል። ለ 4000 ኢትዮጵያውያን የመመለሻ ዶክመንት (Travel Document) መስጠቱን፣ ሌሎች የሚቀሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች እንዳሉና ወያኔ ለዚሁ ሲል የእዝ ጣቢያ(Command Post) እንዳቋቋመም ገልጿል። ከሳውዲ አረቢያ ተጓዥ ኢትዮጵያውያን ሕጋዊ በሆነና ባልሆነ መንገድ ትርፍን የሚያግበሰብሰው ወያኔ እነዚህን ወገኖቻችንን እንደገና ወደኢትዮጵያ እንዲመለሱመወትወቱ ከምን የመነጨ እንደሆነ ማወቅ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል።

ሌላም አለ። ወያኔ ሕዝባዊው ትግል በተፋፋመበት ጊዜ ለይስሙላም ቢሆን በሀገር ውስጥ ከሚገኙ ”ተቃዋሚ ፓርቲዎች” ጋር ለመነጋገር ፈቃደኛ በመሆን ድርድር ጀምሮ የነበረ ቢሆንም ትንሽ ሳይቆይ ግንበመጀመሪያ ድርድሩን ውይይት ነው በማለትና በማቃለል በኋላም ያለምንም ውጤት ድርድሩ እንዲበተን በማድረግ ቋጭቶታል። ከተወሰኑት ጋር ከዚያ ወዲህ የቀጠለ ውይይት ሊኖር ይችላል ቢባልም ከይስሙላእንደማያልፍ ለመገመት አያስቸግርም። ይህን ያነሣሁት የሕወሐትን የወቅቱን መንፈስ (Mindset) ለማሳየት እንጂ ድርድሩ ቢሳካ እንኳን የሚፈለገውን ለውጥ ያስገኛል በማለት አይደለም።

እንግዲህ እነዚህንና ሌሎችንም ተመሳሳይ እንቅስቃሴዎችን ስንመለከት ነው የሕወሐት “አዲስ ዕቅድ” ምን ሊሆን እንደሚችል ለመጠየቅ የምንገደደው። የሕወሐት አዲስ ዕቅድ በቀጥታ የሚመለከተው ኤርትራን ሊሆንቢችልም በተጓዳኝ ከኢትዮጵያውያንና ይልቁንም ከአማራው ተጋድሎ ጋራ ቀጥተኛ ግንኙነት ሊኖረው ስለሚችል ስለዕቅዱና ሊያስከትለው ስለሚችለው ውጤት አስቀድሞ ማወቅ ለመዘጋጀት ይጠቅማል።

ለመሆኑ የሕወሐት “አዲስ ዕቅድ” ምን ሊሆን ይችላል? ለሚለው ጥያቄ በአጭሩ ሦስት መላ ምቶችን ማቅረብ ይቻላል። “አዲሱ ዕቅድ” ለፕሮፖጋንዳ ፍጆታ ብቻ ነው የሚል፣ ከኤርትራ ጋር ዕርቅ ማድረግ ነውየሚልና በኤርትራ ላይ “ጠንካራ ርምጃ” መውሰድ ነው የሚል ናቸው።

የመጀመሪያው በሕወሐት አንጃዎችና በትግራይ ብሔረተኝነት አቀንቃኞች ዘንድ በኤርትራ ላይ ጠንከር ያለ እርምጃ እንዲወሰድ ከፍተኛ ግፊት በሕወሐት አመራር ላይ ሲደረግ ስለቆዬ አመራሩ ለዚህ ጥያቄ የይስሙላመልስ በመስጠት ይህን ግፊት ለማርገብ ብቻ ያደረገው የፕሮፖጋንዳ ፍጆታ ነው የሚለው ነው። ከሕወሐት የቅጥፈትና የቀላማጅነት ታሪክ ይህ ሊሆን አይችልም ባይባልም በተከታታይ ከሚደረጉት የዲፕሎማሲግንኙነቶችና በሕወሐት ላይ እየጠነከረ ከመጣው የአገር ውስጥና የውጭ ተቃውሞ በመነሣት ወያኔ አሁን የተነሣበትን ተቃውሞ በፕሮፖጋንዳ ብቻ መፍትሔ ሰጥቶ ለማለፍ ያስባል ለማለት አስቸጋሪ ነው። አገዛዙምያውቃል ሕዝቡም ይህን ጠንቅቆ ያውቃል።

