ይህን ነበር የምፈራው! – ብሥራት ደረሰ – ከአዲስ አበባ

ማስታወቂያ!

የመጀመሪያው የዐማራ ዓለም አቀፍ ጉባኤ –
The First International Amhara Conference May 14 2017

ወያኔን እግዜር ይይለት! የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች እንደሆኑ የሚታመኑ ምዕራባውያንም ይሁኑ ምሥራቃውያን እነሱም እግዜር ይይላቸው! በተለይ በተለይ የነዚህ የውጭ ምንደኛ ጠላቶቻችን አሽከር በመሆን ላለፉት 42 ዓመታት ኢትዮጵያን እንደደሮ ሲበልቱና ሕዝቧን እንደአሻሮ ሲቆሉ ሀብት ንብረቷንም በግላጭ ሲዘርፉና ወደጎሬኣቸው ሲያጓጉዙ የነበሩ ሰሜነኛ ናዚዎችና ፋሽስቶች ዘር አይውጣላቸው፡፡ የጀመሩት እንደጪስ በንነውና እንደጤዛ እረግፈው ወደታሪክ ትቢያነት የመለወጥ ትንቢታዊ የመጨረሻ ዕጣ በቅርብ ጊዜ ተጠናቆ ሀገራችን ነፃ እንድትወጣ ፈጣሪ ይርዳን፡፡ አሜን፡፡

ይህን ነበር የምፈራው፡፡ ይህ እንዳይመጣም ከልብ ከመጸለይ ጀምሮ የአባትነት ምክሬን ስሰጥ ቆይቻለሁ፡፡ ግን ምኞቴ አልተሣካም፤ ጸሎቴም አልሠመረም፡፡ እናም የፈራሁት ደረሰ፡፡ እንግዲህ ይቺን ምሥኪን ሀገር ማነው “ኢትዮጵያ” ብሎ የሚጠራት? ሀገሪቷንና ሕዝቧን ታሪክ አልባ አድርጎ በታትኖ ለማስቀረት ቀደም ካለ ጊዜ ጀምሮ የተጠነሰሰው ሤራ ፍሬ እያፈራ መሆኑን ባይናችን በብረቱ እየታዘብን ነው፡፡ ከዚህ ሸርና ተንኮል ተጠቃሚ የሚሆነውን ደግሞ ዕድሜ የሰጠው ያየዋል፡፡ በርግጠኝነት መናገር የሚቻለው የገጠጠ እውነት ግን ወያኔ በሸረበው በአጠቃላይ ኢትዮጵያንና በተለይ ደግሞ አማራን የማጥፋት ዘመቻ በምንም ዓይነት መንገድ ትግራይም ሆነች ትግሬዎች ተጠቃሚ ሊሆኑ አይችሉም – የአሁኑን መሬትን እንኳን ለመርገጥ እስኪጠየፉ ድረስ በጥጋብ መቦረቃቸውንና ኅሊናን በሚያስት ዲያብሎሣዊ ጥጋብ መነብረራቸውን አትመልከቱ፡፡ ማየት ዛሬን ብቻ ሣይሆን ትናንትንና ነገንም ጭምር ነው – ታያለህ ይህ ሁሉ ተምችና አንበጣ የሚደበቅበትን የሚያጣበት ቀውጢ ቀን ይመጣል፡፡ አሁን ማሰቢያውን ስለተነጠቀ የሚሠራውን አያውቅም፤ የሚሠሩትን የማያውቁት አይሁዶች የገዛ ሥጋቸውን ክርስቶስን ገርፈው እንደሰቀሉት የሚሠሩትን የማያውቁት ወያኔ ትግሬዎችም የገዛ ወንድማቸው አማራ ላይ ተኝተው ወደላይ እያስታወኩ ነው፡፡ የገማ ትውከታቸው ሲመለስ ከሥር በተኛው አማራ ላይ ሣይሆን በነሱ ላይ እንደሚያርፍ አልገባቸውም፡፡ ደንቆሮ የሚሰማው ሲሞት ብቻ ነው፡፡

