በሰሜን ሸዋ አገዛዙ በደንገት የገበሬዎችን መሣሪያ ገፈፈ – ሙሉቀን ተስፋው

ሚያዚያ 16 ቀን 2009 ዓ.ም በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ  መልካ ጅሎ ቀበሌ ልዩ ቦታው አሞራ ቤት በተባለ አካባቢ የወያኔ ወታደሮች በድንገት የዐማራ ገበሬዎችን መሣሪያ መግፈፋቸው ተገልጧል፡፡ ከብት በማርባት የሚታወቁት እነዚህ ገበሬዎች ከብቶቻቸውን ውኃ አጠጥተው ምሳ የያዙትን ምሳ በመመገብ ላይ ሳሉ ነበር ድንገት በሁለት ፓትሮል የተጫኑ የወያኔ ወታደሮች ደርሰው ገበሬዎቹን ትጥቅ የቀሙት፡፡ በዕለቱ 27 ክላሽንኮፍ መሣሪያዎች እንደተወሰደባቸው የገለጹት ገበሬዎች በሌሎች አካባቢዎችም ተመሳሳይ ድንገተኛ ጥቃት ሊደረግ ስለሚችል ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳስበዋል፡፡

በሰሜን ሸዋ ምንጃር ወረዳ በአካባቢው ያሉ የከረዩ ጎሣዎች በሕወሓትና በኦሕዴድ አይዞህ ባይነት ተከታታይ ጥቃት እንደሚያደርሱባቸው የገለጹ ሲሆን የዐማራዎቹ መሣሪያ ከተገፈፈ በኋላ ከረዩዎቹ እንደገና እንደታጠቁ ገለጸዋል፡፡ የዐማራዎቹ ገበሬዎችና አርብቶ አደሮች መሣሪያ እንዲገፈፍ ያደረጉትን የምንጃር ወረዳ ካቢኔዎች የመለየት ሥረ እንደተሠራም በተጨማሪ ተገለጧል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.