ኢትዮጵያዊ_ነኝ! – በዕውቀቱ ስዩም


ኑሮ ቢገፋኝ የማልወድቅለት
እንደ አክሱም ግንብ እንደቦሃ አለት
የመከራ አለት ያልነቀነቀኝ
ለሙሾ ሲያጩኝ ቅኔ የምቀኝ
በግራ ሲሉኝ የምገኝ በቀኝ
ኢትዮዺያዊ ነኝ
.
ከዋርካ ባጥር ከንቧይ ተልቄ
ከፀሃይ ባንስም ከኩራዝ ልቄ
ከምድረ በዳ ውሃ አፍልቄ
ጥሜን የምቆርጥ በፍኝ ጠልቄ
ኢትዮዺያዊ ነኝ
.
ልክ እንደ ቻይናው የትም ሳልረባ
እንደ እንግሊዙ ሳልሰራ ደባ
እንደ አሜሪካው በቁም ሳልሰባ
በመጠን ኖሬ አፈር ምገባ
ኢትዮዺያዊ ነኝ
.
ግትር ጠላቴን ባጭር አንካሴ
እራስ ምታቴን በዳማከሴ ነቅዬ ምጥል
አገር በነገር የማብጠለጥል
ነገር በነገር የማብጠረጥር
ኢትዮዺያዊ ነኝ
.
እንደ ማህረብ ቤቴን በኪሴ
እንደ ንቅሳት ተስፋን በጥርሴ
ይዤው የምዞር ከቦታ ቦታ
በሰበብ ኬላ የማልረታ
ኢ..ት..ዮ..ጵ..ያ..ዊ…. ነኝ!
—-//——-
© በዕውቀቱ ስዩም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.