ሳስበው ሕወሓት የተሳሳተው መሠረታዊ ቁም ነገር አለ፡፡ የቀመር ወይም የፎርሙላ ስህተት ፈጽሟል ብዬ አምናለሁ፡፡ ልብ አድርጉ – በአሁኑ ሰዓት ትግራይ ውስጥ የሚገኙ ተጋሩ ከሁለት ሚሊዮን እንደማይበልጡ በስፋት እየተነገረ ነው፡፡ በሌላ በኩል ወያኔ የአማራን ቁጥር በተለያዩ መንገዶች ሲቀንስ የትግሬን ግን ከመቼውም ጊዜ በላይ እንዲጨምር አድርጓል፤ እነዚህ ጉዶች የሕዝብ ብዛት መቀነስ እያስጨነቃቸው እንደሚገኙት አውሮፓውያን ለሚወልዱ ትግሬዎች የማበረታቻ ገንዘብ ሳይሰጡ የሚቀሩ አይመስለኝም፡፡ ያም ሆነ ይህ የትግሬዎች የአሁኑ ብዛት በትልቅ ግምት 10 ሚሊዮን ይሆናል ብንልና “ስምንቱ ሚሊዮን የት ገባ?” ብለን ብንጠይቅ መልሱ ለብዙዎቻችን ሩቅ አይደለም፡፡ “ጀምበር ሳለች ሩጥ፣ አባት ሳለ አጊጥ” እንደሚባለው ይህ ሁሉ ትግሬ የወንድሞቹንና የእህቶቹን ሀብትና ንብረት እንዲሁም ገንዘብ እየዘረፈ የሚኖረው በሁሉም የኢትዮጵያ ግዛቶች ውስጥ በአንደኛ ደረጃ ዜግነት እንደመዥገር ተሰግስጎ ነው፡፡ ገልማጭ የለው ቆንጣጭ  ዕድሜ ለእናት ውድቡ ሕወሓት “መዐሪና ሰኮሪና ዕድመ ንስዉዓት አህዋትና” እያለ – ራሱ ህግ አውጪ – ራሱ ህግ ተርጓሚ – ራሱ ህግ አስፈጻሚ – ራሱ ከሳሽ – ራሱ ዳኛ – ራሱ መንግሥት – ራሱ ዲፕሎማት – ራሱ ሰጪ – ራሱ ነሽ – ራሱ አሣሪ – ራሱ ገራፊ – ራሱ አዳይ ራሱ ደልዳይ – ራሱ ፖሊስ – ራሱ መከላከያ ፤  ራሱ ሁሉንም ሆኖ የመላ ሀገሪቱን አንጡራ ሀብት ያለአንዳች ተቀናቃኝ እየቦጠቦጠ ይገኛል – በርግጥ ሁሉም ትግሬ (እኩል) ተጠቃሚ ካለመሆኑም በላይ በትምህርት ባለመግፋት፣ ወደ ማዕዱ የሚያስጠጋው ዘመድ አዝማድ በማጣት፣ የአበላል መንገዱን ባለማወቅ ወይም ምናልባትም በይሉኝታና በመሳሰሉ ምክንያቶች የተነሣ ብዙ ትግሬዎች እየተቸገሩ እንደሚኖሩና እንዲያውም እንደኛው ለልመናና ለስደት እንደሚዳረጉም እናውቃለን፡፡ ይህ ከፍ ሲል የተጠቀሰው የትግሬዎች ወቅታዊ ሁኔታ ታዲያ – ከትግራይ በዘመቻ መልክ የመውጣታቸውና በሌሎች አካባቢዎች ወንድሞቻቸውን እያባረሩና ንብረታውን እየቀሙ የመሥፈራቸው ሁኔታ – ከሕወሓት ነባር የትግራይ ሪፓብሊክ መሥረታ ጋር ይጋጫል፡፡ ለምሣሌ ነገ ጧት ወያኔ መቀሌ ላይ ሪፓብሊኳን መሠረትኩ ቢል ሰው ከሌለ ድንጋይ ሊያስተዳድርበት ነው በሪፓብሊኩ? ወይንስ ሌላው ወገናቸው ጉሮሮ ላይ አጥንት እየሻጡ በነሱ ጉሮሮ ጮማና ዊስኪ የሚያንቆረቁሩ ዘበናይ ትግሬዎች ያፈሩትን ሀብትና ንብረት ትተው ለሪፓብሊኳ ኅልውና ሲሉ ወደጭንጫ መሬታቸው ሊሄዱ ይሆን? በማንም ይሁንባችሁ – ስትፈልጉ በእግዜር ካልፈለጋችሁም በነሱው አምላክ በሰይጣን –  እንደመዥገር ተጣብቀው እዚሁ አብጠው ይፈነዷታል ወይም የሚመጣባቸውን ቅጣት ሁሉ እዚችው ይቀበሏታል እንጂ ከእንግዲህ ወደ ትግራይ አይሄዱም – መተላለፊያ ኮሪደር ተፈጥሮላቸው በሰላም የመሄድ ዕድሉን እንኳን ቢያገኙት ማለቴ ነው፡፡ እዚያ እኮ እሰው ትከሻ ላይ ፊጥ ብሎ እንዲህ እየተምነሸነሹና እየተዘባነኑ መኖር የለም፡፡ ጌትነታቸው እዚህ እንጂ እዚያማ ቢሄዱ ጥንት ይታወቁበት የነበረውና አሁን ግን እነሱም ስሙን ሣይቀር የረሱት የዱሮው ቀን አውጪ ኩንቲ እንኳን በዚህ ዘመን ላይኖር ይችላል፡፡ ስለዚህ ሕወሓት ፖሊሲውን ማስተካከል አለበት፡፡ ለማንኛውም ከፎከረ ቀርቶ ከወረወረ የሚያድነው የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በቶሎ ይድረስልንና የምንተባበርበትን ልብ ሰጥቶን አንድ በመሆን ከዚህ የወያኔ ግፍና በደልና የጠላቶቻችን  ኢትዮጵያን የማፈራረስ ድብቅ ሤራ በአፋጣኝ እንገላገል፡፡ ከተባበርን ችግራችን ቀላል ነው፡፡ ካልተባበርን ግን ለነሱ እንደተመቸናቸው እንኖራለን፡፡ እነሱም ብልጥ ሆነው ይህን ሁሉ ሕዝብ እንደከብት ሲነዱት ሳይ በውነቱ እጅግ ይገርመኛል፡፡ ዕዝ እኮ ነው፡፡ ዕዝ መጥፎ ነው፤ አታስቀረውምም፡፡ በጸሎትና በምህላ እንዲሁም በተባበረ ክንድ ግን ልታለዝበውና ልታመክነውም ትችላለህ፡፡ እኛ የሳትነው ይህን ነው፡፡

