ጦማሪያኑ እና ጋዜጠኞቹ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸው

Zone-9-trail-Tadias-Magazine-cover-2

በዛሬው እለት በልደት ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት የቀረቡት የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን እና ጋዜጠኞች ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸው፡፡ ችሎቱ በዛሬው እለት ተሰይሞ የነበረው ጦማሪያኑ እና ጋዜጠኞቹ ታህሳስ 7 ቀን 2007 ዓ.ም ክስሳቸውን በማስመልከት ባቀረቡት አስተያየት ላይ አቃቤ ህጉ ክሱን አሻሽሎ እንዲቀርብ በተወሰነው መሰረት የነበረ ቢሆንም ዛሬ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት በተሰየመው ችሎት ላይ አቃቤ ህጉ ክሱን አሻሽሎ ባለመቅረቡ ፍርድ ቤቱ ለጥር 6 ቀን 2007 ዓ.ም አቃቤ ህግ ክሱን አሻሽሎ እንዲቀርብ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

ጦማሪያኑ እና ጋዜጠኞች ላለፉት ዘጠኝ ወራት በእስር ላይ መሆናቸው ይታወቃል፡፡