ይህ ከሆነ የቀሩት ሁለቱ አማራጮች ዕርቅና “ጠንከር ያለ ርምጃ” የሚሉት ይሆናሉ።
በኤርትራ ላይ “አዲሱ ዕቅድ” ዕርቅ ነው የሚሉ ወገኖች ከሚያቀርቧቸው ምክንያቶች ጥቂቶቹ ከኢትዮጵያ ጋር የዲፕሎማሲ ግንኙነት ከሚያደርጉት አገሮች ሁሉም ባይሆኑ አብዛኞቹ (ሳውዲ፣ የተባበሩት አረብኤምሬት፣ ኳታር፣ ሱዳን) ከኤርትራም ጋር የጠበቀ ወዳጅነት ያላቸው መሆኑን በመጥቀስ ሲሆን (የሱዳኑ መሪ ከኢትዮጵያው ጉብኝቱ ቀጥሎ ወደኤርትራ ማቅናቱን ይጠቅሳሉ) ወያኔ በአገር ውስጥ ካለበት ውጥረትየተነሣ በኤርትራ ላይ የኃይል አማራጭ ለመውሰድ አይሞክርም የሚሉ ናቸው። የወያኔ ደጋፊ በመሆኑ የሚታወቀው “ሪፖርተር” ጋዜጣም በትናንትናው እትሙ ስለኳታሩ መሪ ጉብኝት ባወጣው ዘገባ ማጠቃለያ ላይየሚከተለውን አስፍሯል፦

“በነዳጅ ሀብቷ የምትታወቀው ኳታር ኤርትራ ከሱዳንና ከጂቡቲ ጋር ዕርቅ እንድትፈጥር ጥረት ያደረገች ሲሆን፣ ከኢትዮጵያ ጋር የጀመረችው ግንኙነት ሙቀት በዚሁ ከቀጠለ ኢትዮጵያንና ኤርትራን የማስታረቅፍላጎት እንዳላት የፖለቲካ ተንታኞች ይናገራሉ።”

ከዚህም በተጨማሪ በሕወሐትና በሻእቢያ መካከል ከጦርነቱ በኋላ የተተካው ግልጽ ጦርነትም ሆነ ሰላም የሌለበት (No war, no peace) ሁኔታ ለሁለቱም (ለሻእቢያና ለወያኔ) የተመቻቸው ስለሆነ እንዲቀጥልይፈልጉታል የሚሉ አሉ። ስለዚህ አዲሱ ዕቅድም ሆነ የሚታየው ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴ ከጸብ ይልቅ ወደድርድርና ከተቻለም ወደዕርቅ ለመሄድ የሚደረግ ጥረት ነው ባይ ናቸው።

በሌላ በኩል የሕወሐት “አዲስ ዕቅድ” የሻእቢያን አቅም በእጅጉ ሊያዳክም ከሚችል ጠንከር ካለ ወታደራዊ ርምጃ ጀምሮ ሻእቢያን እስከማስወገድ ሊደርስ እንደሚችል የሚከራከሩ ሰዎች ምክንያታቸውን የሚያቀርቡትበሚከተለው መንገድ ነው። 

በመጀመሪያ ነገር በኢትዮጵያ ውስጥና በአካባቢው ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ እንዲሁም ዓለም አቀፍ ሁኔታዎችን ማጤን ያስፈልጋል። እነዚህ አንዳቸውም እውነተኛ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.