በመሠረቱ አማራ አይፈረድበትም፡፡ ራሱን ለማዳን የሚወስደው እርምጃ ሁሉ ቢያስመሰግነው እንጂ አያስወቅሰውም፡፡ በተለይ ላለፉት 26 ዓመታት በወያኔ ትግሬ አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቷል፡፡ ስለሆነም ከጥፋት ለመዳን ራሱን ሲያደራጅና ለመታገል ሲቆርጥ “አትደራጅ” ብሎ መውቀስ አልፎ ተርፎም መዝለፍ ከባድ ስህተት ነው፡፡ ለምን ወደዚያ ደረጃ እንደተገፋ ተረድቶ የአማራውን ትግል ከማገዝና ከዕልቂት ከመታደግ ይልቅ እንዳይንቀሳቀስ መንገድ መዝጋት በነበረው የዕልቂት መንገድ ተጉዞ ዘሩ እንዲጠፋ ከወሰኑበት ከወያኔዎች ተለይቶ አለመታየትን ያስከትላል፡፡ አማሮች ለዘመናት ተኝተው ነበር፡፡ በተኙበት ተጨፈጨፉ፡፡ ወያኔ ደግሞ በተኙበት መጨፍጨፍ አሣምሮ ያውቅበታል፡፡ ከደደቢት ጀምሮ የዳበረ ልምድ አለው፡፡ የራሱን ወገኖች ሳይቀር እንደተኙ እየጨፈጨፈ ነው ለአራት ኪሎ ያልታሰበና ፍጹም ያልተጠበቀ ድግስ የበቃው፡፡ ባዶ ቤተ መንግሥት ሲገኝ ዱሮውንስ ማን ዝም ብሎ ያልፈዋል? መንግሥቱ ኃይለ ማርያም እግዜር ይይልህ!…

የፈራሁት መድረሱ ካልቀረ አሁን የሚያሳስበው አማራው ማን ነው? የሚለው ትልቅ ጥያቄ ነው፡፡ ይህ ጥያቄ ማንም በቀላሉ ሊመልሰው የማይችል ከባድና ጠንቀኛ ጥያቄ ነው፡፡ በዚህ ጥያቄና በመልሱ ውስብስብነት ምክንያትም ይመስለኛል የአማራ መሰባሰብ አስቸጋሪ ሆኖ አማራው እስካሁን ድረስ ለወያኔ ጊሎቲንና ኦሽትዊዝ እንደተጋለጠ፣ ዘሩም ከምድረ ገጽ እንዲጠፋ በሁሉም ጠላቶቹ ዘንድ እንደተሞከረ ዘመናት የተቆጠሩት፡፡ “አማራ ነኝ” የሚልን ሰው “አማራ አይደለህም” ብለን የምንሞግትበት አንድም ተጨባጭ የሆነ ሰበብ ወይም አመክንዮ የለንም፡፡ አንድ ሰው “ትግሬ ነኝ” ቢል ትግርኛ መቻሉን፣ በየትኛው የትግራይ ክፍለ ሀገር መወለዱን… ልንጠይቅና የአካባቢው ሰው ከሆን የልዩ ልዩ ቦታዎችንና ሰዎችን ስሞች በማንሳት ልናመሳክር እንችላለን፡፡ ጉራጌ ወይንም ኮንሶ ነኝ የሚልንም እንደዚሁ፡፡ እነዚህኞቹ ቀላል ናቸው፡፡ ደምን የማነፍነፍ ጉዳይ ነው፡፡

አማራ ነኝ የሚልንስ? አማራ እንዳልሆነ ልናውቅበት የሚያስቸለን የምርመራ ዘዴ በፍጹም ልናገኝ አንችልም – ፓስተር ሆስፒታልም ሆነ ደደቢት ላይ ሰሞኑን የተመረቀው “የመለስ ዜናዊ መታሰቢያ የብሔር ብሔረሰቮች ደምና አጥንትን ማበጠሪያና መለያ ተቋም” እንኳን የአማራነትን ደም መለየት አይችሉም፡፡

አማርኛ ቋንቋ እንደሆነ ከሞላ ጎደል የሁሉም ቋንቋ ነው – የሚገርመው ወያኔ እንኳን መንግሥት ከሆነ ወዲህ ላለፉት ሁለትና ሦስት አሠርት ዓመታት እንደ እባብ አናት አናቱን ቢቀጠቅጠውም – ባሏን የጎዳች መስሏት ምንትስ አደረገች እንደምትባለው ሴት ወይዘሮ – አማርኛን የሚናገረው የሕዝብ ቁጥር እየጨመረ እንጂ እየቀነሰ ሲሄድ አይታይም (እርግጥ ነው ለአማርኛ ቋንቋ አድልቼ ሣይሆን የጋራ መግባቢያ አስፈላጊነት ያለው ጥቅም ተፅዕኖ አሳድሮብኝ ይህ አባባሌ ከእውነት ይልቅ ለስሜት ሊቀርብ እንደሚችል እኔ ራሴም እገምታለሁ – እናም ለግምቴ ቀላል ግምት ባልሰጠውም የአማርኛን ወቅታዊ ሀገራዊ ፋይዳ ይበልጥ ለመገንዘብ የሆነ ጥናትና ምርምር ቢደረግ አይከፋም፡፡)፡፡  የአማራ ዘር በየቦታው የተበተነ ነው፡፡ በክፍለ ሀገር ያልተወሰነ፣ በጎሣና በነገድ ያልተዋቀረ፣ አልፎ አልፎ እንደሚስተዋለው በመንደር ልጅነት ካልሆነ በስተቀር እሳት እንደተጠጋው የናይሎን ጨርቅ በአማራነት በቀላሉ የማይጨማደድና እንደ አንዳንድ ጉዶች ወደጢሻና ጉድባ ወርዶ የማይኮማታተር በተፈጥሮው ቦርቃቃ አስተሳሰብና አመለካከት ያለው ሕዝብ ነው፡፡  እውነቴን ነው – የዘረኝነትን አደገኛ ልክፍት ተቋቁመው “ሰው” የሆኑ ትግሬዎችን ፈልጌ ለማግኘት ሺ(ህ) ሚሊዮን ጊዜ ሞክሬ ቁጥራቸው ከሁለት ሊያልፍልኝ አልቻለም – ፕሮፌሰር መሰፍንንም ከዚህ ነጥብ አንጻር የማስታውስላቸው አንድ አባባል አላቸው፡፡ ደግሜ ደጋግሜ ዐይኔንም ጨፍኜ ጆሮየንም ደፍኜ አሰብኩ – ግን እነዚያው ሁለት ሰዎች ብቻ ናቸው ወደ አእምሮየ የሚመጡት፡፡ ዘራቸው ይባረክ፡፡ በውጭ ሀገር ነው ያሉት፡፡ ስማቸውን ታሪክ ይጥራው እንጂ አሁን አልናገርም፡፡ ሌሎች እዚያና እዚህ የሚረግጡ ግን ጥቂት የማይባሉ የሁለት ዓለም ሰዎችን – የሌሊት ወፎችን – ልብ ይስጣቸው፡፡ ዘር አስቸጋሪ ነው በውነቱ፡፡ ዘር ከልጓም እንደሚስብ ለመረዳት በአንድ ጎኑ ትግሬ የሆነ አንድ የቅርብ ጓደኛየን አኳኋን ልጠቅስላችሁ እችላለሁ – ከልቡ  እንደሚወደው ጧት ላይ የነገረህን የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ በወያኔያዊ አመለካከት በተቃኘ በአንድ ራስ ሁለት ምላሱ የጭቃ ጅራፉን ሲያወርድበት ለመስማት ለደቂቃዎች ብቻ መታገስ ይኖርብሃል፡፡ ብዙዎቹ ወገኖቼ የዘሬን ብተው ያንዘርዝረኝ ዓይነት ናቸው፡፡ ለዚህም ነው ዘር መጥፎ ነው መባሉ፡፡ ከዚህ አሽክላና ሳይገድል የማይለቅ የብልቃጥ መርዝ የራቀ ብፁዕ ነው፡፡ እኒያ ወዳጆቼ በራሳቸው ሣይሆን በፈጣሪ ምርጫ በትግሬ ቤተሰብ ውስጥ ተወልደው ሲያበቁ “ትግሬነቴ ከኢትዮጵያዊነቴ በልጦ ለጎሣየና ለሆዴ ስል ኅሊናየን አልሸጥም!” በማለት ምርጥ ዜጋ ለመሆን በመብቃታቸው አርአያነታቸው ዘላለማዊ ነው፡፡

በተረፈ በሚሊዮኖች ትግሬዎች የሚገፋ በዘርና በአጥቢያ የመጨማደድና የመኮማተር መጥፎ ጠባይ ወደ አማራውና ወደ ኦሮሞው እንዲሁም ወደሌሎች ዘሮች ከተሰራጨ ኢትዮጵያ ወደማታንሠራራበት እጅግ አደገኛ ሁኔታ ውስጥ እንደምትገባ ስናሟርት የባጀን ብዙ ሰዎች እንደነበርን የሚታወስ ነው፡፡ መፍትሔውንም ስንጠቁም ነበር፡፡ ግን ሁሉም ነገር የጨረባ ተዝካር ሆነና ሰሚ ጠፍቶ ይሄውና አንዱ የኢትዮጵያዊነት ያማረ ሠበዝ ራሴን በነገዴ ላደራጅ እያለን ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ የኔ ስሜት ድብልቅ ነው፡፡ ደስ ይለኛል – ደስ አይለኝምም፡፡ ይህን አይ/አዎ አወዛጋቢ ስሜት ማስረዳት ለቀባሪ እንደማርዳት ስለሚሆን ልተወው፡፡

ለማንኛውም አማሮች ምርጫ አጥታችሁ በገባችሁበት ለእናንተ የማይመጥን እጅግ ጠባብ ካባና ቀሚስ ውስጥ ተዘናግችሁና በቀቢፀ ተስፋ ተውጣችሁ ወያኔያዊ ካባውም ሞቋችሁ በዚያው እንዳትቀሩ ተጠንቀቁ፤ የብዙዎች ተስፋም ናችሁና በደረሰባችሁና በሚደርስባችሁ በደል ተማርራችሁ ሌሎችን እንዳትዘነጉ፤ የጉዳቱ ደረጃ ይለያይ እንጂ መበዳደል በአንድ ማኅበረሰብ ውስጥ የነበረና ያለ ነው፡፡ በብልኃትና በአስተዋይነት በመጓዝ የተበላሹ ነገሮችን ማስተካከል እንደሚቻል ደግሞ የታወቀ ነው፡፡ ስለሆነም ትኩረታችን ይበልጡን የተወለጋገዱ ነገሮችን በማስተካከሉ ዙሪያ እንዲሆን መጣሩ ጥሩ ነው፡፡ እነዚህ ከይሲዎች በተለሙት መንገድ ብዙም እንዳንገፋበት ማስታወስ እወዳለሁ፡፡ ከጉዳት በስተቀር ጥቅም የለውም፡፡

አንድ አዲስ ነገር በቀላሉ አይለመድምና እኔን የመሰሉ ብዙ “አማሮች”/አማሮች በተወሰነ ደረጃ እንቅፋት ሊሆኑባችሁ ይችላሉ፡፡ ዝም ብለው ማለቅን መርጠው ሳይሆን ሁሉም ነገር ተወነባብዶባቸው ነውና በነሱም ብዙም አትፍረዱባቸው፡፡ ይሄ የመሆንና ያለመሆን ሼክስፒራዊ ጥያቄ ትልቅ ራስ ምታት ነው፡፡ ቤተሰባዊ አስተዳደግና ማኅረሰብኣዊ ወግና ልማድ ያስርህና መሆን የሚያምርህን ነገር መሆን እየፈለግህ ሳትሆነው ትቀራለህ፡፡ መሆን የምትፈልገውን ሳትሆን በመቅረትህ ምክንያት የሚደርስብህ ጉዳት ተጠናክሮ ቀጥሎ የችግርህ እስከማዕዜኑነት ሲያንገላታህ ደግሞ በ“ወይ ያኔ!” ለቁጭት ትዳረጋለህ፡፡ ይህን የ“ሰፊነትና የድምበር የለሽ ታጋሽነት” ተፈጥሮህን ተረድቶ ወዳንተ ሜዳ የሚመጣ ሲጠፋና ባዶህን መቅረትህን ስታስብ ደግሞ የባሰውን ትበሳጫለህ፡፡ የኔን መሰሎች ችግር በዚህን እሳቤ ዙሪያ የሚጥመለመል ይመስለኛል – እውነቱን አጥተነው ሳይሆን ነገሮችን መረዳት የምንፈልገው እኛ በምንፈልገው የስብስቴ ዘመን አስተሳሰብ እንጂ ዘመኑ በተለመው እፉኛታዊ የአስተሳሰብ ዘይቤ ባለመሆኑ ነው፡፡ የአይ/አዎ -ኣችን ማጠንጠኛም ይህ ትርጉም የለሽ የሁለት ተጻራሪና ተጠፋፊ ዓለማት ልዩነት ነው፡፡ …

እናንተ አማራነትን በቁጪት ለማራመድ የቆረጣችሁ ወገኖች ግን መነሻችሁ የአማራው መገፋትና ቀን በሰጣቸው እባብ ወያኔዎች እየተነደፈ ማለቅ ስለሆነ ዓላማችሁ ፍትሃዊ ነውና እግዜር ከእናንተ ጋር ይሁን፡፡ ከስብሰባና ከመግለጫ ባለፈም ገንዘባችሁንና ዕውቀታችሁን አስተባብራችሁ አሁን በሕይወትና በሞት መካከል እየተንጠራወዘ የሚገኘውን አማራ በአፋጣኝ ለማዳን ነገ ዛሬ ሳትሉ ተባብራችሁ ተነሱ፡፡ መንገዳችሁ ሁሉ ቀኝ በቀኝ እንዲሆን ከፈለጋችሁ ደግሞ እንቅስቃሴያችሁ እንደሰይጣኖቹ ወያኔዎች በጭካኔና በበቀል ስሜት ሳይሆን በርህራሄና በእውነት ላይ የተመሠረተ ይሁን፡፡ “ዐይን ለዐይን፣ ጥርስም ለጥርስ” በሚለው የሀሙራቢ ህገ ኦሪት መመራት ዳፋው ምን ሊሆን እንደሚችል ተረድታችሁ ጉዟችሁ አስተዋይነትና ጥበብ የተሞላበት ይሁን፡፡ ይህን አሰባሰብ እንደታክቲክ እንጂ እንደ ግብ እንዳትወስዱት ደግሞ እንደ አንድ የአማራ ማኅበረሰብ አባል አደራ እላለሁ፡፡ አማራ በአማራነት የመደራጀት ተፈጥሯዊም ይሁን ሰው ሠራሽ ጠባይ ስለሌለው የኢትዮጵያ ጉዳይ ከወያኔዎች እጅ ወጥቶ መልክ እስኪይዝ ድረስ ብቻ በመለስተኛ መርሐ ግብርነት የአማራነትን የመታገያ ሥልት በጊዜያዊነት ብትይዙ የኃጢኣቱ ሥርየት ከሁለት አቡነዘበሰማያት ባልዘለለ የንስሃ ቀኖና የሚገኝ ይመስለኛልና እምብዛም የሚያስወቅሳችሁ አይሆንም፡፡ ከዚያ በኋላ ግን ይህን ቅንቅንና ተባይ የሚበዛበትን የነገድ አደረጃጀት ትታችሁ በአንዲት ሀገር የጋራ ዜግነት ኢትዮጵያችሁን አሳድጉ፡፡ በእስካሁኑ የዓለማችን ታሪክ በጎሣና በነገድ የዘረኝነት ቅኝት ተቧድኖ ወይም በሃይማኖትና በፆታ ተደራጅቶ አገርን ያቀና አንድም ፓርቲ ወይም ቡድን የለም፡፡ የጥፋት ኃይሎች ቂላቂሎችን በቀላሉ የሚያገኙትና በአምባላይ የስሜት ፈረስ ደንገላሣ እያስጋለቡ የንጹሐንን ደም የሚያፈሱት ዘርንና ሃይማኖትን በመሣሪያነት ሲጠቀሙ ነው፡፡ ዘርና ሃይማኖት ደምን በቀላሉ ስለሚያሞቁ – እምነትን እንጂ ዕውቀትንና ጥበብንም ስለማይሹ ምክንያታዊነትን በስሜት ጽላሎት ይጋርዱና ሰውን ዐውሬ ያደርጋሉ፡፡ ዓለማችን የተለከፈችው ደግሞ በነዚህ ደዌያት ነው፡፡

ትልቁ ተግዳሮታችሁ ሊሆን የሚችለው አማራነት አጥር ስለሌለው በዚህ ክፍተት ተጠቅመው ጉዳት የሚያደርሱባችሁ ወገኖችን የመከላከሉን ጥበብ የመላበሱ ጉዳይ ነው፡፡ የአማራነት ስሜት ከራሱ ከብዙ አማራ እንኳን ሩቅ በሆነበት ሁኔታ የአማራን ብሔርም በሉት ጎሣ በአማራነት ማሰባሰቡ ከባድ ነው – ክብደቱ ደግሞ እንኳንስ ወደ ተግባሩ ገብተውበት ገና ሲያስቡት ጭንቅላት ያዞራል፡፡ አማራ በኢትዮጵያ ውስጥ እንደወተት ሊመሰል ይችላል – ያልገባበት ጓዳና ጎድጓዳ ስለሌለው ተሰበጣጥሯል፤ መሰበጣጠሩም በልዩነት በማያስታውቅ ሁኔታ ነው፡፡ በአንጻራዊነት ደግሞ ሌሎቹ – በተወሰነ ደረጃ ኦሮሞን ሳይጨምር – እንደዘይት ሊመሰሉ ይችላሉ – “እነእንቶኔነታችንን ጠብቀን ይዘናል” የሚል ተኩራሮት ያላቸው ብዙ ጎሣዎች አሉ፤ ለዚህም ነው ከሁለትና ምናልባትም ከአሥር የማይበልጡ እውነተኛ ኢትዮጵያውያን ትግሬዎች የሚገኙበት ብሔረ ተጋሩ አማራን በልዩ ዘርነት – በጭራቅነት – ፈርጀው ይህች ለነሱ ብቻ ቀጭን ወርቃማ ዘመን ሳታመልጣቸው እቀየው ድረስ በመዝመት ጭምር አናት አናቱን ባልተወለደ አንጀታቸው እየቀጠቀጡት የሚገኙት፤ ይህ ነገር ሀሰት ነው የሚል ወገን ካለ “ያሳዝነኛል” ከማለት ውጪ ክርክር ውስጥ አልገባም – ዋጋ የለውምና፤ (ከንቱ) ሰው ማመን የሚፈልገውን ብቻ ያምናል፡፡ ዛሬ የአማራው ሀብትና ንብረት በትግሬዎች ቁጥጥር ሥር ነው የሚገኘው – ነፍሱም ጭምር፡፡ … ቢበቃኝስ ጃል! ምን ዓይነት አስለፍላፊ ዘመን ገጠመነ እባካችሁ፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.